31/08/2026
ለተማሪዎች 5 ጠቃሚ መተግበርያዎች !
1. Goodnotes
Goodnotes ለተማሪዎች የሚሆን ምርጥ የማስታወሻ መያዣ (best note taking ) መተግበሪያ ሲሆን ለሁሉም ተጠቃሚ ሊሆን የሚችል ብዙ ፊቸር ያለው የnote taking app ነው።
Goodnotesን በመጠቀም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ Digital notes ማዘጋጀት እንችላለን።
Pdf ፋይሎችን አፕሎድ አድርገን annotate ማድረግ ያስችለናል።
ወሳኝ የምንላቸውን መረጃዎች highlight ማድረግ ና ኖቶቻችንን የተለያዩ ዲቫይዞች ላይ Sync ማድረግም ያስችለናል።
2. FocusPomo
ይህ አፕ በጥናት ግዜ ትኩረታችን እንዳይሰረቅ Pomodoro የተሰኘውን ዘዴ በመጠቀም ስናጠና distracted እንዳንሆን ይዳናል።
ይመተግበሪያ ለግዜው ለIOS ወይም ለiPhone ተጠበቃሚዎች ብቻ የሚገኝ ነው።
3. Quizlet
Quizlet ተማሪዎች ለፈተና ስንዘጋጅ አጫጭር ኖቶች ለማውጣት ፣ በሌሎች ተማሪዎች የተዘጋጁ የጥናት ስልት ስብስቦችን ለማግኘት ና ጥናታችንን ውጤታማ ለማድረግ የሚረዳን መተግበሪያ ሲሆን ፤ ለመምህራንም የሚረዳ ፊቸር አለው።
Quizlet ለiOS ና ለWindows የሚሆን አፕ ያለው ሲሆን ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች በweb browsers https://Quizlet.com ላይ ገብተን Signup አድርገን መጠቀም እንችላለን።
4. GroupMe
ይህ መተግበሪያ ለኮሌጅ ወይም ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከክፍል ጓደኞቻቸውን ና ከካምፓስ መሃበረሰብ ጋር መረጃ ለመለዋወጥ የሚረዳ ና በክላስ ውስጥ ስለ ፈተና እንዲሁም ስለ አሳይንመንቶች ለመነጋገር ግሩፕ ቻት ማድረግ ያስችላል ።
5. Microsoft OneNote
OneNote ተማሪዎች ሁሉንም የክፍል ማስታወሻዎቻቸውን ለአጠቃቀም ቀላል በሆነ መልኩ ለማደራጀት ይረዳል ፤ OneNoteን በመጠቀም ተማሪዎች የሚይዟቸውን የክላስ ማስታወሻዎች በሰሚስተር ፣ በSubject ና በተለያዩ ቶፒኮች በመከፋፈል ማደራጀት ከማስቻሉም በላይ online ወደ OneDrive Sync ማድረግ ፣ የዕጅ ጽሁፍ ማስገባት ና ሌሎችም በርካታ ፊቸሮች አሉት ።
Facebook : https://facebook.com/DeritaTech
Telegram : https://t.me/DeritaTech
X : https://x.com/Deritatech
Youtube : https://Youtube.com/DeritaTechSolution
| Blog : https://DeritaTech.blogSpot.com/