ዋኖስ ሚዲያ

ዋኖስ ሚዲያ Fact | First | Accountable

“ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ጉዳዮች በመሳሪያ ሳይሆን በውይይት መፍታት አለባቸው” — ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ በሀገሪቱ ...
22/08/2026

“ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ጉዳዮች በመሳሪያ ሳይሆን በውይይት መፍታት አለባቸው” — ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ በሀገሪቱ የሚነሱ ጥያቄዎችና አለመግባባቶች በመሳሪያ ሳይሆን በውይይት፣ በምክክርና በመግባባት መፍታት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ይህን አቋም በቅርቡ በተካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ በንግግራቸው ማስተላለፋቸው ተገልጿል።

ኮሚሽነሩ በንግግራቸው፣ ለ46 ቀናት በተካሄደው የምክክር ሂደት ወደ 4 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች በመወያየትና በመመካከር ሀሳቦቻቸውን ማቅረባቸውን አድንቀዋል። ይህም ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን በውይይት ማስተናገድና በጋራ ውጤት ላይ መድረስ እንደሚችሉ ያሳየ ልምድ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን፣ የሀገር ጉዳዮችን በኃይል ለመፍታት መሞከር ከመሆኑ ይልቅ ሁሉም ወገኖች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በግልጽ መነጋገር የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። የኮሚሽኑም ዋና ተልዕኮ ተለያዩ ወገኖችን በማሰባሰብ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር መሆኑን አስረድተዋል።

በተለይም ወጣቶች ጥያቄዎቻቸውን በኃይል ከመግለጽ ይልቅ ወደ ውይይት ማምጣት እንደሚገባቸው ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። ችግሮችን በመነጋገር መፍታት የጋራ መግባባትን በማስፋት ለሀገር ዘላቂ ሰላም መሠረት ሊሆን እንደሚችልም አስገንዝበዋል።

በመሆኑም የሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ኢትዮጵያውያን በልዩነት ውስጥ ተቀምጠው መነጋገር፣ መደማመጥና የጋራ መፍትሄ መፈለግ እንደሚችሉ ያሳየ ልምድ መሆኑ ተጠቁሟል።

በእርስዎ እይታ፣ የሀገሪቱ ጥያቄዎች በውይይትና በምክክር መፍታት ይቻላል? ሀሳብዎን ያካፍሉን።

**ሰላም ለኢትዮጵያ።
ሰላም ለሕዝባችን።**

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ 14 ዓመታት ተቆጠሩአዲስ አበባ፦ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ዛሬ 14 ዓመታት ተቆጠሩ።መለስ ዜ...
20/08/2026

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ 14 ዓመታት ተቆጠሩ

አዲስ አበባ፦ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ዛሬ 14 ዓመታት ተቆጠሩ።

መለስ ዜናዊ በ57 ዓመታቸው በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራሰልስ በሕክምና ላይ እያሉ ነሐሴ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያን መንግሥት ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ በመምራት እስከ ሕይወታቸው ማለፍ ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት መለስ ዜናዊ፣ በሀገሪቱ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የልማት ታሪክ ላይ የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል።

በአስተዳደራቸው ዘመን የተመዘገቡ የልማትና የኢኮኖሚ ለውጦች እንዲሁም በውጭ ግንኙነትና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የነበራቸው ተሳትፎ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ በአዎንታዊ መልኩ ይታወሳል።

በሌላ በኩል የመለስ ዜናዊ የፖለቲካ ቆይታና የመንግሥት አስተዳደር በተለያዩ ወቅቶች ትችትና ክርክር ያስነሳ መሆኑም ይታወሳል።

ከሕይወታቸው ማለፍ 14ኛ ዓመት ላይ በደረሱበት ዛሬ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የፖለቲካ ታሪክና ለሀገሪቱ ያበረከቱት አስተዋጽዖ በተለያዩ ወገኖች እየተዘከረ ይገኛል።

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የወርቅ ማዕድን ጉድጓድ ተደርምሶ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ ++++++ባንጉይ፦ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ምዕራባዊ ክፍል፣ ከካሜሩን ድንበር አቅራ...
20/08/2026

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የወርቅ ማዕድን ጉድጓድ ተደርምሶ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
++++++
ባንጉይ፦ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ምዕራባዊ ክፍል፣ ከካሜሩን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ዛምቦዬ መንደር የወርቅ ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ተደርምሶ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።

በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡና ከተጎዱት መካከል የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እንዲሁም የጎረቤቷ ካሜሩን ዜጎች እንደሚገኙ ተነግሯል።

አደጋው በባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ላይ መከሰቱ ተገልጿል። የጉድጓዱ መደርመስ በማዕድን ማውጫው ውስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ እንዲደርስ አድርጓል።

የአካባቢው ዓቃቤ ሕግ የአደጋውን መንስኤ እና የማዕድን ማውጫውን ሕጋዊነት ለማጣራት ምርመራ መጀመሩን ገልጿል።

በተጨማሪም በአደጋው ቦታ የነፍስ አድን ሥራዎችና ከፍርስራሹ ውስጥ አስከሬኖችን የማውጣት ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠላቸው ተገልጿል።

የአደጋው ምርመራ በመቀጠሉ፣ የሟቾችና የተጎዱት ቁጥር እንዲሁም የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል።

 🇪🇹የሰንደቅ አላማ ጉዳይ "አሁን ያለው ይቀጥል" የሚለው አስማምቶ፣ "አርማው አካታች በሆነ መልኩ ለወደፊት ይታይ" የሚል አማራጭ ሀሳብ ቀረበለት።👉 ለኢትዮጵያ "ብሔራዊ ቋንቋ ለጊዜው አያስ...
20/08/2026

🇪🇹

የሰንደቅ አላማ ጉዳይ "አሁን ያለው ይቀጥል" የሚለው አስማምቶ፣ "አርማው አካታች በሆነ መልኩ ለወደፊት ይታይ" የሚል አማራጭ ሀሳብ ቀረበለት።

👉 ለኢትዮጵያ "ብሔራዊ ቋንቋ ለጊዜው አያስፈልግም" ፤ ካስፈለገ ለወደፊት ይኖራል በሚል ተመካካሪዎችን አስማምቷል።

👉 አምስት ቋንቋዎች የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ፣ ሌሎችም መስፈርት ወጥቶላቸው ለወደፊት እንዲታዩ ተብሏል።

ከ8ቱም ቡድኖች በተመረጡ አጠናቃሪዎች የተዋቀረው አዘጋጅ ቡድን እያንዳንዳቸው 500 ሰዎችን ከያዙ 8 ቡድኖች ተቀብሎ ያጣጣማቸውን፣ ድግግሞሽ እንዳይኖር ያስወገደላቸውን የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች አዘጋጅቶ የ8ቱንም ቡድኖች ምክረ ሀሳቦች የያዘ ቃለጉባዔ ለ8ቱም ቡድኖች ዛሬ አቅርቧል።

ተመካካካሪዎች በተለያዩ ቡድኖች ተደራጅተው ሀሳብ ከማመንጨት እስከ በሀሳቦቹ መከራከር ድረስ ከመከሩባቸው ስምንት አጀንዳዎች መካከል የሀገር ግንባት አጀንዳ አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ አጀንዳ በዛሬው ቃለጉባዔ ከተነሱት ምክሮች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።

ብሔራዊ ቋንቋ ፦

የቋንቋ ጉዳይን በተመለከተ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ይኑራት? ወይስ አይኑራት? እና ይኑራት ከተባለ ደግሞ አማርኛ ይሁን፣ አፋን ኦሮሞ ይሁን የሚሉ ምክረ ሀሳቦች ከተመካካሪዎች ቀርበው ሲያከራክሩ ሰንብተዋል።

ከ8ቱም ቡድኖች የተመረጡ 120 አባላት ያሉት በምክረ ሀሳቦቹ አንድ ወጥ አጀንዳ የሚያዘጅ ቡድን እያንዳቸው 500 ሰዎች ለያዙት ቡድኖች 8ቱም ቡድኖች ባነበበው ቃለጉባዔ መሰረት ደግሞ፣ "አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ብሔራዊ ቋንቋ አያስፈልገንም" የሚለው ስምምነት እንደተደረሰበት የአንድ አጀንዳው ተሳታፊ ነግረውናል።

"ሲያስፈልግ እንደ ሁኔታው ታይቶ ካሉት ቋንቋዎች አስፈላጊው ሊደረግ ይችላል" የሚል ምክረ ሀሳብም ተያይዞ መቅረቡን ገልጸዋል።

የሥራ ቋንቋ ፦

የፌዴራል የሥራ ቋንቋን በተመለከተ ደግሞ፣ መጀመሪያ አምስት ቋንቋዎች ቀርበው፣ በኋላ ደግሞ ወደ 13 ቋንቋዎች የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ተመካካሪዎች ምክረ ሀሳብ ሲያቀርቡ ነበር።

በተነበበው ቃለጉባዔ ደግሞ፣
- አማርኛ
- አፋን ኦሮሞ
- ትግርኛ
- አፋርኛ
- ሶማሊኛ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ፣ በቀጣይነት ሌሎችም እንዲከቱ የሚል ሀሳብ በአመዛኙ ተመካካሪዎች መቅረቡን ተሳታፊው ተናግረዋል።

እንዲሁም ፦
- ወላይትኛ
- ሲዳምኛ
- ጉራግኛ
- ከምባትኛ
- አገውኛ
- ከፊቾ/ከፍኛ
- ጋሞኛ ቋንቋዎችም መስፈርት ወጥቶላቸው "እንደተናጋሪው ብዛት መስፈርት እየታዬ" ለወደፊት የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ የሚል አማራጭ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።

የሰንደቅ አላማ ፦

የሰንደቅ አላማን ጉዳይ በተመለከተ ተመካካሪዎች አሁን ያለው ይቀጥል፤ አርማው ይቀየር፣ ሲቀየር ደግሞ የሕዳሴ ግድብ ይሁን፣ የዓድዋ ድል፣ የእርግብና ሌሎች ይሁን የሚሉ አማራጭ ምክረ ሀሳቦች ከጉባያተኞች ቀርበው ነበር።

ዛሬ በተነበበውና አስተያየት ተሰጥቶበት ነገ ይጠናቀቃል በተባለው ቃለጉባዔ ደግሞ፣ "አሁን ያለው ይቀጥል እና አርማው አካታች በሆነ መልኩ ለወደፊት ይታይ" የሚሉ ሁለት ምክረ ሀሳቦች መቅረባቸው ተገልጿል። "አካታች በሆነ መልኩ" ሲባል "ህዝቡ ለወደፊት ቀርቦ እንዲወስን" መባሉ ተመልክቷል።

ብሔራዊ መዝሙር፦

ኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በተመለከተ የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወቃል። በዛሬው ውሎ ደግሞ፣ "ብሔራዊ መዝሙር እንዳለ ይቀጥል" የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡን ተመካካሪዎች ተናግረዋል።

የክልሎችን መዝሙር በተመለከተም፣ "መዝሙሩ ይኑር፤ የክልሉን ነባራዊ ሁኔት አካታች ያድርግ፣ በአላስፈላጊት የገቡ መብትን የሚነኩ ግጭት የሚቀሰቅሱ ሀሳቦች ካሉ ይታረሙ" የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡም ተገልጿል።

ከዚህ አጀንዳ በተጨማሪ ሌሎች አጀንዳዎችም የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች የቀረቡላቸው ሲሆን፣ ይህን ጨምሮ የሁሉም የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ሰነድ አስተያየት ካለ ተካቶባቸው ነገ ለ4ሺሕው ጉባያተኞች ቀርበው ለመጨረሻ ጊዜ ይሰነዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዮቹን ተከታትሎ መረጃ የሚያቀርብ ይሆናል።

ከውኃ ውጭ መኖር የማይችለው 16 ዓመቱ ታዳጊ፤ አስገራሚውና አሳዛኙ ታሪክአስገራሚ የጤና ታሪክ፦ በሕንድ ዌስት ቤንጋል ግዛት የሚኖረው 16 ዓመቱ ኢቅባል ሼክ ከውኃ ውጭ መቆየት በሚያስቸግረው...
20/08/2026

ከውኃ ውጭ መኖር የማይችለው 16 ዓመቱ ታዳጊ፤ አስገራሚውና አሳዛኙ ታሪክ

አስገራሚ የጤና ታሪክ፦ በሕንድ ዌስት ቤንጋል ግዛት የሚኖረው 16 ዓመቱ ኢቅባል ሼክ ከውኃ ውጭ መቆየት በሚያስቸግረው አስገራሚ የጤና ችግር ምክንያት ላለፉት አምስት ዓመታት ከፍተኛ ፈተና ውስጥ እንደኖረ ተገልጿል።

እንደተዘገበው፣ ኢቅባል ከ11 ዓመቱ ጀምሮ ከውኃ ውጭ ሲቆይ በቆዳውና በሰውነቱ ላይ ከባድ እና የሚያቃጥል ሕመም ይሰማዋል። በመሆኑም መብላት፣ መተኛትና የዕለት ተዕለት ጊዜውን ማሳለፍ እንኳን በኩሬ ውኃ ውስጥ ሆኖ ማድረግ እንደተገደደ ተገልጿል።

ቤተሰቦቹ ለችግሩ መፍትሔ ለማግኘት ኢቅባልን ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎችና የባህላዊ ሕክምና ተቋማት ቢወስዱትም፣ የጤና ችግሩን ትክክለኛ መንስኤ ለመለየት እንዳልተቻለ ተነግሯል።

ታዳጊው በውኃ ውስጥ ሆኖ ምግብ ሲመገብ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ ግን ታሪኩ ሰፊ ትኩረት አግኝቷል። በዚህም ታዋቂው የሕንድ ባለሀብት አናንት አምባኒ የታዳጊውን የሕክምና ወጪ ለመሸፈን ቃል እንደገቡ ተዘግቧል።

በአሁኑ ወቅትም ኢቅባል በልዩ አውሮፕላን ወደ ሙምባይ ተወስዶ በከፍተኛ የሕክምና ተቋም ልዩ ክትትል እያገኘ መሆኑ ተገልጿል።

የታዳጊው ታሪክ የጤና እና የመደበኛ ኑሮ ዋጋ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳስብ ነው። ያለሕመም መተንፈስ፣ መንቀሳቀስ፣ መብላትና መተኛት በየዕለቱ በቀላሉ የምናደርጋቸው ቢሆኑም፣ ለብዙ ሰዎች ግን ትልቅ ጸጋ ናቸው።

ስለዚህ ጤናችንን እንጠብቅ፤ ላለን ጤናም ሁልጊዜ ምስጋና እናቅርብ።

ምንጭ፦ Dylanpage

ተፈጥሮ፣ ባህል፣ ታሪክ እና ዘመናዊ ልማት በተዋህዶ የተጣመሩባትን ኢትዮጵያን የመጎብኘት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው! 🇪🇹​በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የልማት ራዕይና አመራር፣ ኢ...
19/08/2026

ተፈጥሮ፣ ባህል፣ ታሪክ እና ዘመናዊ ልማት በተዋህዶ የተጣመሩባትን ኢትዮጵያን የመጎብኘት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው! 🇪🇹
​በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የልማት ራዕይና አመራር፣ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ ላይ ትገኛለች። ይህም የማረኩ ተፈጥሯዊ የመሬት አቀማመጦችን ከዘመናዊ የእንግዳ ተቀባይነት አገልግሎትና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ጋር የሚያገናኙ አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን እውን አድርጓል።
​ከአስደናቂው የወንጪ የእሳተ ገሞራ ሀይቅ (Wanchi Crater Lake) እና ቤኑና ሎጅ እስከ ዳንዲ ኤኮ ሎጅ፣ ሃላላ ኬላ እና ጎርጎራ የቱሪዝም ፕሮጀክት ድረስ ያሉ አዳዲስ መስህቦች፣ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን በአዲስና አስደሳች መንገድ እንዲያዩ ሰፊ እድል ፈጥረዋል።
​ይህ አጠቃላይ የመሬት ገጽታ ለውጥ መዲናችን አዲስ አበባንም የሸፈነ ሲሆን፣ የወንዞች ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ሳቢ ህዝባዊ ቦታዎችን በመፍጠር፣ የከተማዋን ትስስር በማሻሻልና ለአዲሷ አዲስ አበባ አዲስ የከተማነት መገለጫ (Urban Identity) በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
​=> ኢትዮጵያ ዓለምን ለመቀበል ዝግጁ ነች!
ይምጡና ተራሮቻችንን፣ ሀይቆቻችንን፣ ጫካዎቻችንን፣ ወንዞቻችንን፣ የዱር እንስሳቶቻችንን፣ ጥንታዊ ቅርሶቻችንን፣ ህያው ከተሞቻችንን እና የሙቀት የተሞላውን እንግዳ ተቀባይነታችንን ይለማመዱ። ኢትዮጵያን ይወቁ! ኢትዮጵያን ይጎብኙ! በኢትዮጵያ ይደሰቱ!
​የጉዞ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ!
​ #የጉዞጊዜወደኢትዮጵያ #ኢትዮጵያንይጎብኙ #ኢትዮጵያ #ቱሪዝም #ኢትዮጵያንይወቁ #ወንጪ #ቤኑናሎጅ #ዳንዲኤኮሎጅ #ሃላላኬላ #ጎርጎራ #አዲስአበባ

የአፍሪካ ህብረት በሱዳን የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ተቀናቃኝ መንግሥታትን መመስረት አስጠነቀቀ====ካርቱም፦ የአፍሪካ ህብረት (AU) በሱዳን የውጭ አካላት ጣልቃ ገብነትንና ተቀናቃኝ መንግሥታት...
18/08/2026

የአፍሪካ ህብረት በሱዳን የውጭ ጣልቃ ገብነትንና ተቀናቃኝ መንግሥታትን መመስረት አስጠነቀቀ
====
ካርቱም፦ የአፍሪካ ህብረት (AU) በሱዳን የውጭ አካላት ጣልቃ ገብነትንና ተቀናቃኝ መንግሥታትን ለመመስረት የሚደረጉ ሙከራዎችን በጥብቅ በመቃወም፣ እነዚህ እርምጃዎች በሀገሪቱ ያለውን ግጭት የበለጠ ሊያባብሱና የሱዳንን አንድነትና ሉዓላዊነት ሊያሰጉ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ።

ማስጠንቀቂያው የመጣው የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት ልዑክ በሱዳን ያደረገውን የሁለት ቀናት ጉብኝት ተከትሎ ነው።

ልዑኩ በካርቱም ከሱዳን የጦር ኃይሎች አዛዥ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር ባደረገው ውይይት፣ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ውይይት፣ ብሔራዊ እርቅና በሱዳኖች የሚመራ የፖለቲካ መፍትሔ አማራጭ የሌላቸው መንገዶች መሆናቸውን ገልጿል።

የአፍሪካ ህብረቱ በተጨማሪም በጦርነቱ የተጎዱ ሰዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ የተሻለ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት፣ የተኩስ አቁም እና ሁሉንም ወገኖች ያካተተ የፖለቲካ ሽግግር እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።

ህብረቱ የሚፈልገው የፖለቲካ ሽግግር በመጨረሻ በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ የሚመረጥ ሕገ-መንግሥታዊ መንግሥት እንዲቋቋም የሚያስችል መሆኑንም ገልጿል።

ሱዳን ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሱዳን የጦር ኃይሎች (SAF) እና በፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) መካከል በተካሄደ ከባድ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች። ግጭቱም በሀገሪቱ ሰፊ የሰብዓዊ ቀውስና የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲባባስ አድርጓል።

የአፍሪካ ህብረቱ አቋም ዋና ትኩረቱ የሱዳንን አንድነትና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ፣ ግጭቱን በውይይት ማስቆም እና ሱዳንን ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር ማሸጋገር እንደሆነ ተገልጿል።

የባሕር በር እጥረት ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ወጪና ሉዓላዊነት ሥጋት እያጋለጣት መሆኑ ተገለጸ====አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ የራሷ የባሕር በር ባለመኖሯ ለከፍተኛ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወጪ፣ ...
18/08/2026

የባሕር በር እጥረት ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ወጪና ሉዓላዊነት ሥጋት እያጋለጣት መሆኑ ተገለጸ
====
አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ የራሷ የባሕር በር ባለመኖሯ ለከፍተኛ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወጪ፣ ለተለያዩ ጫናዎችና ለሉዓላዊነት ሥጋት ተጋላጭ መሆኗን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ከበሪሳ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የባሕር በር እጥረት በተለይ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን አስረድተዋል።

የራሷ የባሕር በር የሌላት ሀገር በተለያዩ የውጭ ጫናዎች ልትጋለጥ እንደምትችል የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ይህም በሀገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ገልጸዋል።

በተጨማሪም የራስ የባሕር በር መኖሩ የወደብ ኪራይንና ሌሎች የሎጂስቲክስ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የአገልግሎት ዋጋን ተመጣጣኝ ለማድረግና የምርት አቅርቦትን ለማፋጠን ወሳኝ ሚና እንዳለው ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

አሁን ግን ኢትዮጵያ የወደብ አገልግሎትን በራሷ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ባለመቻሏ ለወደብ ኪራይና ለተለያዩ የሎጂስቲክስ ወጪዎች ከፍተኛ ገንዘብ እያወጣች መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በተለይም አንድ ምርት ከውጭ ሀገር ተገዝቶ በፍጥነት እንዲገባ ሲያስፈልግ፣ የወደብ አስተዳደርን፣ የጭነትና የማውረጃ ሥራዎችን፣ የመርከብ የመቆሚያ ቅደም ተከተልን እና የምርቶች ቅድሚያ የሚወስነው ኢትዮጵያ ባለመሆኗ በአቅርቦት ላይ ተጨማሪ ጫና እንደሚፈጠር ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም፣ የራሷ የምትቆጣጠረው የባሕር በር ወይም ወደብ ማግኘት ለኢትዮጵያ የወደብ ወጪን ከመቀነስ ባሻገር የንግድ ፍሰትን፣ የምርት አቅርቦትንና የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ አቅም ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

“እጁ ንጹሕ የሆነን ሰው ማንም ባለሀብትም ሆነ ቡድን ሊገዛው አይችልም። ሙሰኛን ግን በሻይ፣ በውኃ፣ በላፕቶፕ ወይም በመሬት ታገኘዋለህ።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
16/08/2026

“እጁ ንጹሕ የሆነን ሰው ማንም ባለሀብትም ሆነ ቡድን ሊገዛው አይችልም። ሙሰኛን ግን በሻይ፣ በውኃ፣ በላፕቶፕ ወይም በመሬት ታገኘዋለህ።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ያሲኖ በኢቢኤስ (EBS) የ «ቤተሰብ ጨዋታ» አቅራቢዎች ውድድር አሸናፊ ሆነበኢቢኤስ ቴሌቪዥን (EBS TV) ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለውን የ «ቤተሰብ ጨዋታ» ፕሮግራምን በዋና አቅራቢነት ለመም...
16/08/2026

ያሲኖ በኢቢኤስ (EBS) የ «ቤተሰብ ጨዋታ» አቅራቢዎች ውድድር አሸናፊ ሆነ
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን (EBS TV) ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለውን የ «ቤተሰብ ጨዋታ» ፕሮግራምን በዋና አቅራቢነት ለመምራት ሲካሄድ በቆየው ከፍተኛ ውድድር ያሲኖ (Yasino) አሸናፊ በመሆን ተመርጧል።

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዋኖስ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share