EthioScie Tech Zone

EthioScie Tech Zone Technology tips and tricks

ሰላም የ ኢትዮ ሳይ ቴክ ዞን ተከታታዮች የ YouTube ቻናሌ በማላቀው ምክያት ተዘግቶብኛል እናም Subscribe በማድረግ ወደ አዲስ ወደ ተከፈተው ቻናል ተቀላቀሉ እናም እንደጠፋው አቃለው...
17/10/2022

ሰላም የ ኢትዮ ሳይ ቴክ ዞን ተከታታዮች የ YouTube ቻናሌ በማላቀው ምክያት ተዘግቶብኛል እናም Subscribe በማድረግ ወደ አዲስ ወደ ተከፈተው ቻናል ተቀላቀሉ እናም እንደጠፋው አቃለው ግን ትንሽ ቢዚ ሆኜ ነው አሁን ለናንተ ቪድዮ ሰርቼ አዘጋጅቼለው ተጨማሪ ቪድዮ እስካዘጋጅ እናንተም ቻናሉን Subscribe በማድረግ 1000 ሺህ Subscriber ሲደርስ ያዘጋጀውትን አዳዲስ ቪድዮ መልቀቅ ጀምራለው እስከዛ ድረስ ደሞ የጠፉትን ቪድዮች ይለቀቃሉ እናንተም በተቻላቹት መጠን ተባበሩኝ ቻናሉን Subscribe እና Share በማድረግ እንድትተባበሩ ስል ጠይቃለው አመሰግናለው። ሊንክ ከስር ባለው ግቡ ወይም YouTube ላይ EthioScie Tech Zone ብላቹ ማግኘት ትችላላችሁ https://www.youtube.com/channel/UC1Q8guhR26CbKJJLc4Lo5Rw?sub_confirmation=1 እና ደሞ ጠፍተሀል ምንድነው ላላቹኝ አመሰግናለሁ እና ምትፈልጉትን ጥያቄዎች ሆኑ አስተያየት ልታጋሩኝ ትችላላችሁ ።

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!! ……………✝️✝️✝️……………
07/01/2021

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!!
……………✝️✝️✝️……………

 #ዛሬ አንድ ገራሚ ነገር ልንገራችሁ እስቲ ።ዲጂታል ማሽተት ቴክኖሎጂ ምንድነው?እስከዚህ ጊዜ ድረስ የመስመር ላይ ግንኙነት ሁለት የስሜት ህዋሳቶቻችንን ፣ የማየት እና የመስማት ስሜታችንን ...
08/12/2020

#ዛሬ አንድ ገራሚ ነገር ልንገራችሁ እስቲ ።

ዲጂታል ማሽተት ቴክኖሎጂ ምንድነው?

እስከዚህ ጊዜ ድረስ የመስመር ላይ ግንኙነት ሁለት የስሜት ህዋሳቶቻችንን ፣ የማየት እና የመስማት ስሜታችንን ብቻ ያካተተ ነበር ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ሶስተኛውን ማለትም አፍንጫን በመጠቀም የመሽተት ስሜትን ያካትታል ፡፡ የዲጂታል ሽታ ቴክኖሎጂ የኢ-አፍንጫ ዋና አተገባበር ነው ፡፡ በዲጂታል ሽታ ቴክኖሎጂ አማካኝነት በበይነመረብ በኩል ማሽተት ማስተላለፍ ፣ ማስተላለፍ እና መቀበል ይቻላል ፡፡
ለተጠቃሚው ይበልጥ ተጨባጭ የሆኑ የፊልም ውጤቶች እንዲሰማው በፊልሞች ወይም በጨዋታዎች ውስጥ የዲጂታል ሽታ በጣም አዲስ ተቋም ተዋወቀ ፡፡ ለዚህ መሠረታዊው ሀሳብ ሽቶ አምራች ኩባንያዎች ለሽቶቻቸው ማስታወቂያዎች የተሰጡ ናቸው ፡፡
የዲጂታል ሽታ የሚሠራው የጄል እንክብሎችን በእንፋሎት ከሚተነተኑ ሽታዎች በተከታታይ በማያ ገጹ ጥግ በአንዱ ወደ አራት የአየር ዥረቶች ነው ፡፡ እነዚህ የአየር ዥረቶች በአድናቂዎች ከማያ ገጹ ገጽ ትይዩ ይወጣሉ ፣ እና የእነሱ ጥንካሬ እና አቅጣጫን በመለዋወጥ በማያ ገጹ ላይ ወዳለው ቦታ ሁሉ መዓዛውን ያሰራጫል ፡፡
የሃርድዌር መሳሪያዎች ሲንሸሲዘር ማሽተት የሽታ ሲንሳይዘር ማለት ሽቶቹን ለማመንጨት የሚያገለግል መሳሪያ ነው ፡፡ እንደ አይ.ኤስ.ኤም.ኤል የመሳሰሉት ኮምፒተርን በመጠቀም ጋዝ ለማምረት የሚያገለግል መሳሪያ ነው ፡፡ በገበያው ውስጥ የተለያዩ አይነቶች የማሽተት ማቀነባበሪያዎች አሉ ፣ ግን ለኮምፒዩተር ማሽተት ማቀነባበሪያው በዲጂቶች ኢንዱስትሪ የተሰራ ነው ፡፡
iSmell:
አይ.ኤስ.ኤም. በተከታታይ ወይም በዩኤስቢ ወደብ በኩል ከፒሲ ጋር የሚገናኝ የፒሲ ድምጽ ማጉያ መጠን ያለው የከባቢያዊ መሣሪያ ነው ፡፡ ከቀለም ጄት አታሚዎች የቀለም ካርትሬጅዎችን ከሚጠቀሙበት ጋር ተመሳሳይ እና የሚተኩ የሚጠቀሙባቸውን የፍጆታ ካርቶሪዎችን ይጠቀማል ፡፡
አይ.ኤስ.ኤም. መሣሪያው የዲጂታል መዓዛ ፋይልን ያነባል ፣ በማጠራቀሚያ ውስጥ ከተከማቹ 128 ኬሚካሎች “ቤተ-ስዕል” ውስጥ ሽታ ይፈጥራል ፣ ከዚያም በትንሽ ማራገቢያ ወደ አየር ይወጣል።

❤️SHARE AND SUPPORT❤️

➖Ⓒ ➖

https://youtu.be/_7pL7y9NCTw
02/12/2020

https://youtu.be/_7pL7y9NCTw

💥የ Wi-Fi ፍጥነት የሚጨምርልን ምርጥ 5 ሴቲንጎችን ብቻ በማስተካከል || Best 5 Settings To increase your Wi-Fi speed ?ቴሌ ለምን አስተካክለው አልሰጡንም ? 💥Sponsored by ❤️ ...

11 Secret Codes That Unlock Hidden Features on Your Phone(1) Field Mode: 3001 #12345 #(2)General Test Mode:  #0 # (3) Di...
27/11/2020

11 Secret Codes That Unlock Hidden Features on Your Phone

(1) Field Mode: 3001 #12345 #

(2)General Test Mode: #0 #

(3) Display your IMEI: #06 #

(4) Check Your Call Forwarding: #67 #

(5) Get Even More Info on Call Forwarding: #61 #

(6) Check Your Available Minutes: 646 #

(7) Check Your Bill Balance: 225 #

(8) Hide Your Phone From Caller ID: #31 #
I could only get this to work on Android. But entering this code prompted a pop-up stating that my Caller ID had been disabled. In order to re-instate Caller ID, enter 31 # .

(9) Check Your Billing Cycle: 3282 #

(10)SMS Message Center: 50057672 #

(11) Activate Call Waiting: 43 #
This code will activate call waiting; you can deactivate it by entering #43 #.

❤️SHARE AND SUPPORT❤️

➖Ⓒ ➖

MQ-9 Reaper - ሰው አልባዋ የመከላከያ ሰራዊት ተዋጊ ድሮን (drone)ሰሞኑን በትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት MQ-9 Reaper የተባለች ...
24/11/2020

MQ-9 Reaper - ሰው አልባዋ የመከላከያ ሰራዊት ተዋጊ ድሮን (drone)

ሰሞኑን በትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት MQ-9 Reaper የተባለች የስለላ እና ተዋጊ ድሮን (ሰው አልባ ጀት ) እየተጠቀመ እንደሆነ በተለያዩ መንገዶች እየተጠቆመ ነው። የ አየር ሃይል አዛዡ ይህን በቀጥታ የሚያረጋግጥ ነገር ባይናገሩም፣ "ጠላቶቻችን በአሁኑ ሰአት የት እንዳሉ እናውቃለን" ማለታቸው ይህን ጭምጭምታ የሚያረጋግጥ ነው።

ለመሆኑ MQ-9 Reaper ማን ናት? ምን ምን ብቃቶች አሏት? ለጠቅላላ እውቀት ይረዳ ዘንድ በዚህ አጭር ፅሁፍ እንደሚከተለው ዳስሻታለሁ።

MQ-9 Reaper - አሜሪካ ሰራሿ ተዋጊ ድሮን

MQ-9 Reaper አሜሪካ ሰራሿ ሰው አልባ ድሮን 11 ሜትር ቁመት፣ 20 ሜትር የክንፍ ስፋት ያላት ለተለያዩ ሚሽኖች የምትውል ሰው አልባ ድሮን ናት። General Atomics Aeronautical Systems, Inc በተባለው የ አሜሪካ ዲፌንስ ኮንትራክተር ዲዛይን ተደርጋ የተሰራችዋ ይችው ድሮን ለመጀመሪያ ጊዜ ኦፕሬሽን ላይ የዋለቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 2007 ሲሆን አሜሪካ በዋናነት በውጭ ሀገራት ለምታደርጋቸው የስለላ እንዲሁም ለደህንነት ስጋት የሆኑ ተንቀሳቃሽም ሆነ የቆመ ታርገጌቶችን ነጥሎ የመምታት ኦፕሬሽኖቿን በብቃት ለማክናወን የሰራችው ድሮን ነው።

MQ-9 Reaper ድሮን እስከ 1,800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ውስጥ ሆኖ እንቅስቃሴዋን ሙሉ በሙሉ መከታተል እና ማዘዝ ይቻላል።

የድሮኗ አየር ላይ ለብዙ ጊዜ ቆሞ የመቆየት ብቃቷ (Loiter time)፣ ሰፊ ቦታ መሸፈን የሚችለው ሴንሰሯ (wide-range sensors)፣ መሬት ላይ ካሉ ስቴሽኖች ጋር ለመገናኘት ያላት ብቃት እና በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢላማ ብቃቷ (precision weapons) እጅግ ተፈላጊ (high-value)፣ ለአጭር ጊዜ ብቻ እይታ ላይ የሚቆዩ ኢላማዎችን (fleeting and time-sensitive targets) በብቃት ለመሰለል እና አልሞ ለመምታት ለየት ያለ ብቃት አላት።

ድሮኗ የምትልካቸውን ላይቭ ቪዲዮች ጠላት የት እንዳለ ለመከታተል ታስችላለች። የድሮኗ ዋና ብቃት ደግሞ፣ በብርሃን ጨረር እገዛ ተንቀሳቃሽ የሆነን የጠላትን ታርጌት በብቃት መከተታተል መቻሏ እና በዚሁ በብርሃን ጨረር የሚመራ ፈንጂ መሳሪያ (laser-guided munitions) መተኮስ መቻሏ ነው። ይህ ብቃቷ በጣም ኢላማን የጠበቀ (highly accurate)፣ በጣም ትንሽ የሆነ ከኢላማ ታርጌት ውጭ የሚደርስ ጉዳት (low-collateral damage) ያለው ድብደባን ለማድረግ ተመራጭ ያደርጋታል።

ከውጊያ ባሻገር፣ በድንበር አካባቢ ሊኖር የሚችል የህገ-ወጥ የመሳሪያ ዝውውርን እና መሰል የሰርቪላንስ ተግባሮችን ለማከናወን የምትውል ድሮን ናት። ድሮና ተነቃቅላ በኮንቴነር ውስጥ በመግባት ከቦታ ቦታ በቀላሉ መዘዋወር ትችላለች።

ሙሉ ገፅታዋ (specifications)

🔸ይህቺ ድሮን ከታች የተጠቀሱት ጠቅለል ያለ ገፅታ (specifications) አሏት:

📌ዋና ጥቅም - የጠላት ታርጌትን ፈልጎ መጨረስ

📌ቁመት - 11 ሜትር

📌የክንፍ ስፋት - 20 ሜትር

📌ከፍታ - 3.8 ሜትር

📌ያለ ጦር መሳሪያ ክብደት - 2,223 ኪሎ ግራም

📌መጫን የምትችለው የጦር መሳሪያ ክብደት - 1,701 ኪሎ ግራም

📌የበረራ ፍጥነት - በሰዓት 370 ኪሎ ሜትር

📌የበረራ ከፍታ - 50,000 ጫማ (15,240 ሜትር )

📌የአንዷ ድሮን ዋጋ - $64.2 ሚሊዮን (የአሜሪካን ዶላር )

▪️ምንጭ - U.S. Air Force

❤️SHARE AND SUPPORT❤️

➖Ⓒ ➖

https://youtu.be/NFMeBTPIbBo
24/11/2020

https://youtu.be/NFMeBTPIbBo

💥በነፃ ገራሚ የስልክ ስክሪን ሪከርድ ማረግያ App || Best Free Screen Recorder App Without Watermark 2020💥Sponsored by ❤️ Download the software on telegr...

https://youtu.be/HByjOLAR1rk
23/11/2020

https://youtu.be/HByjOLAR1rk

💥ስልካቹ ላይ Storage Full እያለ ለተቸገራችሁ 4 ምርጥ መፍትሔዎች ምንም File ሳናጠፋ||How to fix Insufficient storage space ! 💥Sponsored by ❤️ Download the soft...

የክሮም ብሮዉዘር ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ ዝመና እንዲያደርጉ ጉግል አሳሰበ በጉግል ክሮም የመረጃ ማፈላለጊያዉ (Browser) ላይ ከፍተኛ የሚባል የደህንነት ክፍተት መከሰቱን ተከትሎ ተጠቃሚዎች...
15/11/2020

የክሮም ብሮዉዘር ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ ዝመና እንዲያደርጉ ጉግል አሳሰበ

በጉግል ክሮም የመረጃ ማፈላለጊያዉ (Browser) ላይ ከፍተኛ የሚባል የደህንነት ክፍተት መከሰቱን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ክሮምን (Chrome) በፍጥነት እንዲያዘምኑ ጉግል አሳሰበ፡፡
ከዚህ ቀደም ወቅታቸዉን ጠብቀዉ በሚለቀቁ የሶፍትዌር ዝመናዎች ያልተለዩ የዜሮ ደይ (zero-day) ተጋላጭነቶች እና የደህንነት ክፍተቶች መከሰታቸዉን ጉግል ኩባንያ ገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎም ጉግል ድንገተኛ የሆነ እና ለክፍተቱ መድፈኛ የሚሆኑ ዝመናዎችን (Update) ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያ ተጠቃሚዎች አቅርቧል፡፡
በጉግል የስጋት ትንተና ቡድን የተገኘዉ የጥቃት ተጋላጭነት (CVE-2020-16009) ዘግይቶ የተገኘ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ሲሆን ጉግል ባለፈው ወር 'ለዜሮ-ደይ' ክፍተት የሚሆን መጠገኛ ያቀረበ ቢሆንም የዊንዶውስ ስርዓትን የሚጎዳ ተጨማሪ ክፍተት ተከስቷል፡፡
በክሮም የተገኘዉ (CVE-2020-16009) ተጋላጭነት የጃቫ ስክሪፕትን (JavaScript) ኮድ በሚያስተዳድረው የአሳሽ ክፍል ውስጥ ተደብቆ ተገኝቷል፡፡ ሆኖም ተጠቃሚዎች የክሮም የመረጃ ማፈላለጊያ ወደ version (86.0.4240.183) ወይም ከዚያ በኋላ ወደ ተለቀቁ የክሮም ስሪቶች እንዲያሳድጉ ጉግል አሳስቧል፡፡
የክሮም ተጠቃሚዎች ብሮዉዘሩን ለማዘመን "Customize and control Google Chrome" የሚለዉን በመክፈት "Settings" መምረጥ ከዚም "about chrome"ን በመጫን እየተጠቀሙበት ያለዉ ከ 'Version 86.0.4240.183' በታች ከሆነ አሁኑኑ ክሮሙን ያዘምኑ፡፡
©INSA

❤️SHARE AND SUPPORT❤️

➖Ⓒ ➖

https://www.youtube.com/watch?v=HO4PnPvxoLU
15/11/2020

https://www.youtube.com/watch?v=HO4PnPvxoLU

💥የ Instagram ፎቶ እና ቪድዮ በቀላሉ በ Telegram Download ማድረግ||Download Instagram Image & Video Using Telegram 💥Sponsored by ❤️ Download the soft...

✅ሳምንታዊ አጫጭር ቴክኖሎጂያዊ ዜናዎች1⃣ Microsoft በአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሳይበር ጥቃት ከChina, Iran እና Russia እንደተፈፀመ አረጋግጫለሁ አለ።2⃣ በDarkweb ...
15/11/2020

✅ሳምንታዊ አጫጭር ቴክኖሎጂያዊ ዜናዎች

1⃣ Microsoft በአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሳይበር ጥቃት ከChina, Iran እና Russia እንደተፈፀመ አረጋግጫለሁ አለ።

2⃣ በDarkweb ላይ 15 billion ሀክ የተደረጉ ፓስወርዶች ለሽያጭ እንደቀረቡ ተገለፀ። ለአንዱ ፓስወርድም እስከ £56 ዩሮ እንደሚያስከፍሉም ተነግሯል።

3⃣ ለPS5 አዳዲስ ገራሚ ጌሞች Launch ተደርገዋል እነሱም Spiderman, Godfall,Sackboy,Fortnite,Assassins Creed Vallhala,Dirt 5 የመሳሰሉት ይገኙበታል።

4⃣ ቻይና የአለማችንን የመጀመሪያውን 6G Satellite ወደ Orbit ላከች።

5⃣ Iran ከምድር በታች (Underground) እየሰራች ያለችው የሚሳኤል ቴክኖሎጂ ሀገራትን እያስፈራ እንደሆነ ተነግሯል።

6⃣ ሁለት ጣሊያናዊ የ17 አመት ታዳጊዎች Darkweb ላይ ለLivestreaming murder site (በቀጥታ ሰው ሲገደል የሚያሳይ ዌብ አለ) Bitcoin ሲከፍሉ Report ተደርጎባቸው በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት ይገኛሉ። (ሸቤን በፍቅር እያጣጣሟት ነው😂)

7⃣ በቻይና በተደረገ " Tianfu cup 2020 " Cyber security Challenge ተወዳዳሪዎቹ Windows 10,ios,chrome,Adobe pdf የመሳሰሉትን በብቃት ሀክ እንዳደረጉት ተገልጿል።

8⃣ የNorth korea ሀከሮች torisma የተባለ Spyware በመጠቀም በትልልቅ ካምፓኒዎች ላይ የስራ እድል ለመጠቀም እንደሞከሩ ተነግሯል።

❤️SHARE AND SUPPORT❤️

➖Ⓒ ➖

✅ያውቁ ኖሯል ?💠በአለማችን ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወደ አደገኛ ሀከሮች ኪስ በህገወጥ መንገድ በ Internet  አማካኝነት ገብቷል !💠ወደ ፊትም ይህን መሰል ጥቃቶች ለመከላከል የተማረ ...
12/11/2020

✅ያውቁ ኖሯል ?

💠በአለማችን ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወደ አደገኛ ሀከሮች ኪስ በህገወጥ መንገድ በ Internet አማካኝነት ገብቷል !

💠ወደ ፊትም ይህን መሰል ጥቃቶች ለመከላከል የተማረ የሰው ሀይል ያስፈልጋል፡፡

💠በተደረጉ ጥናቶች በነጮች 2021 በመረጃ ደህንነት እና ጥበቃ (Cyber Security ) ዘርፍ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ክፍት የስራ ቦታዎች ይኖራሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡

💠እና ዝግጁ ናችሁ??

❤️SHARE AND SUPPORT❤️

➖Ⓒ ➖

Address

Wolkite
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioScie Tech Zone posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EthioScie Tech Zone:

Share