02/10/2021
እናስተዋውቃችሁ። ጎግል ድራይቭ - Google Drive
ጎግል ድራይቭ ከጎግል መተግበሪያዎች አንዱ ሲሆን ፋይሎቻሁን በጎግል ሰርቨሮች ማስቀመጥና ማስተዳደር እንድትችሉ ያግዛችኋል። ይህ አገልግሎት ኮምፒዩተራችሁን በሚተካ መልኩ መረጃችሁን በሪሞት ሰርቨሮች በማስቀመጥ ከየትኛውም የኮምፑተር መሳሪያ በየትኛውም ቦታ አክሰስና ማኔጅ እንድታደርጉ የሚያስችላችሁ ሲሆን ፍይሎችን ከተለመደው ፋይል የማስተላለፍ ዘዴን በማስቀረት አንድ ጊዜ ያስቀመጣሁትን ፋይል የጎግል አካውንታችሁን ብቻ በመጠቀም ከየትኛውም መሳሪያ ማስተዳደር እንድትችሉ ያደርጋኋል። ደህንነቱ በሙሉ የሚረጋገጠው በጎግል ማኔጅመንት ስለሆነ ምንም አይነት የቫይረስና የደህንነት ችግራችንን ይቀርፋል። ኮምፒዩተራችን ቢሰረቅ፣ ቢጠፋ ፍይላችሁን ጎግል ድራይቭ ላይ ካስከመጣችሁ ፋይላችሁን ከመጥፋት ታድኑታላችሁ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ፍይሎች ላይ ብዙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በራሳቸው ኮምፒዩተር በጋራ መስራት የሚያችል አቅም ይዞ ስለመጣ የቢሮ ስራዎችን ቀልጣፋና ቀላል ያደርግልናል።
ተከታተሉን።
---
ሮሃ ቴክሾው - Roha TechShow
ሮሃ ቴክሾው የኮምፒዩተር ሳይንስ ወሬዎችና ቱቶሪያሎች ለኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያውያን። ወቅታዊ የቴክኖሎጅ መረጃዎች፤ የቴክኒካል ድጋፎችና ስልጠናዎች ይሰጡበታል። የቴክ ዶክመን.....