Ase D-sh and receiver software solution

Ase D-sh and receiver software solution Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ase D-sh and receiver software solution, Electronics Company, Ariba Minch, Arba Minch'.

📺🔧 በመልቲሜትር የTV IC ብልሽት እንዴት ይመረመራል?1️⃣ ⚡ Power (VCC) ይለኩ• መልቲሜትሩን በDC Voltage ያድርጉ።• 3.3V / 5V / 12V መደበኛ ቮልቴጅ እንዳለ ያረጋግ...
10/07/2026

📺🔧 በመልቲሜትር የTV IC ብልሽት እንዴት ይመረመራል?

1️⃣ ⚡ Power (VCC) ይለኩ
• መልቲሜትሩን በDC Voltage ያድርጉ።
• 3.3V / 5V / 12V መደበኛ ቮልቴጅ እንዳለ ያረጋግጡ።

2️⃣ 🔍 Short Circuit ይፈትሹ
• ቲቪውን ከኤሌክትሪክ ያላቅቁ።
• Continuity (🔔) ወይም Ω ላይ ይለኩ።
• 🔔 ቢፕ ወይም 0–10Ω ካሳየ ➜ ሾርት ሊኖር ይችላል።

3️⃣ 📏 Resistance ያነፃፅሩ
• ከጤናማ IC ወይም ከDatasheet ጋር ያነፃፅሩ።
• 📉 እጅግ የተለየ ውጤት ➜ IC ችግር ሊኖረው ይችላል።

4️⃣ 🌡️ ሙቀትን ይመልከቱ
• IC በፍጥነት ከሞቀ 🔥 ➜ የውስጥ Short ሊኖረው ይችላል።

⚠️ ማስታወሻ
✅ መልቲሜትር የመጀመሪያ ምርመራ ብቻ ይሰጣል።
🛠️ 100% ለማረጋገጥ Datasheet፣ Oscilloscope ወይም ጤናማ IC ጋር ማነፃፀር ይመከራል።

ለአንድ የዲሽ ባለሙያ በስልኩ ላይ ሊኖሩት የሚገቡ 4 ምርጥ እና ወሳኝ Apps አንድ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻን ስራውን ቀልጣፋ፣ ትክክለኛ እና ዘመናዊ ለማድረግ የስማርትፎን መተግበሪያዎችን (...
07/07/2026

ለአንድ የዲሽ ባለሙያ በስልኩ ላይ ሊኖሩት የሚገቡ 4 ምርጥ እና ወሳኝ Apps

አንድ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻን ስራውን ቀልጣፋ፣ ትክክለኛ እና ዘመናዊ ለማድረግ የስማርትፎን መተግበሪያዎችን (Apps) መጠቀም አስፈላጊ ነው።
​ለአንድ የዲሽ ባለሙያ በስልኩ ላይ ሊኖሩት የሚገቡ 4 ምርጥ እና ወሳኝ Apps ዝርዝር እነሆ፦

​1. Satellite Director (ወይም SatFinder AR)

​ዋና ጥቅም: የሳተላይቶችን ትክክለኛ አቅጣጫ (Azimuth) እና ከፍታ (Elevation) ለማግኘት።
ስልካችን ላይ ያለውን GPS እና ማግኔቲክ ኮምፓስ (Compass) በመጠቀም የምንፈልገው ሳተላይት (ለምሳሌ Nilesat, Yahsat, NSS 12) ያለበትን ትክክለኛ አቅጣጫ ያሳያል።

​አሰራር ሂደት : ስልካችንን ወደ ሰማይ ስናዞረው በካሜራው አማካኝነት (Augmented Reality - AR) ሳተላይቱ ያለበትን ትክክለኛ ነጥብ በስክሪኑ ላይ ያሳያል ። የዲሹን የእጅ መታጠፊያ (LNB arm) ስክሪኑ ላይ ከሚታየው ቀስት ጋር በማስተካከል ሳተላይቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል።

​2. DishPointer AR

​ዋና ጥቅም: ከፊት ለፊት የሚጋርዱ እንቅፋቶችን (ዛፎች፣ ህንፃዎች) አስቀድሞ ለመለየት።

​ዲሽ ለመግጠም ቦታ ስንመርጥ ሳተላይቱ ካለበት አቅጣጫ የሚመጣውን ሲግናል የሚጋርድ ነገር መኖር አለመኖሩን በቦታው ላይ ሆነን ለማወቅ ይጠቅማል።

​የስራ አካሄድ: የስልካችንን ካሜራ ዲሹን ልንተክልበት ባሰብነው ቦታ ላይ አድርገን ወደ ሳተላይቱ መስመር ስናዞረው፣ የሳተላይቱ የሲግናል መስመር በህንፃ ወይም በዛፍ እንደተሸፈነ በካሜራው ላይ በቀጥታ መስመር አድርጎ ያሳያል።

​ጥቅሙ: ዲሹን ሰክተህ ሲግናል ለማግኘት ከመለፋት እና ጊዜ ከመባከኑ በፊት፣ ቦታው ተስማሚ መሆን አለመኖሩን በሰከንዶች ውስጥ እንድናውቅ ይረዳናል።

​3. Bubble Level (የውሃ ልክ እና ክሊኖሜትር)

​ዋና ጥቅም: የዲሹን ቋሚ ቧንቧ (Mast) እና የማዘንበል ዲግሪ በትክክል ለማስተካከል።
​ማንኛውም የዲሽ ባለሙያ እንደሚያውቀው፣ ዲሹ የሚታሰርበት እግሮ (ፓይፕ) በጥቅሉ 90 ዲግሪ ቀጥ ያለ ካልሆነ የሳተላይት አቅጣጫን ማስተካከልና ሁሉንም ቻናሎች በአንድ ላይ ማምጣት አድካሚ ይሆናል ።

​የስራ አካሄድ: ስልካችንን የ ዲሹ እግር ብረት ላይ በማስቀመጥ እግሩ ወደ የትኛውም አቅጣጫ አለማዘንበሉን (perfectly vertical) መሆኑን በዲጂታል የውሃ ልክ ያረጋግጣል ።

​ተጨማሪ ጥቅም: የዲሹን LNB ዝንባሌ (LNB skew/tilt) እና የሳተላይቱን ከፍታ አንግል (Elevation Angle) በትክክል በዲግሪ ለመለካት ያገለግላል።

​4. G-MScreen (ወይም GTShare / STB Finder)

​ዋና ጥቅም: የሪሲቨሩን ስክሪን እና የሲግናል መለኪያ በቀጥታ ወደ ስልክ ለማስተላለፍ።
​ይህ መተግበሪያ ያለ digital finder ጣራ ላይ ወጥተን ዲሽ ለማስተካከል ።

​የስራ አካሄድ: የምንጠቀመው ሪሲቨር የዋይፋይ አንቴና የሚቀበል ከሆነ እና ይህን አገልግሎት የሚሰራ ከሆነ ፣ ከስልክህ ሆትስፖት (Hotspot) ጋር በማገናኘት የሪሲቨሩን የሲግናል መለኪያ ገጽ በቀጥታ በስልክህ ስክሪን ላይ ማየት ይቻላል ።

​ጥቅሙ: ጣራ ላይ ብቻህን ሆነህ የሲግናል ጥራቱን (Quality) በስልክህ እያየህ ዲሹን ለማስተካከል እና ቻናሎችን ለማስገባት (Scan) ያስችላል።

​ ማስታወሻ:

👉 እነዚህን መተግበሪያዎች ስትጠቀም ሁልጊዜ የስልክህ GPS (Location) መብራቱን አረጋግጥ። እንዲሁም ዲሽ አቅራቢያ ስትሆን ማግኔቲክ ሴንሰሩ በዲሹ ብረት እንዳይስተጓጎል ስል

🌩️ ⚡ መብረቅ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እንዴት ይጎዳል  መፍትሔዎች ⚡⁉️🖥️ ❎ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ለመብረቅ አደጋ ተጋላጭ የሚሆኑት መብረቅ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ቮልቴ...
13/05/2026

🌩️ ⚡ መብረቅ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እንዴት ይጎዳል መፍትሔዎች ⚡⁉️

🖥️ ❎ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ለመብረቅ አደጋ ተጋላጭ የሚሆኑት መብረቅ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ቮልቴጅ (High Voltage) በድንገት ወደ መስመሮች ስለሚለቅ ነው። ይህ ሂደት "Power Surge" ይባላል።‼️

✅ ⚡መብረቅ በቀጥታ መሣሪያውን ባይመታው እንኳ፣ በአቅራቢያው በሚገኝ የኤሌክትሪክ ምሰሶ ወይም የቴሌኮም መስመር ላይ ሲያርፍ፣ ከፍተኛ ኃይል በገመዶች በኩል ተጉዞ ቤታችን ይገባል።

1️⃣ . ⚡መብረቅ ለምን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ያጠቃል?⁉️

ℹ️ ከፍተኛ ሙቀትና ኃይል፦ መብረቅ በቢሊዮን የሚቆጠር ዋት ኃይል ስላለው፣ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ውስጥ ያሉ ጥቃቅን የኤሌክትሪክ መንገዶችን (Circuits) ወዲያውኑ ያቀልጣል ወይም ያቃጥላል።

ℹ️ ኢንዳክሽን (Induction)፦ መብረቅ በአቅራቢያው ባለ ገመድ ላይ ሲያርፍ፣ በሌሎች በአቅራቢያው ባሉ ገመዶች ላይ እንኳ ሳይነካኩ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲፈጠር ያደርጋል።

2️⃣ . በኮምፒውተርና በቲቪ ላይ የሚጎዱ ክፍሎች

↗️ መብረቅ ሲከሰት በብዛት የሚጎዱት ክፍሎች የኤሌክትሪክ ኃይል መጀመሪያ የሚያርፍባቸውና ስስ የሆኑት ናቸው፦

↗️ በኮምፒውተር ላይ፦⁉️

❎ Power Supply Unit (PSU)፦ የኤሌክትሪክ ገመዱ መጀመሪያ የሚሰካበት ክፍል ስለሆነ ከፍተኛውን ድንገተኛ ኃይል ይቀበላል።

❎ Motherboard፦ በውስጡ ያሉ ጥቃቅን ትራንዚስተሮችና ፕሮሰሰሮች ለትንሽ የቮልቴጅ ለውጥ እንኳ በጣም ስስ ስለሆኑ በቀላሉ ይቃጠላሉ።

❎ Network Card/Modem፦ በኢንተርኔት ገመድ (Ethernet) በኩል የሚመጣን መብረቅ የሚቀበለው ይህ ክፍል ነው።

↗️ በቲቪ (TV) ላይ፦⁉️

❎ Power Board፦ ቲቪው የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኝበት ዋናው ሰሌዳ ነው።

❎ Main Board (Motherboard)፦ ምስልንና ድምፅን የሚቆጣጠረው ዋናው ክፍል ነው።

❎ HDMI/Antenna Ports፦ ከአንቴና ወይም ከዲሽ ገመድ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ድንገተኛ ቮልቴጆች እነዚህን መግቢያዎች ያቃጥሏቸዋል።

3️⃣. መከላከያ መንገዶች

🟧 Surge Protector መጠቀም፦ እነዚህ መሣሪያዎች ድንገተኛ ከፍተኛ ኃይል ሲመጣ ወደ መሬት በማፍሰስ መሣሪያው እንዳይጎዳ ይረዳሉ።

🟧 ገመዶችን መንቀል፦ ዝናብና መብረቅ በሚኖርበት ጊዜ የኤሌክትሪክ፣ የዲሽ እና የኢንተርኔት ገመዶችን ከግድግዳው ነቅሎ ማቆየት አስተማማኝ መፍትሔ ነው።

🟧 Earthing (መሬት ግንኙነት)፦ የቤትዎ የኤሌክትሪክ መስመር በትክክል ወደ መሬት የሚፈስ ሽቦ (Earth wire) ያለው መሆኑን ማረጋገጥ።

በዚህ ሰዓት ለGseek ቅናሽ ሪሲቨር በጣም በሀሪፍ ዋጋ ወርቃማው LEG N24 PRO MAX PRIME ሪሲቨርየ1 አመት funcam ለOSN ለፊልም እና የልጆች መዝናኛ ቻናሎች  ለcarton ፊ...
13/03/2026

በዚህ ሰዓት ለGseek ቅናሽ ሪሲቨር በጣም በሀሪፍ ዋጋ

ወርቃማው LEG N24 PRO MAX PRIME ሪሲቨር
የ1 አመት funcam ለOSN ለፊልም እና የልጆች መዝናኛ ቻናሎች ለcarton ፊልሞች በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚሆን
የ1 አመት Apollo የተጫነበት በዚህም ሙሉ የኳስ ቻናሎችን መመልከት የሚያስችል
ከኢትዮ ሳት ጋር አብሮ የሚሠራው GS€€K መስራት የሚችል ዋጋውም ዝቅተኛ የሆነው (ማለትም የ3 ወር እስከ 900 ብር በመክፈል ሁሉንም ኳሶች መመልከት የምትችሉበት ።
Pሪሜርሊግ SHAንፒዮንስ ሊግ ላሊጋ እና ሁሉንም የአውሮፓ ሀገራት ሊግ ጨዋታዎች ያስተላልፋል

መግዛት ለምትፈልጉ መረካቶ እና በሁሉም ኤሌክትሮኒክስ መደብሮች ያገኙታል ።

ለበለጠ መረጃ

📡📡 📡📡📡📡Asee dish installation  📡📡       አድራሻ ፦👉 አርባ ምንጭ 👉 ስሌ👉 ኤልጎ👉  እና ከቅራቢያውን🔧🔧 ማንኛውም  አይነት የዲሽ ሳተላይትEthiosat Dstv, Red...
10/03/2026

📡📡 📡📡
📡📡Asee dish installation 📡📡
አድራሻ ፦
👉 አርባ ምንጭ
👉 ስሌ
👉 ኤልጎ
👉 እና ከቅራቢያውን

🔧🔧 ማንኛውም አይነት የዲሽ ሳተላይት
Ethiosat Dstv, Red channel , H24 sport ... ሊያሰሩ 🔧🔧
ከፈለጉ ከታች ባለው ቁጥር ይደውሉ👇👇
Ase👉👉 0923369289
Ase👉👉 0718893154

ቃና 11105 H 45000
06/03/2026

ቃና 11105 H 45000

Address

Ariba Minch
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ase D-sh and receiver software solution posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share