24/07/2026
በAlyah Technologies የበለጸገው የተቀናጀ የግብርና መረጃ አስተዳደር ሲስተም ወደ ስራ ሊገባ ነው!
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በጋራ ያከናወኑት የተቀናጀ የግብርና መረጃ አስተዳደር ሲስተም (Integrated Agricultural Information Management System) የመጨረሻ ግምገማ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ይህንን የክልሉን የግብርና ዘርፍ ወደ ዘመናዊ ዲጂታል አሰራር የሚያሸጋግር ግዙፍ ሲስተም እኛ Alyah Technologies በጥራት አልምተን ለማጠናቀቅ በመቻላችን እና ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ አገልግሎት አስተዋጽኦ በማድረጋችን ታላቅ ደስታና ኩራት ይሰማናል።
ሲስተሙ ዋና ዋና የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያካትታል፦
👉የገበሬዎችን መረጃ፣ የውሃና አፈር ሀብት፣ የመሬት አጠቃቀም፣ የማዳበሪያ ስርጭት እና የምርት መረጃዎችን በአንድ ቋት ያቀናጃል።
👉የዕቅድ ዝግጅትንና የሪፖርት አቀራረብን ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ዲጂታል መንገድ በመተካት የጊዜ ብክነትን ያስቀራል፤ አሰራሩንም ግልጽና ተጠያቂነት ያለው ያደርጋል።
👉በየቀበሌው የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች ከወረዳ ጋር በቅጽበት መረጃ እንዲለዋወጡ የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ (Mobile App) እና የአጭር ጽሑፍ መልእክት (SMS) ስርዓትን ያካተተ ነው።
በተሰጡ አስተያየቶች ላይ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ሲስተሙ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ይገባል።
Alyah Technologies ሀገራችንን ወደ ተሻለ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያሸጋገሩ ዘመናዊ የሶፍትዌር መፍትሔዎችን ማቅረቡን አጠናክሮ ይቀጥላል!