H_GeeZ

H_GeeZ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from H_GeeZ, Computer Company, road_ 10, Bahir Dar.

14/08/2018

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተቋማት በፋክስ መልእክቶች ሳቢያ ለመረጃ ጥቃት መጋለጣቸው ተነገረ

************************
አዲስ አበባ፤ነሃሴ 8/2010፡- ይሆናል ብለን ባልጠበቅናቸው የፋክስ ምስሎች አማካኝነት የሳይበር ወንጀለኞች የኮርፖሬት ኔትዎርኮችን ሰብረው መጋባት መቻላቸውን የዘርፉ ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡
አንደሚታወቀው አብዛኛዎቻችን የፋክስ ማሽን መጠቀም ከጀመርንበት እለት አንስቶ ፕሪንተሮችን እና የፎቶኮፒ ማሽኖችን በውስጥ የግንኙነት አማራጮች ማያያዛችን የሚታወቅ ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ ስለ ስለተከሰተው የፋክስ ማሽን ቫይረስ በላስቬጋስ እየተካሄደ ባለው ዲፍኮን የመረጃ በርባሪዎች ኮንፈረንስ ላይ ገለጻ ሰጥተዋል፡፡
በሰኣቱም ተመራማሪዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኩባንያዎች በአደጋ ውስጥ መሆናቸውን እና የፋክስ አብዛናዎቹ ኩባንያዎቸም የመረጃዎቻቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ እዚህ ግባ የሚባል ደህንነቱ የተጠበቀ የፋክስ መስመር እንደሌላቸው ጠቁመዋል፡፡
እስካሁን ባለው ሁኔታ የኤችፒ (HP) ፕሪንተር ብቻ ለሶፍትዌር ክፍተቱ መጠገኛ ሶፍትዌር ማቅረቡ ታውቋል፡፡ ቢቢሲ

08/08/2018

ሳምሰንግ ለአርተፍሻል ኢንተለጀንስ፣ለ5ጂ ኔትዎርከ እና መሰል ጉዳዮች 22 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን ገለጸ

******************************
አዲስ አበባ፤ነሃሴ 2/2010፡- የደቡብ ኮሪያው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሳምሰንግ (Samsung) በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ለአርትፍሻል ኢንተለጀንስ፣ለ5ጂ እና መሰል ቴክኖሎጂዎች 22 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ለማድረግ ማሰቡን ገለጸ፡፡
ሳምሰንግ በአርተፍሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ፣ የ5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ ለተሽከርካሪዎች የሚሆን የኤሌክትሮኒክስ አካላትን ለማቅረብ እንዲሁም የባዮ ፋርማሲውቲካል ቢዝነስ ነው ከፍተኛ የተባለ ገንዘብ መመደቡን ያሳወቀው፡፡ ምንጭ ሮይተርስ

16/10/2015

(ለአንድሮይድ ስልኮች) መሸወድ ቀረ፤፤
በተደጋጋሚ ኢንተርኔት ገብተው ሲወጡ በዛ ያለ ገንዘብ
እየተወሰደ ከተማረሩ
የሚከተለውን ያድርጉ።
ይህን ገጽ ላይክ ሼር ያድርጉና የተለያዩ አዝናኝ እና ቁምነገር ወቅታዊ
መረጃ ወዲያው ያግኙ።Abogida አቡጊዳ መረጃ.
Setting -> Connection ( Wireless
and networks)
ከሚለው ስር Data usage የሚለው ውስጥ
ስንገባ ኢንተርኔት በጣም
የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን እንደወሰዱት
መጠን ተዘርዝረው
ያገኟቸዋል። ሁሉንም አፕ በየተራ
ይክፈቷቸው። (በፎቶው
እንደሚታየው) Foreground (ከፍተው
የተጠቀሙት) እና
Background (ያለፍቃድዎ እና ሳይታዩ አፑ
በራሱ የተጠቀመው) ምን
ያህል Mega Bytes እንደሆነ
ያስቀምጠዋል።
እሱን ዝቅ አድርገው Limit background
process ከሚለው ፊት
ያለውን [ √ ] በማድረግ ይምረጡት። ይሄም
ካለ እኛ ፈቃድ አፑ
ኢንተርኔት እንዳይጠቀም መከልከል ሲሆን
ወደ ሗላ እየተመለስን
ሁሉንም Data usage ውስጥ የተዘረዘሩ
አፖች እየከፈትን መዝጋት
(Limit) ማድረግ አለብን።
* ሁሌም አዲስ አፕ በጫን ቁጥር እየገባን
መዝጋት ይኖርብናል።
* አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በታች ለሆኑ
( samsung 5830 አይነቶች)
Data usage የላቸውም፣ በዚህ ምትክ
Setting -> Accounts
and Sync ገብተን Background data
የሚለውን አለመምረጥ ።
በተጨማሪም Setting -> Privacy
የሚለውን በመክፈት Back up
my data የሚለውን እንዲሁ አለመምረጥ።
ይህ አንድሮይዳቸው ከ
4.0 በላይ ለሆኑትም ይሰራል።
ለ Huawei ስልኮች Data usage
ለመግባት፣ Setting —>
wireless & Networks -> more .. —
> Data Usage ->
Restrict background data የሚለውን
[ √ ] በማድረግ
መምረጥ
Setting -> personal ከሚለው ስር
Location access
የሚለው ውስጥ ገብተን እሱን መዝጋት።
ይሄም ስልካችን ያለንበትን
ቦታ ለማወቅ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም
ያደርጋል።
Setting -> Developer option
(About phone ከሚለው
ከፍ ብሎ ያገኙታል) የሚለውን ከፍተን ወደ
ታች ስንወርድ
Background Process limit የሚለውን
እንክፈት። ይሄ ሁሌም
ስልኩ በራሱ Standard Limit የሚለውን
ይመርጠዋል። እዚህ ላይ
No background process የሚለውን
እንምረጥ። ሁሌም ስልካችንን
አጥፍተን ካበራነው በራሱ ወደ Standard
limit ስለሚቀየር እየገባን
መቀየር ይኖርብናል። Standard Limit
ላይ ከሆነ ቢያንስ እስከ 10
አፕሊኬሽኖች ያለ እኛ ፈቃድ ኢንተርኔት ጋ
ይገናኛሉ ማለት ነው። ይሄም
ከፍተኛ ገንዘብ ይወስዳል።
Developer option የሚለውን Setting
ውስጥ ካጡት
የሚከተለውን ያድርጉ። Setting ->
About phone የሚለው ውስጥ
እንግባና Build number የሚለውን 7 ጊዜ
በፍጥነት እንካው። ከዚያ
ሲመለሱ Setting ውስጥ About Phone
ከሚለው ከፍ ብሎ
Developer option ያገኙታል።
የስልካችን ሶፍትዌር ራሱን እንዳያድስ
(update) መዝጋት።
ለዚህም Setting -> About phone
(device) -> Software
update ገብተን Auto update የሚለው
የተመረጠ ከሆነ [ √ ]
እሱን ማንሳት ወይንም አለመምረጥ።
GPS መዝጋት
ኢንተርኔት ክፍት እንዳደረግን ኢንተርኔት
የማይጠይቁ አፖችን
(ጌም) አለመጠቀም። ይሄም አፖቹ
ከአምራቻቸው ጋ በመገናኘት ፣
ማስታወቂያ እንዲመጣ በማድረግ ...
የሚጠቀሙትን ኢንተርኔት
ያስቀራል።
Play store በ Wi–fi ካልሆነ በስልካችን
ኢንተርኔት
አለመግባት።
Opera Mini የምንጠቀም ከሆነ Opera
Setting ውስጥ
Image quality የሚለውን Low
quality ማድረግ። ይሄም ኦፔራ
ፈጣን እንዲሆን እና ብዙ ገንዘብ እንዳይወስድ
ያደርጋል። (ስለ Opera
ቀጣይ ፖስት አደርጋለሁ
ሼር ማድረግዎን አይርሱ፤፤ መልካም ቀን ይሁንልዎ

14/10/2015

ሳምሰንግ እንቅልፍ የሚያስተኛ እና የእንቅልፍ ሁኔታችንን
የሚከታተል አዲስ ምርት አስተዋወቀ ሳምሰንግ “እንቅልፍ
አልወስድ አለኝ፤ ስልኬን ስነካካ እንቅልፍ ይወስደኝ ይሆን?”
በማለት ስማርት ስልኮችን ይዞ መተኛትን የሚያስቀር ቴክኖሎጂ
ይዤ መጥቻለሁ እያለ ነው። ግዙፉ የኮሪያ የቴክኖሎጂ አምራች
የሆነው ሳምሰንግ የእንቅልፍ ሁኔታችንን የሚከታተል እና እንቅልፍ
እምቢ ሲለን ለመተኛት የሚረዳን ስሊፕ ሴንስ / SleepSense/
የተባለ አዲስ ምርት አስተዋውቋል። ታዲያ ይሄ ስሊፕ ሴንስ
በምንተኛበት ጊዜ ትራሳችን ስር በመክተት እንቅልፍ ቶሎ
እንዲወስደን እና የእንቅልፋችንን ሁኔታ መከታተል ያስችለናል ነው
የተባለው። አዲሱ ስሊፕ ሴንስ በምንተኛበት ወቅት የልብ
ምታችንን፣ አተነፋፈሳችንን እና በእንቅልፍ ጊዜ የምናደርጋቸውን
እንቅስቃሴዎች ይከታተላል። ከዚህ በፊት ከስሊፕ ሴንስ ጋር
ተመሳሳይ የሆኑ ምርቶች ቢኖሩም ይሄኛውን ልዩ የሚያደርገው
ግን በምንተኛበት ጊዜ የሚከሰቱ የሰውነታችን ተግባራት
በመከታተል ምክር ይሰጣል መባሉ ነው። በተጨማሪም
የምንወዳቸውን ሰዎች የእንቅልፍ ባህሪም ለመከታተል
እንደሚያስችለን ኩባንያው አስታውቋል። ስሊፕ ሴንስ እንቅልፍ
እንደወሰደን ካረጋገጠ በኋላ በቤት ውስጥ የተከፈቱ እንደ
ቴሌቪዥን ያሉ እና ሌሎች የኤሌከትሮኒክስ እቃዎችን ይዘጋል
ሲልም ሀፊንግተን ፖስት አስነብቧል። ምርቱ በምን ያህል ዋጋ
እንደሚሸጥ እና መቼ ለገበያ እንደሚቀርብ ግን ከኩባንያው
እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

09/10/2015

64 የሳምሰንግ ጋላክሲ ሚስጥራዊ ቁጥሮች
1- * #06 # (Display IMEI number)
2- * #1234 # (Display current firmware)
3- * #* #4636 #* #* (Diagnostic and general settings
mode)
4-* #* #7780 #* #* (Factory soft reset)
or * #7780 #
5- *2767*3855 # (Factory hard reset to ROM firmware
default settings)
6- *2767*4387264636 # (To display product code)
7- * #272*imei #* (Display/change CSC code)
or * #272*HHMM #*
8- * #* #1472365 #* #* (GPS test settings)
9- * #* #197328640 #* #* (Service mode main menu)
10- * #12580*369 # (SW & HW Info)
11- * #232337 # (Bluetooth Address)
12- * #232331 # (Bluetooth Test Mode)
13- * #232338 # (WLAN MAC Address)
14- * #0228 # (ADC Reading)
16- * #32489 # (Ciphering Info)
17- * #2263 # (RF Band Selection)
18- * #9090 # (Diagnostic ConfiguratioN)
19- * #7284 # (USB I2C Mode Control)
20- * #232339 # (WLAN Test Mode)
21- * #0842 # (Vibra Motor Test Mode)
22- * #0782 # (Real Time Clock Test)
23- * #0673 # (Audio Test Mode)
24- * #0* # (General Test Mode)
25- * #872564 # (USB Logging Control)
26- * #4238378 # (GCF Configuration)
27- * #0283 # (Audio Loopback Control)
28- * #1575 # (GPS Control Menu)
29- * #3214789650 # (LBS Test Mode)
30- * #745 # (RIL Dump Menu)
31- * #03 # (NAND Flash S/N)
32- * #0589 # (Light Sensor Test Mode)
33- * #0588 # (Proximity Sensor Test Mode)
34- * #273283*255*3282* # (Data Create Menu)
35- * #34971539 # (Camera Firmware Update)
36- * #526 # (WLAN Engineering Mode)
37- * #746 # (Debug Dump Menu)
38- * #9900 # (System Dump Mode)
39- * #44336 # (Sofware Version Info)
40- * #273283*255*663282* # (Data Create SD Card)
41- * #3282*727336* # (Data Usage Status)
42- * #7594 # (Remap Shutdown to End Call TSK)
43- * #0289 # (Melody Test Mode)
44- * #2663 # (TSP / TSK firmware update)
45- * #528 # (WLAN Engineering Mode)
46- * #7412365 # (Camera Firmware Menu)
or * #* #34971539 #* #*
47- * #80 # (Unknown)
48- * #07 # (Test History)
49- * #3214789 # (GCF Mode Status)
50- * #272886 # (Auto Answer Selection)
51- * #8736364 # (OTA Update Menu)
52- * #301279 # (HSDPA/HSUPA Control Menu)
53- * #7353 # (Quick Test Menu)
54- *2767*4387264636 # (Sellout SMS / PCODE view)
55- * #7465625 # (View Phone Lock Status)
56- *7465625*782* # (Configure Network Lock NSP)
57- *7465625*27* # (Insert Network Lock Keycode NSP/
CP)
58- #7465625*27* # (Insert Content Provider Keycode)
59- #7465625*782* # (Insert Partitial Network Lock
Keycode)
60- *7465625*77* # (Insert Network Lock Keycode SP)
62- #7465625*77* # (Insert Operator Lock Keycode)
63- *7465625*638* # (Configure Network Lock MCC/
MNC)
64- #7465625*638* # (Insert Network Lock Keycode)
ላይክ,ኮሜንትና,ሼር በማድረግ ፔጃችንን ያስተዋዉቁ:
እናመሰግናለን!!!
ይመቻቹ.....

በአንድሮይድ ስልኮ facebook ለመጠቀም mobile data onሲያደርጉ ሌሎች background አፖች like google playstore, viber, whatsup እና ሌሎችም አፓች የራሳቸ...
20/09/2015

በአንድሮይድ ስልኮ facebook ለመጠቀም mobile data on
ሲያደርጉ ሌሎች background አፖች like google play
store, viber, whatsup እና ሌሎችም አፓች የራሳቸዉን
task [update, download, send report]
ሊያደርጉብን ይችላሉ…ይህም ሳንፈልግ ሳንቲማችንን
ይበላብናል…
ስለዚህ ስልካችን ላይ firewall በመጫን extra የሆነ cost
ከማዉጣት እንተርፋለን ማለት ነው።
★በመጀመሪያ ይህን ለማድረግ አንድሮይድ ስልካችን root
መደረግ
አለበት። root ማድረግ ማለት አንድሮይድ unix based የሆነ
operating system ስለሆነ በስልኩ ላይ ሙሉ የሆነ ፍቃድ
ማግኘት ማለት ነው (super user/administrator
previlage) መሆን ማለት ነው። root ማድረግ እንደ device
model እና አይነት ስለሚለያይ እራሳቹ google or
youtube ላይ የሞዴሉን አይነት በመግለፅ how to root
ብላቹ ፈልጉ።
★በመቀጠል root ካደረጋቹ በሀላ google play store ላይ
afwall+ የሚል app download በማድረግ አፑን ስትከፍቱት
permission for root access ይጠይቃቸሃል grant በሉትና
የፈለጋቹትን app ለwifi ለብቻ ለmobile data ለብቻ
መፍቀድ እና መከልከል ትችላላቹ…ከፈለጋቹም ፋየርዎሉን
disable
or enable ማድረግ ትችላላቹ
ተጨማሪ ፖስቶች 。。。
Popular Posts ...
የእግርዎ ቅርፅ የፍቅር ህይወትዎን
እንደሚገልፅ ያቃሉ?!
Views : 297 | Sep 19
ዛሬ የማሳያችሁ ያለ ምንም ስልክ ቁጥር
whatsapp እንዴት መክፈት እንደምንችል ....
Views : 391 | Sep 17
Yemaydegem Sitota (የማይደገም ስጦታ)
Ethiopian Movie
Views : 75 | Sep 18
የመዳፍ መስመርዎ ስለ ፍቅር ግንኙነት
ህይወቶ እነደሚናገር ያውቃሉ? ስለራስዎ
ይመልከቱ
Views : 21,854 | May 20
ኢትዮ ቴሌኮም በያዝነው አመት የዱቤ
የሞባይል ካርድ አገልግሎት ይጀ..........
Views : 86 | Sep 19
yegara.com first of its kind Ethiopian social
networking site to share your world. Click Here
To Get Started (ET)
Contact | TOS & Privacy Policy | መዝጊያ
CALL: +251 942 17 81 65


18/09/2015

ምንም አይነት ኬብል ወይም ኮኔክትር
ሳንጠቀም እንዴት ከ
ኮምፒውተር ወደ አንድሮይድ ስልክ ወይም ደግሞ ከ
አንድሮይድ ስልክ ወደ ኮምፒውተር
የፈለግነውን ማንኛውንም አይነት ፋይል እንዴት መላላክ
እንደምንችል ነው።
"AirDroid" ይባላል። አፕሊኬሽን ነው። ኮምፒውተሩን እና
ስልኩን ለማገናኘት
ይጠቅመናል።
step ፩፡ በመጀመሪያ ከGoogle play store ላይ
"AirDroid" ብለን search
እናደርጋለን።
step ፪: አፕሊኬሽኑን search አድርገን ካገኘነው በኃላ
Install እናደርጋለን።
step ፫: አሁን ስልካችንን ከ ኮምፒውተሩ WiFi ጋር
እናገናኛለን።
step ፬: በመቀጠል አፕሊኬሽኑን እንከፍታለን። አፕሊኬሽኑን
ስንከፍተው ባለንበት
አካባቢ ያለውን (የተገኘውን) የ WiFi ግንኙነቶችን
ያመጣልናል። ካመጣልን wifi ጋር
connect ስናደርገው የ AirDroid server ስራውን
ይጀምራል። ከዛም አፑ IP
address ያቀርብልናል።
step ፭: ኮምፒውተሩን ከ AirDroid server ጋር
ለማገና�ኘት IP addressኡን በ
ኮምፒውተሩ web browser ላይ እንሞላለን። በመቀጠል
Enterን እንጫናለን።
Step ፮: በ ኮምፒውተራችን እስክሪን ላይ የ connectionኑን
የፅሁፍ መልዕክት
እናገኛለን። "Accept" ካልነው በኃላ connect ያደርጋል።
step ፯: በ AirDroid web የፊት ገፁ ላይ የመፍቻ ሳጥን
(toolbox) እናገኛለን። ከዛም
የፋይሉን ምስል click በማለት የፈለጉትን ፎልደር ወይም
ፋይል በመምረጥ ወደ ስልካችን
መላክ
step ፰: ፋይሉን ከመረጥንለት በኃላ አፕሊኬሽኑ
የመረጥነውን ፋይል ወደ ስልካችን
ማስተላለፍ ይጀምራል።
step ፱: አሁን ሁሉም ተጠናቋል። የላክነው ፋይል ሚሞሪ
ካርድ ውስጥ ወይም ስልኩ
ውስጥ እናገኘዋለን።

15/08/2015

ስልካችን ቢበላሽ እንዴት አድርገን ስልክ
ቁጥሮቻችንን እናገኛለን ለሚለዉ ጥያቄ
ምንጊዜም ስልክ ቁጥሮቻችንን በ Backup
መያዝ አለብን
እንዴት Buckup እንያዝ?
Step By Step
1:-contact ዉስጥ መግባት
2:-በተለምዶ setting botton የሚባለዉ
Back ከማረጊያዉ ተቃራኒዉን መጫን
3:-ከዛ import/export የሚል ሲመጣ
እሱን መጫን
4:-ከዛ Export to Storage ወይም
export to SD Card ሲመጣ የሚል ሲመጣ
እሱን መጫን
በቃ በ 5 ሰከንድ ዉስጥ FileManager ላይ
Coppy አርጎ ይጨርሳል ከዛ FileManager
መክፈት
5:-Phone Storage ወይም Memory
Storage መክፈት
6:- VCard file ወይም ሌላ አይነት ስም
ይሰጠዋል በቃ Buckup ያዝን ማለት ነዉ
7:-ከፈለግን ደግሞ ወደ Computer ላይ
Coppy ማረግ ይቻላል
8:- Computer ላይ ስልክ ቁጥሮቹን ማየት
ከፈለጋችሁ Coppy ያደረግነዉን በ NotPad
በመክፈት ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ይቻላል
2:-እንዲሁም እያንዳንዱን ስልክ ቁጥር ወደ
ሌላ ስልክ መገልበጥ ሳይጠበቅብን እንዴት በ
ሰከንድ ዉስጥ ሁሉንም ስልክ ቁጥሮቻችንን
ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ አንደምንችል
1:-በመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየሁችሁ
Memory Card ላይ Coppy ማድረግ
አለብን
2:-ከዛ Contact ዉስጥ መግባት
3:-ከዛ setting botton ዉስጥ መግባት
4:-inport/ export ዉስጥ መግባት
5:-Import from Storage ማድረግ
3:-ስልክ ቁጥሮቻችንን SIM Card ሳንይዝ
እንዴት በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት
እንደምንችል፡፡
እዚህ ላይ የስልክ አድራሻዎቻችንን
በጂሜይል / Gmail / ላይ
ማሰቀመጥ ግዴታ ነዉ
የአንድሮይድ ስልካችንን ከጂሜይላችን ጋር
አገናኝተን
የምንጠቀም ከሆነ ሁሉንም የስልክ
አድራሻችንን እዛ
ላይ ማኖር ያስችለናል።
በዚህ መንገድም የስልክ አድራሻዎቻንን
እንዳይጠፉብን
ማድረግ የምንችል ሲሆን SIM Card ሳንይዝ
በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንችላለን
ድንገት ቢጠፉብን እንኳ
ከጂሜይል መልሰን ማግኘት ያስችለናል።
ለዚህም ይረዳን ዘንድ የጂሜይል አድራሻችን
ውስጥ
1:-ኢንቦክስ / inbox / ውስጥ በመግባት
አድራሻ /
2:-Contacts/ የሚለውን መጫን
3:-ከሚመጡንል ምርጫዎች ውስጥ /
Restore contacts/
የሚለውን በመጫን የስልክ አግራሻችንን
ጂሜይል ላይ
ለማኖር እንችላለን

13/08/2015

3G Internet Usage Tutorial

Manage your 3G/4G mobile internet data usage with these helpful hints.

Data usage limit
Different apps and types of usage have different data needs. Apps that stream or download video (like YouTube and Face book) will use more data than apps that don't.
To set your data usage limit use the below steps.
Data usage > mobile data > data usage cycle > limit the data as you want by dragging the pattern sign

2. Turn off automatic Updater
Do not turn on automatic updater unless you want to update software/programs

3. Turn off mobile data when using Wi-Fi
Turn off your mobile data when using free Wi-Fi spots

4. Turn off data roaming when overseas
If international roaming is switched on, your data services will continue to work while you’re overseas. If you don’t want to use data roaming while you’re overseas, use the following steps.

Android: Settings > Wireless & Networks > Mobile Networks > Press Data roaming to turn the function on or off.
IPhones: Settings > General > Network > Turn the Indicator next to Data Roaming on or off.
5. Remove unused apps from your phone
Some of your unused apps may be sending and receiving data so that delete or uninstall the application.

6. Turn off push notifications & background data for apps
You may not realize, but many apps use data even when you're not actively 'using' them. After you download an app, say no to push notifications or use of location data and you'll be keeping their background data usage to a minimum. Then you can manually switch them on when using the app.

7. Delete unsent emails; they can be a data drain
If there are unsent emails in your email outbox, they may be trying to resend themselves over and over, which can use a lot of data (especially if they have large attachments).

8. Video, music or game streaming can use data fast
When streaming or downloading video or music, choosing higher quality content means you’ll use more data. In some cases, choosing the highest quality content can use two or more times the amount of data than the lower quality options.
Making sure that the YouTube videos that you play on your mobile aren't set up to play at higher quality is also a good move to cut down the amount of mobile data that you use. To switch this feature off:

1. Open the YouTube App
2. Go to the Menu and select General
3. Un-tick High Quality on Mobile

Just be aware that high quality music streaming (256kbps) can use over 100MB per hour, and HD video can use up to 1GB in an hour!
Interactive online games can also reach to download limits when using anywhere between 10MB and 80MB an hour.

9. Background data usage
Even when you’re not doing stuff like browsing the web, sending emails or streaming videos, your phone can still be using data in the background. A few things to keep managed for include:

Auto uploads of content to Drop box, Flicker, Google Drive, etc.
Software updates
App updates
To save data, it’s good idea to turn these things off or make sure they’re set to Wi-Fi only.

10. Turn off location services
Location services allow your phone to collect info on your geographical location so that apps and other features can use that data to provide you with stuff that’s relevant e.g. the weather where you are.
As they often run in the background and keep using data, you might want to switch them off to keep your usage down.

11. Email settings
Your email app has the ability to check for new emails at different intervals. You can define how often this is (e.g. every 10 minutes or automatically as they arrive) or you can set it so you have to manually check.
To change the frequency your phone checks for emails:

Choose the type of email you use (i.e. POP3, IMAP, Exchange)
Follow the step that’s about data retrieval frequency and change the setting in your email app to the one you want. 'Manual' is the best for conserving data.
12. Hotspots and tethering
Hotspots and tethering let other devices use your phone’s mobile data connection either through Wi-Fi or a USB cable. Some connected devices such as laptops can use data highly, so make sure you’re keeping track of how much data they’re using.

14. Switch mobile data off
You’ve also got the ability to switch off mobile data anytime when you don’t want to use it. You’ll still be able to call and text using ethio SIM.

08/08/2015

የኩላሊት ጠጠርን በአስር ቀናት ዉስጥ ማስዎገድ በእለት ከእለት እንቅስቃሴያችን ቀላል ነገሮችን በቸልታ እናልፋለን:: በምጨረሻ የእነዚህ ነገሮች ድምር ከባድ የሆነ ችግር ላይ ይጥለናል:: ለምሳሌ በቂ ዉሃ አለመጠጣት ; እንቅስቃሴ አለማድረግ; የተመጣጠኑ ምግቦችን አለመጠቀም ከተዎሰነ ጊዜ በሁአላ ለከባድ ህመም ህመም

21/07/2015

ጠቃሚ ምክሮች - የ3ጂ/ 4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትዎን ለመቆጣጠር

1. የኢንተርኔት አጠቃቀምን ለመመጠን የተለያዩ መተግበሪያዎች/Applications/ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ የተለያየ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ/ይፈልጋሉ፣
ለምሳሌ ቪዲዮ የሚያጫውቱ እንደ ዩቲዩብ/youtube/ እና ፌስ ቡክ/facebook/ ያሉ መተግበሪያዎች ከሌሎች መተግበሪያዎች ይልቅ ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡ በመሆኑም ስልክዎ ላይ ጭነው የሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የሚጠቀሙትን የኢንተርኔት መጠን ለመቆጣጠር የሚከተለውን አካሄድ መተግበር ይችላሉ፡
• የሞባይል ኢንተርኔትዎን ለመመጠን፡- ሴቲንግ /Setting/ ውስጥ Data usageን ይመርጣሉ > mobile data ውስጥ > data usage cycle የሚለው ላይ > ቀስቶቹን በማንቀሳቀስ ምን ይህል መጠን ያለው ኢንተርኔት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠቀም እንደሚፈልጉ መገደብ ይችላሉ፡፡

2. በራስ መር ማዘመንን /Update/ ማጥፋት ስልክዎ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮች ወይም መተግበሪያዎች እንዲዘምኑ /Update/ ካልፈቀዱ በስተቀር በራሳቸው ጊዜ ያለፈቃድዎ እንዳይዘምኑ Update/ በማድረግ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

3. ቪዲዮዎች ሙዚቃ እና ጌም በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ መመልከት ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ
• ቪዲዮዎች እና ሙዚቃዎችን በቀጥታ ሲመለከቱ ወይም ሲያወርዱ በተለይ ደግሞ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ቪዲዮ እና ሙዚቃዎችን ከሆነ ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡
• በአንዳንድ አጋጣሚዎች ጥራት ያለው ቪዲዮ እና ሙዚቃን መምረጥ በጥራቱ ዝቅ ከሚለው ተመሳሳይ ይዘት ካለው በሁለት እጥፍ የሚልቅ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡
ለምሳሌ ሞባይልዎ ከዩቲዩብ (youtube) ቪዲዮ እና ሙዚቃን እየተመለከቱ ከሆነ ጥራቱን ዝቅ በማድረግ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ
1. ስልክዎ ላይ የዩቲዩብ መተግበሪያን ይክፈቱ
2. ሜኑ የሚለው ውስጥ ጄነራል/General/ን ይምረጡ
3. High Quality on Mobile የሚለውን ያልተመረጠ/ Un-tick/ በማድረግ የቪዲዮውን ጥራት ዝቅ ማድረግ ይችላሉ፤
• ልብ ያድርጉ ከፍተኛ ጥራት ያለው ሙዚቃ(ምስል የሌለው) በ (256kbps) የጥራት መጠን ሲጠቀሙ በሰዓት እስከ 100 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፣
• በተመሳሳይ ሁኔታ ቪዲዮ በHD ጥራት ሲመለከቱ በሰዓት እስከ 1ጂቢ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
• ጌሞችን ከኢንተርኔት በቀጥታ እየተጠቀሙ ከሆነ በሰዓት ከ10 እስከ 80 ሜ.ባ ድረስ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡

4. መተግበሪያዎች ማሳወቂያ /Notification/ እንዳይልኩ ማድረግ እና በውስጥ በኩል ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ ማገድ አንዳንድ መተግበሪያዎች እየተጠቀሙባቸው ባይሆንም በውስጥ በኩል ሳያውቁ ኢንተርኔት ሊጠቀሙ ይችላሉ፤ ለምሳሌ የተሻለ የመተግበሪያው/Applications/ ስሪት ሲኖር ራሳቸውን ሊያዘምኑ/update/ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
• ስለዚህ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ስለመተግበሪያው የተለያዩ ማሳወቂያዎች notifications/ እንዲደርስዎ ይፈልጉ እንደሆነ ሲጠየቁ መከልከል እንዲሁም አካባቢዎን ፈልጎ እንዲያገኝ ፈቃድ ሲጠየቁ ባለመፍቀድ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡
• የጫኗቸው መተግበሪያዎችን ማዘመን/አፕዴት ማድረግ/ ሆነ መጠቀም ሲፈልጉ ብቻ ራስዎ ገብተው እንዲፈቅዱ አድርገው መጫን ይችላሉ፤ በዚህ መንገድ ስልክዎ በውስጥ በኩል እርስዎ ሳይፈቅዱ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ማድረግ ይችላሉ፡፡

5. የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት አንዳንድ መተግበሪያዎች ባይጠቀሙባቸውም ስልክዎ ላይ በመጫናቸው ብቻ ኢንተርኔት ሊጠቀሙ ስለሚችሉ የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎች በማጥፋት ወይም /Uninstall/ በማድረግ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡

6. ያልተላኩ መልዕክቶችን ማጥፋት በስልክዎ ኢሜይል የሚልኩ ከሆነ እና ያልተላከ መልዕክት ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ መልዕክት ካለዎት፣ የሞባይልዎን ኢንተርኔት በሚያበሩበት ጊዜ መላክ ይፈልጉ እንደሆነ ለመጠየቅ ዝግጁ ስለሚሆኑ ኢንተርኔት ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ትላልቅ አባሪዎችን መልዕክቱ ላይ አይይዘው ከሆነ ከፍተኛ ኢንተርኔት ሊጠቀሙ ይችላሉ፤ ስለዚህ ያልተላኩ መልዕክቶች ውስጥ ያሉ መልዕክቶችን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡

7. የኢሜይል ሴቲንግ በሞባይልዎ የኢሜይል አገልግሎት የሚጠቀሙ ከሆነ በምን ያህል የጊዜ ገደብ አዳዲስ ኢሜይሎች ሲገቡ እንደሚያሳውቅዎ መወሰን ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ሁልጊዜም አዲስ ኤሜይል ሲገባ ሊሆን ይችላል፣ በየ10 ደቂቃው ወይም እርስዎ በወሰኑት ጊዜ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን ለመመጠን ይህን ሴቲንግ መቀየር ከፈለጉ፤
1. የስልክዎ 'email' ላይ የሚጠቀሙትን የኢሜይል አይነት ይምረጡ ለምሳሌ (POP3, IMAP, Exchange)
2. በመቀጠልም ቅደም ተከተሉን በመከተል፣ በምን ያህል ጊዜ አዲስ ኢሜይል መግባቱን ማሳወቅ እንዳለበት መወሰን ይችላሉ፡፡

8. የመገኛ አካባቢን አለማሳወቅ /restricting location access/ ስልክዎ የሚገኙበትን አካባቢ እንዲያውቅ ከፈቀዱ በአካባቢዎ ሊገኙ የሚችሉ መረጃዎችን ከኢንተርኔት በመሰብሰብ በቅርበት ስለሚገኙ አገልግሎቶች እና መረጃዎች ሊያቀርብልዎ ይችላል፡፡
• ለምሳሌ የሚገኙበትን አካባቢ የአየር ሁኔታ ሊያሳውቅዎ ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህ አገልግሎቶች ኢንተርኔትዎን በከፈቱበት ወቅት ሁሉ በውስጥ በኩል ኢንተርኔት ስለሚጠቀሙ ካልፈለጉት በሚከተለው ዘዴ ማጥፋት ይችላሉ፡፡ እንደ ስልክዎ አይነት በጥቂቱ ቢለያይም በአብዛኛዎ ስልኮች ላይ ሴቲንግ ውስጥ location ወይም location settingን በመምረጥ እና የመገኛ አካባቢዎ በዋይ ፋይ ብቻ እንዲገኝ በመፍቀድ፤ የኢንተርኔት አጠቃቀም መጠንዎን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡

9. ከአገር ውጪ ሲሆኑ የኢንተርኔት ሮሚንግን ማጥፋት የመጠቀሚያ ቁጥርዎን ከአገር ውጪ በሚሄዱበት ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ የሮሚንግ አገልግሎት ለማግኘት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ውል ፈጽመው ከሆነ የሞባይል ኢንተርኔትን በማጥፋት ቁጥጥር ማድረግ ይችላሉ፡ ይህን ለማድረግ የሚከተለውን ቅደም ተከተል ይተግብሩ
• የስልክዎ አንድሮይድ ሚጠቀም ከሆነ Settings ውስጥ > Wireless & Networks የሚለውን ይመርጣሉ> Mobile Networks ውስጥ በመግባት > Data Roaming የሚለውን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መገደብ ይችላሉ፡፡
• የስልክዎ አይፎን/ iPhone ከሆነ: Settings ውስጥ > General የሚለውን ይመርጣሉ ከዚያም > Network ውስጥ> Data Roaming የሚለውን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መገደብ ይችላሉ፡፡

10. ሆት ሰፖት እና ቴዘሪንግ/ Hotspots and tethering/ የስልክዎን ኔትዎርክ በሌላ መሳሪያ መጠቀም ከፈለጉ እና ስልክዎን እንደ ዋይ ፋይ ሆት ሰፖት አድርገውት ከሆነ ወይም በዩ.ኤስ.ቢ ሚጠቀሙበት ከሆነ ያገናኟቸው መሳሪያዎች ለምሳሌ ኮምፒውተር ቢሆን ከፍተኛ ኢንተርኔት ስለሚጠቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ ሌሎች ሰዎችም የእርስዎን ስልክ ኔትዎርክ እንደ ዋይፋይ ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ የምስጢር ቁጥር በማስገባት መቆጣጠር ይችላሉ፡፡

11. የሞባይል ኢንርኔትን ማጥፋት ከላይ ከተገለጹት የጥንቃቄ ነጥቦች በተጨማሪ ደግሞ ኢንተርኔት መጠቀም በማይፈልጉበት ጊዜ የሞባይልዎን የኢንተርኔት ኔትዎርክ በማጥፋት ከአላስፈላጊ የኢንተርኔት ፍጆታ ይታቀባሉ፡፡

12. ዋይ ፋይ ሲጠቀሙ የሞባይል ኢንተርኔትዎን ማጥፋት የዋይ ፋይ አገልግሎት በሚያገኙበት አጋጣሚ ሞባይል ኢተርኔትዎን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡

በሞባይሎ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ሂሳቦ በቶሎ እንዳያልቅ ማድረጊያ ዘዴሃይ ሃይ...ወዳጆቼአማን ነው? ይቺ ኢንተርኔት የሚሏት ነገርከመጣች እና የእነ Facebook, Viber ምናምን ቡዳ ከበላን ...
11/07/2015

በሞባይሎ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ሂሳቦ በቶሎ እንዳያልቅ ማድረጊያ ዘዴ

ሃይ ሃይ...ወዳጆቼ

አማን ነው? ይቺ ኢንተርኔት የሚሏት ነገርከመጣች እና የእነ Facebook, Viber ምናምን ቡዳ ከበላን ጀምሮ እኮ ስልካችን እንደ ቀዳዳ ኪስ ሳንቲም ይዛ ማቆየት ተሳናት ጎበዝ። እናማ ይሄ ነገር ከእኔ አልፎ ብዙ ወዳጆቼን ሲያስመርር ባስተዋልኩ ጊዜ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝና ጥናቴን አካሄድኩ።

አሁን ባለኝ መረጃ መሰረት ፍራንካችንን ከስልካችን ዘርፈው የሚያሸመጥጡት ዋነኛ ምክንያቶች ሁለት ናቸው፤ አንደኛው fraud call የሚሉት ነገርዬ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ background data roaming ነው። ከዚህ በመቀጠል ስለሁለቱ ምንነት እና እንዴት ችግሩን መፍታት እንደምንችል እናያለን።

Fraud call፦ ማለት በእኛ ስልክ ውስጥ ባለ ሂሳብ እኛ ሳናውቀው ሌሎች (hackers) ሲጠቀሙበት ማለት ነው። ይሄ ሂደት ብዙ ጊዜ በእኛ ሃገር የሚፈጠር ባይሆንም አንድ አንድ ጊዜ እንደሚከሰትአስተውያለሁ፤ ስልኮ በ fraud call ሲጠቃ በራሱ ጊዜ ወደማያውቁት የውጪ ስልክ ቁጥር ይደውላል ነገር ግን የተደወለውን ቁጥር call register ውስጥ ማግኘት እንዲሁም ባትሪውን ከልነቀሉት በስተቀር ጥሪው እንዲቋረጥ ማድረግ አይቻልም ስለዚህ እርሶ ሳያውቁ ስልኮን በኪሶ ወይም በቦርሳዎ ውስጥ አስቀምጠው ብሮትን ወስዶ ያለምንም መረጃ ይጠፋል ማለት ነው። fraud call የሚደወልበትን ቁጥር ለማወቅ ግድ ስልኮትን ማየት የሚችሉበትን ቦታ ማስቀመጥ ይኖርቦታል ወይንም ኢር-ፎን ሰክተው ሙዚቃው ሲቋረጥ ወዲያውኑ ስልኮ ለይ የሚታየውን ስልክ ቁጥር መመዝገብ ይኖርቦታል በመቀጠልም ወደ ቴሌ በመደወል የመዘገቡትን ቁጥር በማሳወቅ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ።ስልኮ በ fraud call መጠቃቱን እርግጠኛ ለመሆን ካርድ ከሞሉ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ያክል ምንም ጥሪ ሳያከናውኑ እና ኢንተርኔት ሳይከፍቱ በመታገስ የስልኮ ሂሳብ መጉደል አለመጉደሉን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል።

Background data፦ ይሄ በአብዛኛው/ሁሉም ማለት ይቻላል የ Android ስልክ ተጠቃሚዎች ጋር የሚስተዋል ሲሆን ብዙዎቻችን ግድ ሳንሰጠው ስልካችን ኢንተርኔት ሲከፈት automatically sync የሚያደርገው data ብዛት እኛ ከምንጠቀመው በ 7 እና 8 እጥፍ ካርዳችን እንዲቆረጥ ያደርጋል ይህንን ለማስተካከል የሚከተለውን ቀላል step በመከተል ማስተካከል ይቻላል

1. የስልኮን setting ይክፈቱ

http://www.studentethiopia.com/img/hawi/mob1__1436362495_213.55.108.112.jpg

2. በመቀጠልdata usage የሚለውን icon ይጫኑ

http://www.studentethiopia.com/img/hawi/mob2__1436362579_213.55.108.112.jpg

3. Mobile data የምትለዋን box check ያድርጉ( የስልኮን ኢንተርኔት ያብሩ)

http://www.studentethiopia.com/img/hawi/mob3__1436362620_213.55.108.112.jpg

4. እዚሁ ገፅ ላይ እያሉ ወደታች ዝቅ ያድርጉት፤ ስልኮ ኢንተርኔት የሚጠቀሙ applicationችን በቅደም ተከተል ያሳዮታል ይህ ማለት ከላይ የተቀመጠው application ብዙውን ሳንቲሞትን የሚወስደው ነው ማለት ነው።

http://www.studentethiopia.com/img/hawi/mob4__1436362748_213.55.108.112.jpg

5. እዚህ ላይ ከሚታዮት ዝርዝሮች መሃል ብዙ Mega Bite የሚጠሙትን በየተራ በመጫን እና ወደታች በመውረግ restrict background data የሚለውን box check ያድርጉ።

http://www.studentethiopia.com/img/hawi/mob5__1436362996_213.55.108.112.jpg

ብዙ ጊዜ Google play store, Instagram, Google services የመሳሰሉት applications ብዙ data ስለሚጠቀሙ restrict ማድረጉን አይዘንጉ። ነገር ግንእነ viber,2go,whatsapp የመሳሰሉትን የቻት ማድረጊያ applicationች restrict ባያደርጓቸው ይመረጣል ምክንያቱም ከሌላ ሰው የተላከሎትን ሚሴጅ applicationኑን ካልከፈቱት በቀር automatically ለእርሶ እንዳይደርስ ስለሚገታው ነው። ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካሎት ከታች ካለው ክፍት ቦታ ላይ comment ያድርጉ እኔ በአፋጣኝ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ፤ቸር ይግጠመን አመሰግናለሁ።

Address

Road_ 10
Bahir Dar
2222

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when H_GeeZ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to H_GeeZ:

Share