Jimat.tech Empowering the Next Era of Tech
(1)

💻 ​የአለም የዌብ ዲዛይነሮች እና ዴቨሎፐሮች ቀን እንኳን አደረሳችሁ! 🌐​በፈጣኑ የዲጂታል ዘመናችን፣ ዌብሳይት ከተራ መረጃ ማስቀመጫነት (Digital Brochure) ባለፈ የድርጅትዎ ዋነኛ...
01/06/2026

💻 ​የአለም የዌብ ዲዛይነሮች እና ዴቨሎፐሮች ቀን እንኳን አደረሳችሁ! 🌐
​በፈጣኑ የዲጂታል ዘመናችን፣ ዌብሳይት ከተራ መረጃ ማስቀመጫነት (Digital Brochure) ባለፈ የድርጅትዎ ዋነኛ ዲጂታል ማንነት፣ ቀዳሚ የገበያ መስኮት እና ከደንበኞችዎ ጋር የሚገናኙበት የመጨረሻው አስተማማኝ ድልድይ ነው።
​ማንኛውም ድርጅት እና ቢዝነስ በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል ከባህላዊ አሰራር ወጥቶ ጠንካራ የዲጂታል ተገኝነት (Digital Presence) መገንባት ይኖርበታል። በጥናት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ፍጹም በሆነ በተጠቃሚ ልምድ (User Experience - UX) ላይ ተመስርቶ የሚገነባ ዌብሳይት ውበት ብቻ ሳይሆን፤ የድርጅትዎን ተአማኒነት ይጨምራል፣ የገበያ ተደራሽነትን ያሰፋል፣ እንዲሁም የቢዝነስዎን እድገት ያፋጥናል።
​እኛ በ Jimat.Tech ድርጅቶች በዲጂታል ዘመኑ ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን እናቀርባለን፦
​🌐 ዘመናዊ የዌብ ዲዛይን እና ልማት (Web Design & Development): ለቢዝነስዎ ተስማሚ፣ ፈጣን እና በሁሉም ስልኮችና ኮምፒውተሮች ላይ በተስተካከለ መልኩ የሚሰሩ ዌብሳይቶች።
​📊 የተቀናጁ የ ERP እና CRM ሲስተሞች: የድርጅትዎን የዕለት ተዕለት ስራዎች፣ ሰራተኞች እና የደንበኛ አያያዝን በአንድ ማዕከል ለማስተዳደር የሚረዱ መፍትሄዎች።
​🤖 ዘመናዊ የ AI መፍትሄዎች (Smart AI Solutions): የቢዝነስዎን የስራ ፍሰት አውቶሜት በማድረግ የስራ ቅልጥፍናን የሚጨምሩ የሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ ቴክኖሎጂዎች።
​🛠️ የአይቲ ማማከር እና አስተዳደር (IT Consulting & Management): አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታ።
​የድርጅትዎን ዲጂታል ሽግግር ዛሬውኑ ከእኛ ጋር ይጀምሩ!
​🚀 የወደፊቱን ቢዝነስ ዛሬ ይገንቡ!

01/05/2026

ለተለያየ አገልግሎት የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ዌብሳይት እና ሶፍትዌሮችን በአጭር ጊዜ ሠርተን እናስረክባለን
አድራሻችን ፡ አዳማ ቀነኔሳ ህንፃ 2ኛ ፎቅ 117 ቁጥር
አሁኑኑ ይደውሉ ፡ 0949332313 ፣ 0941713979
https://www.facebook.com/share/19Hs4HM9tV/?mibextid=wwXIfr
Www.jimat.tech

ጂማት ቴክኖሎጂ ለክቡራን ደንበኞቻችንየጥምቀት በዓልን በደስታ፣ በሰላምና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተሞላ ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ይመኛል።በዚህ የበዓል ጊዜ እንደ ሁሌም በቴክኖሎጂ መፍትሄዎቻችን ንግ...
18/01/2026

ጂማት ቴክኖሎጂ ለክቡራን ደንበኞቻችን
የጥምቀት በዓልን በደስታ፣ በሰላምና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተሞላ ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ይመኛል።
በዚህ የበዓል ጊዜ እንደ ሁሌም በቴክኖሎጂ መፍትሄዎቻችን ንግድዎን እና ሐሳቦችዎን ለመደገፍ ተዘጋጅተናል።
ስለምትታመኑን ስለ መረጣችሁን እናመሰግናለን።
Jimat.Technology wishes our valued customers
a happy and refreshing Timket holiday.
As you enjoy this festive season, we remain committed to empowering your ideas and businesses through innovative technology solutions.
Thank you for trusting Jimat.Technology.
Jimat.Technology maamila keenya kabajamoo hundaan
ayyaana Timket gammachuu, boqonnaa fi yeroo gaarii akka isinitti taʼu hawwa.
Yeroo ayyaanaa kanaanis furmaata teeknooloojii ammayyaa fayyadamuun hojii fi yaada keessan deeggaruu itti fufna.
Nu amanachuun keessan galatoomaa.

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻትቦቶች በግጥም መልክ ሲጠየቁ የደህንነት ህጎችን እንደሚዘነጉ አዲስ ጥናት አመላከተ።በጣልያን የሚገኙ ተመራማሪዎች መጥፎ የሆኑ "prompts"በግጥም መልክ ቻትቦቶችን...
02/12/2025

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻትቦቶች በግጥም መልክ ሲጠየቁ የደህንነት ህጎችን እንደሚዘነጉ አዲስ ጥናት አመላከተ።

በጣልያን የሚገኙ ተመራማሪዎች መጥፎ የሆኑ "prompts"በግጥም መልክ ቻትቦቶችን በመጠየቅ የደህንነት ሁኔታዎችን ማለፍ ይቻላል ብለዋል።

በጥናቱ የጎግል፣ የኦፕንኤአይ እና የኤክስኤአይን ቻትቦቶች ጨምሮ 25 ብዙ ተጠቃማ ያላቸው ቻትቦቶች ተካተው ነበር።

በጥናቱ እነዚህ የኤአይ ሞዴሎች 62 በመቶ ለሚሆኑት በግጥም ለቀረቡ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ተገቢ ባልሆኑት ጥያቄዎች ውስጥ የጥላቻ ንግግር፣ የወሲብ፣ ራስን ስለመግደል እና መሳሪያ እንዴት እንደሚሰራ የሚሉትን በግጥም መልክ መጠየቅ ሲገኙበት የኦፕንኤአዩ GPT-5 nano ለየትኛውም መጥፎ ጥያቄ ምላሽ አለመስጠቱ በአንፃሩ የጎግሉ Gemini 2.5 pro ለሁሉም መልስ መስጠቱ ተነግሯል።

ተመራማሪዎቹ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎቹ በመደበኛ ሁኔታ ስር እና በተለመደው የቋንቋ አፃፃፍ መሰልጠናቸው በግጥም መልክ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎችን ሲጠየቁ ምላሽ እንዲሰጡ ምክንያት ሆኗል ያሉ ሲሆን ለተቋማቱ የጥናቱን ሰነድ እንዲመለከቱና እንዲያስተካክሉ መላካቸውን ገልፀዋል።

ዘገባው ከዩሮኒውስ የተገኘ ነው።

?

በቻይና መንግስት ይደገፋሉ የተባሉ የመረጃ መንታፊዎች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የታገዘ የመጀመሪያ ነው የተባለ የሳይበር ጥቃት ፈፅመዋል ተባለ።አንትሮፒክ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ተ...
16/11/2025

በቻይና መንግስት ይደገፋሉ የተባሉ የመረጃ መንታፊዎች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የታገዘ የመጀመሪያ ነው የተባለ የሳይበር ጥቃት ፈፅመዋል ተባለ።

አንትሮፒክ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ተቋም ባወጣው ሪፖርት በቻይና መንግስት የሚደገፉት የመረጃ መንታፊዎች የራሱን የ"Claude code model" በመጠቀም 30 ድርጅቶች ላይ ጥቃቱን መፈፀማቸውን አስታውቋል።

ድርጅቶቹ በዋነኝነት የቴክኖሎጂ ፣ የፋይናንስ እና የመንግስት ተቋማት ናቸው ተብሏል።

አንትሮፒክ ጥቃቱ የተወሳሰበ መሆኑን ገልፆ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሞዴሉ በራሱ ጥቃቶችን እንዲፈፅም እንደተደረገ ገልጿል።

አንትሮፒክ አክሎም ይህ ያለ ሰው ጣልቃ ገብነት የተፈፀመ የመጀመሪያው የሳይበር ጥቃት እንደሆነም አሳውቋል።

ተቋሙ የሰው ሰራሽ አስተውህሎቱ በራሱ ከ80%-90% የሚሆነውን ስራ እንደሚሰራና ሰዎች የመጨረሻ ውሳኔ ብቻ እንደሚሰጡ በመግለፅ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ እየመጣ ስላለው ተጨማሪ ስጋት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ከተሞከረው ጥቃት ጥቂቱ መሳካቱ ሲገለፅ ቻይና ከጥቃቱ ጀርባ እንደሌለች በኤምባሲዋ በኩል ገልፃለች።

ዘገባው የፎክስ ኒውስ ነው።

Simplify HR. Empower People. Boost Productivity.Managing your team shouldn’t be complicated.Jimat.Tech HR Management Sys...
09/10/2025

Simplify HR. Empower People. Boost Productivity.
Managing your team shouldn’t be complicated.
Jimat.Tech HR Management System automates everything — from recruitment to payroll, attendance, and performance tracking — all in one secure platform.

✅ Smart Employee Records
✅ Attendance & Leave Management
✅ Payroll & Salary Automation
✅ Performance Review & Reports
✅ Cloud Backup & Security

💡 Work Smarter. Lead Better. Grow Faster.

ዘመናዊ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሞዴሎች ዛሬ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በዓለም ላይ በጣም አስፈላጊ ስፍራ እየያዘ ነው። የተለያዩ ሞዴሎች በጽሑፍ፣ በምስል፣ በቪዲዮ፣ በኮድ እና በቋንቋ ...
06/10/2025

ዘመናዊ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሞዴሎች

ዛሬ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በዓለም ላይ በጣም አስፈላጊ ስፍራ እየያዘ ነው። የተለያዩ ሞዴሎች በጽሑፍ፣ በምስል፣ በቪዲዮ፣ በኮድ እና በቋንቋ ትርጉም ላይ ብዙ አገልግሎት ይሰጣሉ።

በዚህ ዘመን፣ AI (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) አዲስ መሣሪያ ብቻ አይደለም፤ የዓለም አዲስ አቅጣጫ ነው። AI አሁን ከእኛ ጋር ነው ይጠቀማል፣ ይማራል፣ ይፈጥራል።

እኛም በ Jimat.Tech የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ወደ አዲስ ደረጃ እያደረስን ነው። በአለም ላይ ከፍተኛ ተጠቃሚ ካላቸው AI ሞዴሎች መካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ቀዳሚዎቹ ናቸው፦

1. Google Gemini 🌐

በGoogle DeepMind የተሰራ ባለብዙ ሞዴል ነው።

ጽሑፍ፣ ምስል፣ ድምጽ፣ ቪዲዮ እና ሌሎች የመረጃ አይነቶችን መረዳትና ማመንጨት ከፈለጉ የተሻለው አማራጭ ነው። ታሪክ መጻፍ፣ ግጥም መፍጠር፣ ኮድ መጻፍ እና መተርጎም ይችላል።አማርኛን ጨምሮ ብዙ ቋንቋዎችን ይረዳል።

2. DeepSeek🔍

ለቋንቋ ግንዛቤና የሂሳብ ጥያቄን መፍታት ላይ ቀዳሚ ነው። ኮድ መጻፍና መተርጎም ይችላል። የጽሑፍ ጥያቄዎችን በተሻለ እይታ ይመልሳል።አማርኛን ጨምሮ ብዙ ቋንቋዎችን ይረዳል ።

3. Anthropic Claude📘

በሥነ–ምግባር የተሞሉ ቋንቋዎች ላይ የተገነባ ሞዴል ነው፣ በተለይ በሥነ–ምግባር እና በደኅንነት ይታወቃል።

ረጅም ጽሑፎችን በአጭሩ መስጠት ይችላል።በንግድ እና በደንበኞች አገልግሎት ዙሪያ በከፍተኛ ደረጃ ጠቃሚ ነው። እንዲሁም ለልጆች ይመከራል፡፡

4. ChatGPT (by OpenAI) 💡

በዓለም ዙሪያ በጣም የተለመደ እና በስፋት አግልግሎት እየሰጠ ያለ ሞዴል ነው። ጽሑፍ መልስ፣ መጣጥፎች፣ ማጠቃለያዎች እና ኮድ መፍታት ተክኖበታል። ቋንቋ መተርጎም እና አዳዲስ ሃሳብ ማፍለቅ ለርሱ ሙዝ የመላጥ ያህል ቀላል ነው።

5. Meta LLaMA 🦙

በMeta (ፌስቡክ) የተሰራ የቋንቋ ሞዴል ሲሆን በጽሑፍ ጥያቄ ላይ ትክክለኛ መልስን ይሰጣል። በአራተኛ ደረጃ በምርምር፥ በአፕሊኬሽን እና በግንባታ ላይ ብዙ ጠቃሚ ነው።

ምን ይመስሎታል?
እነዚህ ሞዴሎች በህይወታችን እየተጠቀሱ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን የሚቀላቀሉ ተስፋ ናቸው። በስራ፣ በትምህርት፣ በንግድ እና በፈጠራ መስክ ሁሉ የሚረዱ መሳሪያዎች ናቸው።

🤔 እርስዎ ከእነዚህ ውስጥ የተጠቀሙበት አለ? ልምድዎን ያካፍሉ።

ለኢሬቻ በአል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! ኢሬቻ የምስጋናና የተስፋ በዓል ነው፤ ሕዝብን በአንድነት የሚይዋህድ የባህል ብርሃን ነው። 🌊🌿እኛም በJimat.Tech ዓለም ውስጥ፣ ቴክኖሎጂን እን...
03/10/2025

ለኢሬቻ በአል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!
ኢሬቻ የምስጋናና የተስፋ በዓል ነው፤ ሕዝብን በአንድነት የሚይዋህድ የባህል ብርሃን ነው። 🌊🌿
እኛም በJimat.Tech ዓለም ውስጥ፣ ቴክኖሎጂን እንደ ብርሃን እንያለን፤
እንደ Hora Harsadee ውሃ ሕይወትን ሲሰጥ፣ ቴክኖሎጂም ዕድገትን ይሰጣል።
እንደ Oda ሰዎችን በአንድነት ሲሰበስብ፣ ቴክኖሎጂም ዓለምን ያገናኛል።
በ Bokku አስተዳደርን እንደ ምመራ ፣ ቴክኖሎጂም ዓለምን ወደ ፊት በትክክል ይመራል።
🌐 እንዲሁም የባህል ብርሃንን እና የቴክኖሎጂ አዲስነትን በአንድ የምንቀላቀልበት ዘመን ነው።
🙏 በኢሬቻ የእርስ በርስ ግንኙነት፣ ሰላምና አዲስ ተስፋ ይሞላባችሁ!

Adresse

Adama
Adama
ADAMA

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque Jimat.tech publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Contacter L'entreprise

Envoyer un message à Jimat.tech:

Partager