BMB TUBE

BMB TUBE Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from BMB TUBE, Information Technology Company, Addis Ababa.

ምስኪን ዘለንስኪ 2 የምሥራቅ አውሮፖዊቷ ዩክሬን ፕረዝደንት፤ የ47 ዓመቱ ጎልማሳ ቮሎድሚር ኡልዲሚሮቪች ዘለንስኪ የዛሬ 3 ዓመት ዘለው ከሩስያ ጋር ጦር ውስጥ የተዶሉት አይዞህ ባያቸውን ዩና...
01/03/2025

ምስኪን ዘለንስኪ 2

የምሥራቅ አውሮፖዊቷ ዩክሬን ፕረዝደንት፤ የ47 ዓመቱ ጎልማሳ ቮሎድሚር ኡልዲሚሮቪች ዘለንስኪ የዛሬ 3 ዓመት ዘለው ከሩስያ ጋር ጦር ውስጥ የተዶሉት አይዞህ ባያቸውን ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካንን ተማምነው ነው። አሜሪካም አላሳፈረቻቸውም። በቃሏ መሰረት ዩክሬንን በገንዘብ፣ በመሣሪያ፣ በሞራል ስትደግፍ ከመቆየት አልፋ የአውሮፓ ሀገራት ከዩክሬን ጎን እንዲቆሙ ብዙ ለፍታለች።

በግልፅ ዩክሬንን ወግናም በሩስያ ላይ በዋንኛነት የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስ ማዕቀብ በመጣል ከባድ ፍጥጫ ውስጥ እስከመግባት ደርሳለች።

ዕድሜ ለትራምፕ ሩስያ ዛሬ ያ ጫናዋ ተረስቶ በአሜሪካ የምትወደስ ሀገር ለመኾን በቅታለች።

በተቃራኒው ተጧሪዋ ዩክሬን ዓይንሽ ላፈር መባሏ ሳያንስ በግልፅ አሜሪካ ለጦርነቱ አውጥተዋለች የተባለው 500 ቢልየን ዶላር በዓይነት እንድትከፍል ተጠይቃለች።

ይኸ ለእነዘለንስኪ ከጦርነቱ የከበደ ዲፕሎማሲያዊ ውድቀትን ይዞ መጥቷል። ከምንም በላይ ባልገቡት ኮንትራት "ላወጣነው ገንዘብ የተፈጥሮ ሐብታችሁን (ማዕድን) ስጡን" የሚለው እጅ ጥምዘዛ የሚፋጅ እሳት ሆኖባቸዋል።

የዩክሬኑ ፕረዝደንት በዚህ ኹሉ ቀውስ ውስጥ ኾነው፣ ሳይወዱ በግድ የተፈጥሮ ሐብታቸው አሜሪካ መጠቀም እንድትችል የሚፈቅደውን ፊርማ ለማኖር 5 ሺ 300 ማይል ወይም ከ10 ሰዓት በላይ የአየር በረራ ተጉዘው ኋይት ሐወስ ተገኙ። ለፕሮቶኮል ብዙም ሳይጨነቁ ቀለል ባለ አለባበስ ትራምኘ ቢሮ የተገኙት ዘለንስኪ ከትራምፕና ምክትላቸው የገጠማቸው በኃይለቃል የታጀበ ሙግት ሰምቶ ማለፍ ተስኗቸው የመጡበትን ጉዳይ ሳይፈፅሙ ለመመለስ ተገደዋል።

ዘለንስኪ ዛሬ አሜሪካንን ተማምነው የጀመሩት ኹሉ ውሀ በልቶታል። "ጦርነት ቆስቋሽ" ከመባል አልፈው "አምባገነን" ተብለው በአደባባይ ተዘልፈዋል። በትላንቱ ውይይትም "በሚልየኖች ሕይወት የምትቆምር" ተብለዋል። የኔቶ አባል ሀገር ለመኾን የነበራቸው ተስፋና ሕልም "እንዳታስበው" በሚለው የትራምፕ ቃል እስከወዲያኛው ተቆልፏል። እኚህ ሰው ታዲያ በአሜሪካ ነገረ ድርጊት ቢበሳጩና ስሜታዊ ኾነውም ቢታዩ ይፈረድባቸዋልን?
ምስኪን ዘለንስኪ?!😘

👉

" በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ቱርካናና ዳሰነች አከባቢ በተከሰተዉ ግጭት እስካሁን 5 ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል " - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር ⚫️ " በአከባቢዉ ዛሬ ከማለዳዉ 2 ሰዓት ...
23/02/2025

" በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ቱርካናና ዳሰነች አከባቢ በተከሰተዉ ግጭት እስካሁን 5 ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል " - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር

⚫️ " በአከባቢዉ ዛሬ ከማለዳዉ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ከፍተኛ ተኩስ ነበር ! "

በጎረቤት ሀገር ኬንያ ቱርካና እና ኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች አከባቢ በአሳ ማጥመጃ ጀልባና መረብ ስርቆቶች እንደተነሳ በተገለጸ የአርብቶ አደሮች ግጭት ባለፉት ሶስት ቀናት 5 ኢትዮጵያዊያን መገደላቸውን የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ 28 ቀበሌዎች ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ጋር ድንበር የሚጋሩ ሲሆን በአከባቢዉ በሁለቱ ሀገራት አዋሳኝ ላይ ከሚገኘው የቱርካና ሀይቅ አሳ በማስገር ስራ የአከባቢው አርብቶ አደሮች በጋራ ሲጠቀሙ የቆዩ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኦሞ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ በኩል የአሳ ምርት መበራከቱንና የኬንያ አርብቶ አደሮች ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀዉ የመግባትና የአሳ ማስገሪያ መረብና ጀልባዎች (ዛተራ) የመስረቅ አዝማሚያዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

ይህን ተከትሎም ባሳለፍነዉ ሳምንት በኬንያ ቱርካና ግዛት የአከባቢው አስተዳዳሪዎች ጋር በመነጋገር መግባባት ላይ በመድረስና ከሁለቱም አከባቢ አርብቶ አደሮች ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞ በነበረበት የኬንያ አርብቶ አደሮች ከትላንት በስቲያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን በትላንትናው ዕለት ደግሞ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን መግደላቸዉን ተከትሎ የዳሰነች አርብቶ አደሮች አስከሬን ለመዉሰድና ለአፀፋ ተኩስ ከፍተዉ እንደነበር የወረዳዉ መንግስት አስታውቋል።

👉

በኢትዮጵያ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መናወጥ የምስራች ዜና ይዞ መጥቷል  የኢሮፒያን ሳተላያት መረጃ ይዞ በወጣው መሰረት ከሰሞኑን በፈንታሌ ሲከሰት የነበረው  የመሬት ርዕደት  እንደተፈራው ...
22/02/2025

በኢትዮጵያ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መናወጥ የምስራች ዜና ይዞ መጥቷል

የኢሮፒያን ሳተላያት መረጃ ይዞ በወጣው መሰረት ከሰሞኑን በፈንታሌ ሲከሰት የነበረው የመሬት ርዕደት እንደተፈራው አደጋ ሳይሆን እጅግ ባልተለመደ መልኩ ሚቴን የተሰኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ከምድር ሆድ እቃ ውስጥ ይዞ ወጥቷል ብሏል።

በሚቴን የተፈጥሮ ጋዝ ዙሪያ የሚሰራው የካናዳው ድርጅት GHGsat እንደገለፀው በፈንታሌ ተራራ በአሁን ሰዓት በ ቀን 1,400 ቶን የሚቴን ጋዝ እየወጣ ይገኛል ። ይህንንም በንፅፅር ሲያስረዳ 1,400 ቶን ጋዝ በቀን ማለት 20ሚሊየን ኪሎ ግራም የከሰል ድንጋይ ቢቃጠል የሚገኘው ሃይል እንደ ማለት ነው ብሏል ግዝፈቱን ለማስረዳት ።

በሌላ በኩል በአሁን ሰዓት በቀን እየወጣ ያለው 1400 ቶን የሚቴን ጋዝ 8000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚችል ሲሆን ይህም... ከህዳሴው ግድብ ሀይል ማመንጫ በ3ሺ ሜጋ ዋት ይልቃል ።

ይህ ብቻ ሳይሆን እንደማየነኛውም የተፈጥሮ ጋዝ ይህ አሁን ፈንታሌ በራሱ ግዜ በገዛ ፍቃዱ እነሆ በረከት ብሎ ብቅ ያለው ሚቴን በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ በአሁን ሰዓት እጅግ ተፈላጊ ወደ ሆነው LNG (Liquefied Natural gas ) ተቀይሮ ወደ 2 ሚሊየን ሊትር በቀን ማምረት ይቻላል ።

በዚህም አያበቃም ... ለግብርና ምርጥ ወሳኝ የሆነው የተፈጥሮ ማዳበሪያ ቢለወጥ ኢትዮጵያ በአለማችን ከፍተኛው ፖታሽ ሃብት ባለቤት እንደመሆኗ የኢትዮጵያን የማዳበሪያ ፍላጎት አሟልቶ በኤክስፖርት የሀብት ምንጭ የሚሆን ሀብት ነው ተብሏል።

በቀላሉ ለማስረዳት ኢትዮጵያ ሳይታሰብ የተፈጥሮ ጋዝ ምድሯን ፈንቅሎ ወጥቷልና አስፈላጊው ጥናትና በጀት ተይዞ ወደ ስራ ሊገባ ይገባል ።

ምንጭ በሜቴን ጋዝ ላይ የሚሰራው የካናዳ GHGSAT ድርጅት እንደገለጸው newscientist.com/article/246864…

👉

“ የአማራ ክልል ምሁራንና ሊህቃን በሰፊው እስር ቤት ነው ያሉት። አንድ ህዝብ ሊህቃን ታስሮበት ሊሳተፍ አይችልም ” - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) “ ጫካ ውስጥ ያሉ ሰዎች አጀንዳ አልመጣም ብዬ ...
19/02/2025

“ የአማራ ክልል ምሁራንና ሊህቃን በሰፊው እስር ቤት ነው ያሉት። አንድ ህዝብ ሊህቃን ታስሮበት ሊሳተፍ አይችልም ” - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

“ ጫካ ውስጥ ያሉ ሰዎች አጀንዳ አልመጣም ብዬ አላስብም ” - ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

| የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመታት ሪፓርት ለፓርላማ ማቅረቡ፣ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ/ም ሦስት አመቱን የሚደፍነው የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ በቋሚ ኮሚቴው ለአንድ አመት መራዘሙ ታውቋል።

ኮሚሽኑ በሪፓርቱ፣ በ10 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች የምክክር፣ የአጀንዳ ልየታ እና ለሀገራዊ ምክክር የሚሳተፉ ተወካዮች የማስመረጥ ተግባራትን እንዳጠናቀቀ አመልክቷል።

በአማራ ክልል ያለው ሥራ መቀጠሉን፣ የትግራይ ክልል ገና መሆኑም ተመላክቷል።

ሪፓርቱ በቀረበበት ወቅት የፓርላማ አባት ያነሷቸው ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ?

የኮሚሽኑ ሪፓርት ከቀረበ በኋላ አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት በተለይ የጸጥታ ችግር ያሉባቸው አካባቢዎች ለምክክሩ የገጣማቸውን የተሳትፎ ውጥንቅጥ የሚመለከቱ ጥቄዎችን ሰንዝረዋል።

አንድ የፓርላማ አባል፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ማኅበረሰቡ በንቃት ነው የተሳተፈው? ለሀገር እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ለማስቀረት ኮሚሽኑ ምን እየሰራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

ሌላኛው የፓርላማ አባል ደግሞ፣ ፓርቲዎች ከምክክሩ የወጡበት ምክንያት ምንድን ነው? አጀንዳቸውን አሁንስ በምን መልኩ ነው የሚሰጡት? በማለት ጠይቀዋል።

የታጠቁ ኃይሎችና አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምክክሩ እንዳልተሳተፉ ሲናገሩ የተደመጡት ሌላኛው የፓርላማ አባል፣ ወደ ፊት ኮሚሽኑ በዚሁ ጉዳይ ምን ለመስራት እንዳሰበ ማብራሪያ ጠይቀዋል::

👉

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን !የካቲት 12 የጣልያኑ ማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ለተደረገው የግድያ ሙከራ ጣልያን በአፀፋው የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የጨፈጨፈችበት ቀን ...
19/02/2025

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን !

የካቲት 12 የጣልያኑ ማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ለተደረገው የግድያ ሙከራ ጣልያን በአፀፋው የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የጨፈጨፈችበት ቀን ነው፡፡

በወቅቱ እስከ 30,000 ሰዎች እንደሞቱ የተገመተ ሲሆን በጊዜው የከተማዋን ነዋሪዎች 20 ከመቶ ያህል ነው ተብሏል፡፡

የጣልያኑ የጦር መሪ ግራዚያኒ በቀድሞው ቤተመንግሥት በአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ " ለኢትዮጵያ ህዝብ ስጦታ እሰጣለሁ " በሚል ዜጎቻችን ይሰበስባል።

በዝግጅቱ ላይ ኣብርሃም ደቦጭ ፣ ሞገስ ኣስግዶም ፣ ስምኦን ኣደፍርስ ፣ ስብሃት ጥሩነህ እና ሌሎች ወጣቶች ቦንብ ይዘው ወደ ስብሰባው ገቡ፡፡

በተለይ ኣብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ ኣስግዶም በኤርትራ በነበሩበት ወቅት የጣሊያን መንግሥት በኤርትራ ሕዝብ ላይ ይፈጽም የነበረውን ግፍ ያውቁ ሥለነበር ከፍተኛ ቁጭት ነበረባቸው፡፡

ወጣቶቹ ወደ አዳራሹ እንደገቡ ግራዚያኒ ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ ስለ አርበኞች እና ስለ ንጉሡ በንቀት ይናገር ነበር፡፡

ወጣቶቹ በግራዚያኒ የንቀት ንግግር እና በስብሰባው ውስጥ በታደመው ተሰብሳቢ ተናደዱ፤ ወደ ግራዚያኒ ቀስ ብለው በመጠጋት ሰባት ቦንቦችን በተከታታይ ወረወሩ፡፡

ተሰብሳቢው የመጀመሪያው የቦንብ ፍንዳታ የደስታ ርችት መስሎት ስለነበር አልተደናገጠም፡፡

በ2ተኛው የቦንብ ፍንዳታ ግራዚያኒ ተመትቶ ብዙ ቦታ ላይ ቆሰለ፣ የጦር ኃይል አዛዥ የነበረውን አውራሊያ ሊአታ አይኑ ጠፋ፤ እግሩ ተቆረጠ፡፡ ሌሎች ሹማምንትም ሕይወታቸው አለፈ።

ይህን ተከትሎ ነው ግራዚያኒ አ/አ ነዋሪዎችን በግፍ የጨፈጨፈው።

እለቱ ለ88 ጊዜ በአ/አ 6 ኪሎ በሚገኘው መታሰቢያ ሀውልት ተከብሯል።

ማጣቀሻ ፦ ኢትዮጵያና የጣልያን ጦርነት (ጳውሎስ ኞኞ)

👉

“ እናቴን በሕይወት ባጣም ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እናቶቼ ያላችሁን በማገዝ ከሞት ታደጉኝ ” - የ16 ዓመቷ የልብ ታማሚበጸጥታ ችግር ከወለጋ ተፈናቅላ በደብረ ብርሃን ቻይና መጠለያ ካምፕ ከገባ...
19/02/2025

“ እናቴን በሕይወት ባጣም ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እናቶቼ ያላችሁን በማገዝ ከሞት ታደጉኝ ” - የ16 ዓመቷ የልብ ታማሚ

በጸጥታ ችግር ከወለጋ ተፈናቅላ በደብረ ብርሃን ቻይና መጠለያ ካምፕ ከገባች አራት አመት እንዳስቆጠረች የገለጸችው የ16 ዓመት ታዳጊ ለቀዶ ጥገና ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቋ እርዳታ እንዲረግላት ተማጸነች።

በቶሎ ካልታከመች ሕይወቷ ከባድ አደጋ ላይ መሆኑን እንደተነገራት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሏን የሰጠችው ታዳጊዋ፣ ለህክምናው ወጪ 783 ሺሕ ብር እንደተጠየቀች፣ ገንዘቡን ማግኘት እንዳልቻለች አስረድታለች።

“እናቴ ሞታለች። የወለጋ ተፈናቃይ ነኝ። ሀኪም ‘የልብሽ የደም ማስተላለፊያ አብጧል’ አለኝ” ያለችው ታማሚዋ፣ በሕይወት ያሉት ቤተሰቦቿም በጸጥታው ችግር ቤት ንብረታቸውን ትተው ተፈናቃይ መሆናቸውን ተናግራለች።

እርዳታ ጠያቂዋ ታዳጊ ሀያት በላይ፣ “እናቴን በሕይወት ባጣም ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እናቶቼ ያላችሁን በማገዝ ከሞት ታደጉኝ” ስትል ተማጽናለች።

የታማሚዋ ቤተሰቦችም፣ ታዳጊ ሀያት ህመሙ ከጀመራት ሰባት አመታትን እንዳስቆጠረች፣ በቻሉት መጠን ህክምና እየተከታተለች ብትቆይም መፍትሄ ሳታገኝ እንደቆየች ገልጸው፣ ልበ ቀናዎች እንዲረዷቸው ጠይቀዋል።

መርዳት ለምትሹ፣ 1000628382895 የታማሚዋ እህት ፋጡማ አሊ ሁሴን የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው።

ደውሎ ለመጠየቅ፣ በ0945667806 ታማሚዋን፣ በ0921195123 ወንድሟን፣ 0955581772 እህቷን ፋጡማ አሊን ማግኘት ይቻላል።

👉

ልዩ ዜና ትግራይ “ በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ “ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸ...
19/02/2025

ልዩ ዜና ትግራይ

“ በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ “ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት “ ቡድን “ ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ “ መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው “ ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል።

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።
👉

ሰበር መረጃ‼️በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል ሲሉ የእስራኤል አምባሳደር ተናገሩ‼️በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ግብፅ የሰላም ስምምነቱን በእ...
18/02/2025

ሰበር መረጃ‼️
በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል ሲሉ የእስራኤል አምባሳደር ተናገሩ‼️
በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ግብፅ የሰላም ስምምነቱን በእጅጉ እየጣሰች ነው ብለዋል። በቅርቡ በግብፅ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ በዛሬው እለት ዝተዋል።

አክለው የተናገሩት በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር ግብፅ ኢንተርኔቱን እና ሶሻል ሚዲያውን በግብፅ ጦር ምስሎች አጥለቅልቃው እየተመለከትን ነው ሲሉ ከሰዋል።
በግብፅ በኩል ያልተለመደ የተባለለት ሰሞንኛ ክስተት የተስተዋለው በተለይም የግብፅ ፓራትሮፐር ብርጌዶች በኦክቶበር 7 ሐማስ ጥቅም ላይ ያዋለውን አይነት የአውሮፕላን ዝላዮች እና ኦፕሬሽኖችን ጨምሮ የተቀናጀ ነው የተባለለትን የወታደራዊ ስልጠና ልምምዶችን የሚያካሂዱበት ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት መዳረሱን ተከትሎ ነው።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉

 #ያሳፍራል😭😭 ምን አይነት ሰዎች ትሆኑ??ይህች ታዳጊ   ትባላለች!የ9ኛ ክፍል ተማሪ ናት!በጣም የምትወደው አባቷን በአንድ ቀን ህመም በድንገት በሞት ካጣች 7ወር ሆኗታል!እሮብ የካቲት5 ም...
18/02/2025

#ያሳፍራል😭😭 ምን አይነት ሰዎች ትሆኑ??

ይህች ታዳጊ ትባላለች!የ9ኛ ክፍል ተማሪ ናት!በጣም የምትወደው አባቷን በአንድ ቀን ህመም በድንገት በሞት ካጣች 7ወር ሆኗታል!

እሮብ የካቲት5 ምንም ነገር ሳትናገር ቃሊቲ አካባቢ ከሚገኘው ቤታቸው ድንገት ወጥታ ጠፍታ እናት በለቅሶና በመንከራተት ለቀናት እየፈለገቻት ትላንት እሁድ የካቲት9 በ0920751657 አንድ ስልክ ይደወልላታል:-

"ፖሊስ ነኝ፣የምደውለው ከአዳማ ነው፣ልጅሽ ከመኪና ላይ ልጆች ወርውረዋት በጣም ተጎድታለች፣ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም ፈሷል፣አሁን የምትገኘው አዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል ነው ሪፈር ወደ አዲስ አበባ ተፅፎላታል፣...." እያላት እናት ተደናግጣ በእንባ ማውራት ስላልቻለች ልጇ ሙሉቀን ስልኩን ይቀበላታል!
ምንድነው ሲላቸው?"በህይወት እንድትተርፍ በግል ትራንስፖርትም ቢሆን በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ መምጣት አለባት"ብሎ የሹፌር ስልክ ሰጣቸው፣

ሹፌር ነኝ ባዩ በ0951948455 ደውሎ በ3000ብር ተስማምቶ ፅዮን አብርሀም በሚል ቴሌብር ብሩን እንዲያስገቡ አስጠንቅቆ በመጨረሻም መንገድ እንደጀመሩና ጥቁር አንበሳ እንዲጠብቁት ነግሯቸው ወዲያውኑ ጎረቤት ወዳጅ ዘመድ ተጨማምረው እያለቀሱ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ደረሱ!!

ከደቂቃዎች በኋላ "የት ደረሳችሁ?" ለማለት ስልክ ሲደውሉ ዝግ ሆነ፣ፖሊስ የተባለው ጋርም ሲሞክሩ አይሰራም፣እንደገና ደውለው ጎማቸው እንደተበላሸና በሌላ መኪና እንዲመጡ ገንዘብ እንዲልኩላቸው ሲጠይቋቸው እያታለሏቸው ሊሆን እንደሚችል ጠረጠሩ!አዳማ ያለ ዘመድ ጋር ደውለው ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ በዕለቱ የተመዘገበ አደጋ እንደሌለና እንዲህ የምትባልም ታማሚ እንደሌለች ሰሙ!!ጉዳዩ ሿሿ እንደሆነ አወቁ‼️

አስቡት በጭንቀታችሁ ላይ ገንዘብ ለማግኘት ብለው በውሸት ፈጠራ ወሬ ሌላን ሰው ለማሳመምና ለመግደል የሚሞክሩ እንደነዚህ ያሉ ብዙ ነውረኞች አሉ! #ተጠንቀቁ🙏 ልቧ የተሰበረው እናት #ሼር በማድረግና በፀሎት ቢያንስ የጠፋችውን ልጇን በማገናኘት ወደ ሳቋ እንመልሳት🙏 እናንተ ነውረኞችም የትም አታመልጡም!
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0913151226-
0912072849

👉

ከጫካ የወጣ አንበሳ በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ  I የዳውሮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ብርሃኑ ባይከዳኝ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን እንደገለፁት በዞ...
18/02/2025

ከጫካ የወጣ አንበሳ በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

I የዳውሮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ብርሃኑ ባይከዳኝ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን እንደገለፁት በዞኑ ታርጫ ዙሪያ ወረዳ አባ ጋርጋ ቀበሌ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ሰዓት አከባቢ በድንገት ከጫካ ወደመኖሪያ መንደር የመጣዉን አንበሳ በሁለት ግለሰቦች ላይ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።

ፖሊስ ከአከባቢው አይን እማኞች እንዳረጋገጠዉ አንበሳዉን የተመለከቱ የመንደሩ ነዋሪዎች አንበሳ ወጥቷል በማለት ጩኸት እያሰሙ ድንጋይ በመወርወራቸዉ እና የጩኸቱን ድምፅ ተከትለዉ ድምፅ ወደሰሙበት አከባቢ በመምጣት ላይ የነበሩ በሁለት ሰዎች ላይ አንበሳ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።

በአንበሳዉ ጉዳት የደረሰባቸዉ ሁለቱ ተጎጂ ግለሰቦች አባ ጤና ጣቢያ ህክምና ተደርጎላቸዉ መመለሳቸዉን እና በቀጣይ መሰል የዱር እንስሳት ሲያጋጥም ከመተንኮስ በመታቀብ ራስን ከጉዳት መከላከል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በድንገት ከጫካ የወጣ አንበሳ ወደነበረበት እንዲመለስ ፖሊስ ከመንደሩ ነዋሪዎች ጋር በቅንጅት ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ አከባቢዉን ከሰዉ እንቅስቃሴ ነፃ በማድረግ አንበሳዉ ወደጫካ እንዲመለስ መደረጉን አዛዡ ጨምረዉ ተናግረዋል።

በዞኑ ጎሽና ዝሆን በተደጋጋሚ ጊዜ ወደመንደር በመዝለቅ ጉዳት ሲያደር እንደነበር የክልሉ ፖሊስ ኮምሽን የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሲያደርስ መቆየቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን በዘገባዉ አመላክቷል።
👉

የ12 አመት ታዳጊ ጠልፎ ለመሄድ የሞከረው ግለሰብ በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ተወካይ ዋና ሳ...
17/02/2025

የ12 አመት ታዳጊ ጠልፎ ለመሄድ የሞከረው ግለሰብ በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ተወካይ ዋና ሳጂን እንድሪስ ሁሴን እንደገለጹት መነሻውን ከከላላ ወረዳ መድረሻውን ደሴ ከተማ ያደረገው የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የካቲት 9/2017ዓ.ም ከጧቱ 12፡00 ስዓት ተከሳሽ ሁሴን አሊ የ12ኣመቷን ታደጊ ሀውለት ታደሰ አሰን የተባለችውን ህፃን ከመነሀሪያ ውጪ አሳፍሮ ወደ ደሴ ለመውሰድ ሲሞክር ተሳፈሪው ህብረተሰብ በሁለቱ መካከል የታየውን ልዩነት በመጠራጠር አቀስታ ከተማ ሲደርስ በከተማው ለሚንቀሳቀሱት ሰላም አስከባሪዎች ና ፖሊሶች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል፡፡

ተከሳሽ ሁሴን አሊ የከለላ ወረዳ 01 አቤት ውሃ ነዋሪ ሲሆን በከላላ ከተማ እራሱን የሀይማኖት መሪ /ሸህ/እና ደረሳ በማስመሰል ሲኖር ቆይቶ ታዳጊ ሀውለት ታደሰ አሰንን ከከላላ ወረዳ 02 ቀበሌ ቀርቀሬ ከምትባል ቦታ ፍየልና ከብት ከምትጠብቅበት የካቲት 8/2017ዓ.ም ከቀኑ11 ፡00 ከተናገርሽ አርድሻለሁ፣ እገልሻለሁ በማለት አስፈራርቶ አክስቱ ቤት በማሳደር ሊሰወር ሲሞክር መያዙን ገልጸዋል፡፡

ታዳጊዋ ጉዳት ሳይደርስባት እንድትገኝና ወንጀለኛውም በቁጥጥር ስር እንድውል ያደረገውን የአውቶቡስ ተሳፋሪ የከለላ ወረዳ ህዝብ እያመሰገን ሁሉም ህብረተሰብ ወንጀልን በማጋለጥ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንድቀጥል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ታዳጊዋን ለቤተሰቦቿና ተከሳሹን ለከላላ ወረዳ ፖሊስ እንደሚያስረክቡ ዋና ሳጂ እንደሪስ ሁሴን ገልጸዋል፡፡

የለጋምቦ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን
👉

* የፕሪቶሪያውን ስምምነት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚመለከት በአፍሪካ ሕብረት  ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄደበትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሂደትን ...
16/02/2025

* የፕሪቶሪያውን ስምምነት

የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚመለከት በአፍሪካ ሕብረት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ

በትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሂደትን በተመለከተና ከስምምነቱ "ሌሎች ምን እንማር?" በሚል ርዕስ ዛሬ የካቲት 9ቀን 2017ዓ.ም
በአፍሪካ ህብረት ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ ውይይት ላይም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ እና ሌሎች ተገኝተዋል።

የፕሪቶሪያውን ስምምነትና አፈፃፀም የተመለከተውን ሪፓርት ደግሞ ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፉኪ ማህማት፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ ኡሊሲንጎን ኦባሳንጆ እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች አቅርበዋል።

ከአንድ ሰአት በላይ የዘለቀ ውይይት ከተካሄደ በኋላ አቶ ጌታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BMB TUBE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share