Muler

Muler Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Muler, Computer repair service, A. A, Addis Ababa.

We fix all brands all problems!
# Operating system install
# Virus and Spyware Removal
# Software Installation
# Photocopy maintenance
# home and Office Network, etc...
call me @ 09-96-98-24-19/ 09-10-59-89-97

19/06/2025

Some one can help me on HP LJ Pro M404dn error code 30.09.03

Dell Vostro 15 3000 series i5 7G Condition ..used Battery...2:30hrHD.. 1TBRAM..4GBPrice 16,000 only
07/02/2024

Dell Vostro 15 3000 series i5 7G
Condition ..used
Battery...2:30hr
HD.. 1TB
RAM..4GB
Price 16,000 only

13/07/2023
28/05/2022

CARD, in collaboration with Data4Change, launches a two-week campaign on internet accessibility May 16, 2022May 16, 2022 Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD) Leave a comment The Center for the Advancement of Rights and Democracy (CARD), assisted by a successive capacity-building fel...

25/05/2022

የራንሰምዌር ጥቃት ከመቼዉም ጊዜ በላይ ማሻቀቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 17/2014: በራንሰምዌር(ransomware) አመካኝነት የሚደርሱ የመረጃ ጥቃቶች በከፍተኛ መጠን ያሻቀበ ሲሆን ቁጥሩ ባልፉት አምስት አመታት ከደረሱት አጠቃላይ ጥቃቶች በ13 በመቶ እንደሚልቅ የቬራይዘን (Verizon) ጥናት አመልክቷል።

ቬራይዘን ይፋ ባደረገዉ የ2022 የዲታ ብሪች ኢንቨስቲጌሽን ሪፖርት (Data Breach Investigations Report) መሰረት ይህ የራንሰምዌር ጥቃት መጠን በሳይበር ደህንነት ታሪክ ውስጥ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን መለየቱን ጠቁሟል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የራንሰምዌር ጥቃት መጨመር ባሻገር ከሰዉ ልጆች አጠቃቀም ስህተት ጋር በተያያዘ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶች 82 በመቶ እንደሚሽፍን የገለጸዉ ቬራይዘን ከስህተቶቹ መካከልም የሶሻል ምህንድስና ጥቃት፣ የአጠቃቀም ስህተቶች እና ያልተገባ የምህዳሩ አጠቃቀም እንደሚገኙበት አሳዉቋል።

የራንሰምዌር ጥቃት በሳይበር ጥቃት ሰለባ የሆኑ ተጎጂዎችን ፋይሎቻቸውን እና ማህደሮችን እንዳይደርሱ(access) የሚከለክል የአጥፊ ሶፍትዌር አይነት ነው። ራንሰምዌር ጥቃት የተጎጂዎችን ሰነዶች፣ ፎቶዎች፣ የመረጃ ቋቶችን እና ሌሎች ፋይሎችን የሚመሰጥር ሲሆን ተጎጅዎች የተመሰጠረባቸዉን ወሳኝ መረጃዎችን መልሰዉ ለማግኘት የራንሰም(ransom) ክፍያ የሚጠይቅ ነዉ።

ተቋማትን በተለየ ሁኔታ የሚያሳስበው አስደንጋጭ የራንሰምዌር ጥሰቶች መጨመር ነው ያለዉ ሪፖርቱ የሳይበር ወንጀለኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ የተራቀቁ የማልዌር ዓይነቶችን የመጠቀም ሁኔታ በይበልጥ በህገወጥ መንገድ የግላዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ እና ገቢ ለማግኘት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለማሳካት ራንሰምዌር ጥቃት ውጤታማ መሆኑ ተጠቁሟል።

ወደፊትም ከሰው ልጆች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የመረጃ ጥሰቶች ዋነኛ መንስኤ ሆነዉ እንደሚቀጥሉ የገለጸዉ ሪፖርቱ የተሰረቁ ማስረጃዎችን መጠቀምም ሆነ መረጃ ማጥመድ አልያም የሰዉ ልጆች በእነዚህ ጥቃቶች መከሰት የራሳቸዉ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸዉ ተገልጿል።

የተደራጁ ወንጀለኞች የሳይበር ደህንነት አለምን እንደተቆጣጠሩ የገለጸዉ ሪፖርቱ በአለም ላይ ከሚከሰቱ አምስት የመረጃ ጥሰቶች ውስጥ ቢያንስ አራቱ ከተደራጁ ወንጀሎች ጋር ይያያዛሉ ብሏል።

ከዚህ ባሻገር ከተቋም ዉጪ ያሉ የሳይበር ጥቃት ስጋቶች ውስጥ ካሉ ስጋቶች አንጻር ሲታይ የዉጭ ስጋቶች ተቋማትን የመጉዳት ዕድላቸው በአራት እጥፍ ይበልጣል ሲል በሪፖርቱ ተገልጿል።

የጂኦ-ፖለቲካ ዉጥረቶች የሳይበር ጥቃት አይነቶችን ረቂቅነት እንደጨመረዉ የገለጸዉ የቬራይዘን ሪፖርት በመንግስታት ድጋፍ ስለሚደረግባቸዉ የሳይበር ጥቃቶች ሃገራት ያላቸዉ የግንዛቤ ደረጃም በተጨባጭ ማደጉን ጠቅሷል።

በመሆኑም ወደ ዲጂታሉ አለም የምናደርገዉ ግስጋሴ በጨመረ ቁጥር ዉጤታማ የሆነ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች፣ ጠንካራ የደህንነት ማእቀፍ እና ስለጉዳዩ የሚሰጥ ተከታታይነት ያለዉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተቋማትን ደህንነታቸዉን አስጠብቀዉ እንዲቀጥሉ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል ተብሏል።

24/05/2022

የመረጃ ማከማቻ ቁሶች አስተዳደር ምንድነው?

የመረጃ ማከማቻ ቴክኖሎጂያዊ ቁሶች ወይም ዲቫይሶች ሰርቨሮችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ ስልኮችን፣ ዳታ ማከማቻና ማንቀሳቀሻ ቁሶችን፣ ካሜራዎችን፣ ከበይነመረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች (IOT) ወዘተ በግለሰብ ወይም በተቋም ደረጃ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሶችን የሚያጠቃልል ነው።

በተቋም ደረጃ በአይቲ ክፍሎች ውስጥ የሰራተኞችን ወይም የተጠቃሚዎችን ዲቫይሶች ወይም ቁሶች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ፣ ለመቆጣጠር ብሎም ለማስተዳደር የሚያስችል ፖሊሲን ለማርቀቅና ለመተግበር የቴክኖሎጂካል ዲቫይስ (ቁሶች) ማኔጅመንት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።

ተጠቃሚዎች ወይም በተቋም ውስጥ ያሉ ሰራተኞች የተለያዩ ቁሶችን ለግልም ሆነ ለስራ ጥቅም ላይ ማዋል እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ቁሶቹን ደህንነትታቸውን በማስጠበቅና ለተቋሙም የጥቃት ምንጭ፣ ተዋናይ ወይም ስጋት እንዳይሆኑ ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር እንዲሁም ሰራተኞች ስራቸውን በብቃት እንዲሰሩ ለማስቻል ከበይነመረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች ቁሶች ማኔጅመንትን በማዘመን ተግባራዊ ይደረጋል።

በተጨማሪም የቁሶችን (በኮምፒውቲንግ፣ በኔትዎርክ፣ በሞባይል እናም ቨርቹዋልንም ጨምሮ) የትግበራ፣ የክዋኔና የማዘመን ሂደቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ሂደትም ነው።

የመረጃ ማከማቻ ቁሶች ማኔጅመንት የሚከተሉትን ጉዳዩች ያጠቃልላል
የቴክኖሎጂካል ዲቫይስ(ቁሶች) ማኔጅመንትን ለማዘመን ተፈጻሚ የሚሆኑ ፖሊሲዎችን ስታንዳርዶችን እንዲሁም ህጎችንም ጨምሮ በማውጣት የቁሶችን ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና መተግበሪያዎች በማዘመን ሊተገበር ይገባል።

• ለጠቃሚዎችም አስፈላጊውን የደህንነት ነክ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሃሳቦችን በመስጠትና በሚይዟቸው ቁሶች በተለይም ለዳታ ማስተላለፊያና ማስቀመጫ እንደ ፍላሽ ዲስክ የመሳሰሉ ቁሶችን እንደ አስፈላጊነቱ በጸረ ቫይረስ ማሰስን ጨምሮ ከተንኮል አዘል መተግበሪያዎች የጸዱ መሆናቸውን ማረጋገጥን ጨምሮ ቁሶቹን እስከ ማገድም ሊደርስ የሚችል አሰራርን በመፍጠር የሚተገበር ይሆናል።

• የቴክኖሎጂካል ቁሶች (ዲቫይስ) ማኔጅመንት ለተለያዪ ቁሶች የተለያየ መመሪያና ደንብ በማውጣት ለስራና ለአሰራር ምቹ የሆነና ደህንነቱ የተጠበቀ የዲቫይሶች ትስስርን መፍጠር ያስችላል።

የመረጃ ማከማቻ ቁሶች ማኔጅመንት ምን ጥቅሞችን ያስገኛል?

• የቁሶች የእርስ በእርስ ትስስር ወይም የኔትዎርክ ግንኙነት እና በተጠቃሚዎች ላይ ባለ የስራ አይነት እና ክህሎት ክፍተት ምክንያት በሳይበር ወንጀለኞች ኢላማ እንዳይዳረጉ ያደርጋል።

• የአዉታረ መረብ ውስጥ ተሳስረው የሚገኙ ቁሶችን ደህንነታቸውን ማስጠበቅ የመረጃ ስርቆትን ለመከላከል፣ እንዲሁም የብዝበዛ ወይም የጥቃት ድርጊቶችን ለመቀነስ ወይም ለመቆጣጠር ያስችላል።

• ቁሶች ውስጥ የሚገኝን ዳታ ወይም በቁሶች በሚፈጠር ወይም በሚኖር ኔትዎርክ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ዳታን ደህንነቱ እንዲጠበቅ የዲቫይስ ማኔጅመንትን መተግበር አስፈላጊ ነው።

• በአጠቃላይ የመረጃን የሚስጥራዊነት፣ ያለመቀየር እና ተደራሽነትን ለማስጠበቅ ይረዳል።

16/05/2022

በትሮጃን ቫይረስ ተጠቂ የሆነ ኮምፒውተር የሚያሳያቸው ምልክቶች የትኞቹ ናቸዉ?

የትሮጃን (Trojan) ቫይረስ በኢ-ሜይል ወይም በሌሎች ዘዴዎች ማለትም በማህበራዊ የትስስር ገጾች ወይም ታማኝ ካልሆኑ የመተግበሪያ ክምችቶች በተጠቃሚዎች የጥንቃቄ ጉድለትና የእውቀት ክፍተት ምክንያት የሚወርዱና የሚጫኑ አጥፊ ሶፍትዌሮች ናቸው።

እንደየ ቫይረሱ አይነት ስራቸውና አላማቸው የተለያየ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ግን ጥቃት የደረሰባቸው ኮምፒውተሮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ

• የኮምፒውተር ስክሪን ከለር መቀያየርና በትክክል አለመስራት ለምሳሌ ብልጭ ድርግም ማለት፤
• የስክሪን የጀርባ ምስል ወይም የምስል ውቀሮችን መቀያየር፤
• ኮምፒውተሩ ያለትእዛዝ ዶክመንቶችን ፕሪንት ለማድረግ መሞከር፤
• ያለተጠቃሚው ትዕዛዝ የድር ጣቢያዎች(website) መክፈት፤
• የድምጽ መጠን በድንገት መለዋወጥ፤
• የጸረ-ቫይረስ ፕሮግራሞች ወይም መተግበሪያዎች ማቆም እና የዳታ መቀየር፣ መጥፋት ወይም መበላሸት፤
• የኮምፒውተሩ የሰዓት እና ቀን መለወጥ፤
• የማውስ ከርሰር (ወይም ጠቋሚ) በራሱ መንቀሳቀስና የቀኝና የግራ ጠቋሚ አሰራርና ተግባር መለዋወጥ፤
• የዊንዶውስ የስታርት ቁልፍ( በተን) መጥፋት፤
• ፖፕ አፖች (ወይም ብቅ ብቅ የሚሉ የመተግበሪያ ክፍሎች) ግልጽ ካልሆነ መልዕክት ጋር መምጣትና ተጠቃሚውን መረበሽ፤
• የኪቦርድና የማውስ ስራ ማቆም ፤
• ተጠቃሚው ግንኙነት ከሌለው አካል የኢ-ሜይል መልዕክት መምጣት ፤
• እንግዳ የሆኑ የጥያቄና የማስጠንቀቂያ የመልዕክት ሳጥኖች ከአዎንታዊና አሉታዊ አማራጮች (በሁሉም አማራጮች ተጠቃሚውን ለሌላ ጥቃት በር መክፈቻነት ጋር መምጣት፤
• ባልተለመደ መንገድ የኮምፒውተር የእንደገና መነሳት(ሪስታርቲንግ)፤
• የታስክ ማናጀር ስራ ማቆም ይህም ለአጥቂው ወይም ለትሮጃኑ ተጠቃሚው ምን ምን ፕሮሰሶች ስራ እየሰሩ እንደሆነ እንዳያውቅ ለማደረግ እና በትሮጃኑ የተጫኑ ፕሮሰሶች ራሳቸውን እንዲደብቁ ለማድረግ ያስችላል፤
• የሲስተም ፍጥነት ወይም የስራ ሂደት አቅም መገደብ ወይም መቀነስ፤
• የትክክለኛ መተግበሪያዎች ስራ ማቆም ወይም በትክክል አለመስራት እና መረበሽ፤

11/05/2022

ማይክሮሶፍት ወርሃዊ ዝመና መርሃ ግብሩ የዊንዶዉስ ምርቶች 75 የክፍተት መጠገኛዎችን አቀረበ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 3/2014: ማይክሮሶፍት በግንቦት /2022-የወርሃዊ ዝመና መርሃ ግብሩ ለዊንዶዉስ ምርቶች 75 የክፍተት መጠገኛዎችን ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ሶስቱ የዜሮ-ደይ ክፍተቶች (zero-day vulnerability) የሚዉሉ መጠገኛዎች መሆናቸዉ ታዉቋል።

በዚህ ወር መጠገኛ ከቀረበላቸዉ 75 ተጋላጭነቶች መካከል ስምንቱ የመረጃ መንታፊዎች በርቀት ሆነዉ የተጠቃሚዎችን እንቅስቃሴ መከታተል የሚያስችሉ በመሆናቸዉ የክፍተት መጠገኛዎቹ “እጅግ ወሳኝ” መጠገኛ ተብለው ተመድበዋል።

የዚህ ወር ለዊንዶዉስ ምርቶች ከቀረቡ መጠገኛዎች መካከል ለሶስት የዜሮ-ቀን ተጋላጭነቶች መጠገኛዎች እንደሚገኙበት ያሳወቀዉ ማይክሮሶፍት ከእነዚህ መካከል አንደኛው በንቃት ጥቅም ላይ የዋለ እና ሌሎቹ በይፋ የታወቁ ክፍተቶች መሆናቸዉን ጠቁሟል።

ማይክሮሶፍት አንድ ተጋላጭነት በይፋ የተገለጸ ወይም ምንም አይነት ይፋዊ የክፍተት መጠገኛ ከሌለውና ክፍተቱ ለመረጃ በርባሪዎች ጥቅም ላይ እንደ ዜሮ-ደይ ክፍተት በማለት ይመድባል።

የቀረቡትን የጥቃት ተጋላጭነት ለመድፈን የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች በመተግበር ብቻ የማይክሮሶፍት ምርቶችን ማዘመን እንችላለን። በመጀመሪያ “stat” የሚለዉን መምረጥ በመቀጠል ከቀረቡ አማራጮች መካከል “setting” የሚለዉን መምረጥ ከዚያ “update and security” በመጫን በመጨረሻ “Check for update” የሚለዉን በመምረጥ ማዘመኛዉን መተግበር ይቻላል።

በመሆኑም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተጠቃሚዎች እነዚህን ለጥቃት አጋላጭ ክፍተቶችን ለመድፈን ሳያመነቱ በማይክሮሶፍት የቀረቡትን የደህንነት ዝመናዎች በተቻለ ፍጥነት መተግበርን በጥብቅ ይመክራል።

03/05/2022

የሲስተም የማዋቀር ስህተቶች እንዴት ይፈጠራሉ? ማዋቀር ስህተት ራሱ ምንድን ነዉ?

አልሚዎች ወይም የሲስተም አምራቾች አንድን ሲስተም ወይም መሳሪያ ለአጠቃቀም ምቹ፣ተጠቃሚ ተኮርና ሁሉን አቀፍ (flexible) እንዲሆን በማሰብ በሚያመርቱበት ወቅት የአወቃቀር ስርዓት ህጎችን መመሪያዎችን እና ደረጃዎችን በማደራጀትና በማዘጋጀት ያስቀምጣሉ።

በዚህ የአሰራር ሂደትም ነባሪ (default) ለሙከራ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ ለማዋል የሚያገለግሉ የአካውንት መለያዎች፣ መዋቅሮች ቅንብሮች ጋር ሲስተሙ ወይም መሳሪያው ወደ ገበያ ወይም ወደ ተጠቃሚዎች ይወጣል።

እነዚህ መተግበሪያዎች ወይም መሳሪያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ ለማዋል በሚደረግበት ወቅት ትክክለኛ የአሰራር ሂደትን በውል ባለመረዳት ወይም ባለመገንዘብ እና ባለማወቅ የሲስተሙ ክፍሎች የሚጠበቅባቸውን የአወቃቀር ስርዓት ባለመከተል ወይም ተግባራዊ ባለማድረግ ወይም በስህተት የአወቃቀር ሂደቱን ለመተግበር በሚደረግበት ወቅት የማዋቀር ስህተት (Configuration Mistakes) ይፈጠራል።

የማዋቀር ስህተት (Configuration Mistakes) እንዴት ሊከሰት ይችላል?
የሲስተሞች የማዋቀር ስህተት (misconfiguration) በጣም ብዙ በሆኑ ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን በዋናነት በሚከተሉት ጉዳዩች ይከሰታል፦

• የአንድ ሲስተም ወይም መሳሪያ የታወቁ የአወቃቀር ስህተቶችን ባለመድፈን፤

• ነባሪ የአካውንት መለያዎችን ባለመቀየር

• የማያስፈልጉ የሲስተም ክፍሎችን ስርዓቶችን መጫንና ጥቅም ላይ ባለማዋል

• ትክክለኛ ያልሆነ ችግር መፍቻ (error handling) ወይም ቁጥጥር ባለመተግበር

• ወደ አዲስ የሲስተም ደረጃ (new version) ለማሳደግ ወይም ለመለወጥ
በሚደረግበት ወቅት ለአዲሱ ቨርዥን የሚሆኑ የታደሱና የዘመኑ የደህንነት መቆጣጠሪያ ዘዴዎችንም ባለመተግበር ወይም የነበሩትንም በማጥፋት፤

• እንደ ሲስተሙ የስራ ከባቢ ሁኔታ ወይም እንደ አሰራር ሂደቱ የማያስፈልጉ ፖርቶችን፣ ቅንብሮችን፣ ሰርቪሶችን፣ ገጾችን፣ ፋይሎችንና አቃፊዎችን፣ አካውንቶችን እንዲሁም የተጠቃሚ ፈቃዶችን ባለማጥፋት ወይም ስራ ላይ እንዲዉሉ በማድረግ

• የደህንነት መቆጣጠሪያ ቅንብሮችን (የHTTP ሄደሮችን) በትክክል ስራ ላይ አለመተግበር ወይም ትክክል ያልሆነ ግብዓት መስጠትና በተሳሳተ መንገድ ማዋቀር

02/05/2022

ኤርጎኖሚክስ (Ergonomic hazard)

ኤርጎኖሚክስ (Ergonomics) ማለት የስራ ቦታን ጤንነት፣ የስራ እንቅስቃሴን ቀልጣፍነት እና የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነት በከፍተኛ ደረጃ የሚለውጥ ጠቃሚና አስፈላጊ ሳይንስ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።

ይህም በየትኛውም የሥራ ቦታ ላይ ሊተገበር ይችላል። አንዳንድ የስራ ባህሪዎች ለረጅም ሰአታት ቢሮ ውስጥ (በአንድ ስፍራ) ተቀምጦ ማሳለፍ ሊሆን ይችላል።

የእርሶ የስራ ሁኔታ ምን አይነት ነዉ❓
እንደነዚህ አይነት የስራ ቦታዎች ከሆኑ, ergonomics መተግበር እና በየቀኑ በስራ ላይ ማዋል ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል።

የኤርጎኖሚክ አደጋዎች በጡንቻ መገጣጠሚያዎች (musculoskeletal) ሥርዓት ላይ የጉዳት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮች ናቸው።

የ Ergonomic አደጋዎች ትክክል ያልሆኑ አቀማመጦች፣ ረጅም ሰአት ተቀምጦ መስራት፣ ልክ ያልሆነ የእቃ አነሳስ፣ በከፍተኛ ፍጥነት ሰውነትን ለመዞር መሞከር እና ሌሎች በርካታ የእንቅስቃሴ ሁኔታዎች የጉዳቶቹ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።

ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በስራ ቦታቸው ላይ ለረጅም ጊዜ ተቀምጠው የሚያሳልፍ ሰዎች ቆመው ከሚውሉ ሰዎች በሁለት እጥፍ ለልብና ደም ዝውውር ስርዓት (cardiovascular) በሽታ ተጋላጭ ናቸው።

ጉዳት የሚያደርስባቸው የሰውነት ክፍሎች

• የታችኛው ጀርባ ጡንቻዎች ወይም አጥንቶች

• የአንገት ጡንቻዎች ወይም ጅማቶች

• የእጅ አንጓ ጡንቻዎች፣ መገጣጠሚያዎች ወይም ነርቮች

• በጉልበት፣ በእግር አጥንቶች እና ጡንቻዎች አካባቢ

የኤርጎኖሚክስ ችግሮች ሰራተኞችን ከመጉዳቱም በላይ በስራው ላይም ሌላ ጫና የመፍጠር እድሉ ከፍተኛ ነዉ ይኸውም በዚህ ጉዳትና ህመም ምክንያት ሰራተኞች ተደጋጋሚ ጊዜ ከስራ መቅረት፣ ከፍተኛ የህክምና ወጪ፣ የጉዳት ካሳ ክፍያ እና ስራን በተገቢው ጊዜ አለመጨረስ ድርጅቶች (መ/ቤቶች) ላይ የሚደርስ ergonomic ደህንነት አደጋዎች ናቸው።

የኤርጎኖሚክ አደጋዎች በስራ አማካይነት የጡንቻ እና ነርቭ ስርዓትን ሊጎዱ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው። እነዚህ ጉዳቶች በሰውነት ላይ በሚፈጠር ውጥረት ምክንያት የሚመጡ ሆነው ሁልጊዜም ወዲያውኑ የማይታዩ ናቸው ይህም እነዚህን አደጋዎች ወዲያው ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል።

✔ በተወሰነ ሰአት ጊዜ ውስጥ ለትንሽ ደቂቃ ሰውነትን በማዝናናት ወክ ማድረግ ቢቻል፣ ከጠረጴዛ ጀርባ ረጅም ሰአት መቀመጥ ለአንገትና ለጀርባ ህመም ወይም ለእጅ አንጓ እና ጣቶች ጉዳት (ህመም) ያስከትላል።

✔ ትክክለኛ የቢሮ ergonomics - ትክክለኛ የወንበር ቁመት፣ በቂ የመሳሪያ ክፍተት እና ጥሩ የጠረጴዛ አቀማመጥን ጨምሮ እርስዎ እና መገጣጠሚያዎችዎ በስራ ላይ ምቾት እንዲሰማዎት ሊረዳዎት ይችላል።

የስራ ቦታዎን ለማስተካከል ዝግጁ ነዎት❓ በኤርጎኖሚክ ስርዓት መሰረት የስራ ቦታዎን ምቹ ማድረግ ይጀምሩ

1. ወንበር
የአከርካሪ አጥንት መገጣጠሚያ የሚደግፍ ወንበር ይምረጡ። የወንበርዎን ቁመት ያስተካክሉ እግሮችዎ ወለሉ ላይ ወይም በእግር መቀመጫ ላይ በትክክል እንዲያርፉ እና ጭኖችዎ ከወለሉ ጋር ትይዩ እንዲሆኑ። ትከሻዎ ዘና ባለ ሁኔታ ብሎም እጆችዎ እንዲያርፉባቸው የእጅ መደገፊያዎችን ያስተካክሉ።

2. የስራ መገልገያ
መጠማዘዝን ለመቀነስ ቁልፍ፣ ስልክ፣ ስቴፕለር ወይም ሌሎች ቁሳቁሶችን ወደ ሰውነትዎ ያቅርቡ። ተቀምጠው በምቾት ሊደረስባቸው በሚችሉበት ርቀት ላይ ማንኛውንም ነገር ያስተካክሉ።

3. የፅህፈት መሳሪያዎች (computers)
መዳፍዎ በቀላሉ ለመድረስ እና ከቁልፍ ሰሌዳው (keyboard) ጋር በተመሳሳይ ርቀት ላይ ያድርጉት። በሚተይቡበት ወይም በሚፅፉበት ጊዜ የአይንዎን ርቀት ይጠብቁ፣ የእጅ አንጓዎን ቀጥ አድርገው፣ የላይኛው ክንዶችዎን ወደ ሰውነትዎ በማቅረብ፣ እና እጆችዎ ከክርንዎ ደረጃ በታች ወይም በትንሹ ዝቅ ያድርጉ።

4. ስልክ
ብዙ ጊዜ በስልክ ካወሩ እና በተመሳሳይ ጊዜ የሚተይቡ ወይም የሚጽፉ ከሆነ ስልኩን በጭንቅላትዎ እና በአንገትዎ መካከል ከማስቀመጥ ይልቅ ለስልክዎ የጆሮ ማዳመጫ (earphone) ይጠቀሙ።

5. ጠረጴዛ
ከጠረጴዛው ስር ለጉልበትዎ እና ለእግርዎ ክፍተት እንዳለ ያረጋግጡ። ጠረጴዛው በጣም ዝቅተኛ ከሆነ እና ሊስተካከል የማይችል ከሆነ ከጠረጴዛው እግሮች በታች ጠንካራ ጣውላዎችን ወይም ብሎኮችን ያስቀምጡ። ጠረጴዛው በጣም ከፍ ያለ ከሆነ እና ሊስተካከል የማይችል ከሆነ, ወንበርዎን ከፍ ያድርጉ እንደ አስፈላጊነቱ የእግር ማሳረፊያ ይጠቀሙ። ጠረጴዛዎ ጠንካራ ጠርዝ ካለው ጠርዙን ያጥፉ ወይም የእጅ አንጓ ይጠቀሙ። እቃዎችን ከጠረጴዛዎ ስር አያከማቹ።
✍🏽 የኔ ሴፍቲ ሶሊሽን‼️

27/04/2022

# Cyberegna Ethiopia Network Security Agency Security Ethiopia #የክላውድ ኮምፒውቲንግ ምንነት እንዲሁም ለሳይበር ጥቃት ያለው ተጋላጭነት እና የመከላከያ መንገዶ...

Address

A. A
Addis Ababa

Telephone

+251996982419

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Muler posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Muler:

Share