08/09/2026
የአዲሱን ዓመት ዋዜማ 15 ሚሊየን ግንኙነቶች በሚል ከሰራተኞቻችን ጋር አክብረናል።
15 ሚሊየን የ90 ቀን ቋሚ ደንበኞች ባፈራንበት ማግስት አዲሱን ዓመት በጋራ ለመቀበል በተሰባሰብንበት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ዋና ስራ አስፈፃሚያችን ዊም ቫንሔልፑት የተጠናቀቀው 2018 ዓ.ም በርካታ ስኬቶችን በጋራ ያስመዘገብንበት ዓመት ነበር ብለዋል።
ዊም በመልዕክታቸው የተጠናቀቀው ዓመት ከፍተኛ እድገት ያስመዘገብንበት፣ ተደራሽነታችን የጨመረበት፣ ድርጅታችን በከፍተኛ የሰው ሃይል ቀጣሪነት ከኢትዮጵያ አልፎ በአህጉር ደረጃ የተሸለመበት ዓመት ነበር ብለዋል።
በተጠናቀቀው ዓመት በርካታ ማህበራዊ ሃላፊነቶች ላይ መሳተፋችንን ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈፃሚያችን ለአቅመ ደካም ቤተሰቦች የጤና መድህን ዓመታዊ ክፍያ በመፈፀም፣ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብ፣ የትምህርት ቤት ምገባ ስነ-ስርዓትን በመደገፍ፣ በተፈጥሯዊ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ በማቋቋም በበርካታ ማህበራዊ ሃላፊነቶች መሳተፋችንን አስታውሰዋል።
በዚህ ሁሉ ስኬት አብረውን ለተጓዙት ውድ ደንበኞቻችን ምስጋናቸውን ያቀረቡት ዋና ስራ አስፈፃሚያችን መጭውም አዲስ ዓመት የበለጠ ደንበኞቻችንን የምናገለግልበት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።
ለእናንተ ለውድ ደንበኞቻችን በሙሉ አዲሱ ዓመት ህልማችሁን ዕውን የምታደርጉበት እንዲሆን እንመኛለን።