Kkz NBI

17/01/2023



ህክምና ሙያ ውስጥ ዓመታትን ያሳለፈችው ቦኒ ዌር (Bonny Ware) እንዲህ ትላለች፦

ብዙ ዓመታት የሞትን ፅዋ ለመጎንጨት የመጨረሻዋን ህቅታ የሚጠባበቁ በሽተኞች ጋር እሰራ ነበር፡፡ የህይወታቸውን የመጨረሻ ከሶስት እስከ አስራ ሁለት ያህል ሳምንታት አብሬያቸው እቆያለሁ፡፡ ስለፀፀታቸው አሊያም ባልሰራሁት ወይም በሰራሁት ኖሮ ስለሚሉት ጉዳይ ሲናግሩ ታዲያ ተመሳሳይ ጭብጦች ከብዙ አንደበት ይፈልቃሉ፡፡

በጣም ሲደጋገሙ ያስተዋልኳቸው አምስት ናቸው፡፡

1.ህይወቴን ሌሎች ሰዎች እንደሚጠብቋት ሳይሆን ለራሴ ሀቀኛ ሆኜ ኖሪያት ቢሆን ኖሮ

ሰዎች የኑሮ ድርሻቸው መገባደዱን ሊያውቁ እና የሆነውን ሁሉ ዞረው ሲመለከቱ በርካታ ያልተሟሉ ውጥኖች ፣ የጨነገፉ ህልሞች ፍንትው ብለው ይታዩዋቸዋል፡፡ የዚህም ምክንያቱ በይሉኝታ ታስረው ራሣቸው በፈለጉት እና በፈቀዱት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች በቀየሱላቸው መስመር መጓዛቸውን ማወቁ እያንገበገባቸው ነው ወደ መቃብራቸው የሚወርዱት፡፡

2. የማይረባ ስራ በመስራት ከመጠን በላይ ተወጣጥሬ ባልኖርኩ ኖሮ

ያስታመምኳቸው ሁሉም ወንዶች ይህ ቁጭት አለባቸው፡፡ የነፍሳቸውን ጥሪ ረስተው ህይወታቸውን በማይጠቅም እና በሚያሰለች ስራ ተጠምደው አቅማቸውን እና ጊዜያቸውን በመጨረሳቸው እንዴት ነው የሚያስቆጫቸው፡፡ እንዴትስ ነው የሚያንገበግባቸው።

3. ለራሴ ደስተኛነትን ፈቅጄለት ቢኖን ኖሮ

ይህ ደግሞ በሚገርም ሁኔታ የሚደጋገም ቁጭት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ሊሞቱ እስኪቃረቡ ድረስ ደስታ ምርጫ መሆኑን አይረዱም፡፡ በልማድ እና በድግግሞሽ ህይወት ተተብትበው የሚኖሩት፡፡ ብዙ ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፤ ይህንን ያህል ገንዘብ ሳገኝ፣ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለሁ እያሉ ለኑሮዋቸው ቀጠሮ ሲሰጡ፤ ያሰቡት እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰኑ ነው። ይህንን በውስጣቸው እውነቱን ቢረዱትም ደስተኛ ለመምሰል ብዙ ጥረት ያደርጋሉ ባይሳካላቸውም ቅሉ

4- ስሜቶቼን የመግለጽ ድፍረት ቢኖረኝ ኖሮ

አያሌ ሰዎች ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ሰላም ለመፍጠር ሲሉ ስሜታቸውን ይደብቃሉ ከዚህም የተነሳ መሆን የሚሹትን እና የሚችሉትን ሁሉ ሳይሆኑ እንዲሁ ያልፋሉ፡፡ ብዙዎቹንም ይህ ቂም እና የውስጥ እህህ ለህመም ዳርጓቸዋል፡፡

5. ከጓደኞቼ ጋር ብዙ በተገናኘሁ ኖሮ

የድሮ ጓደኛን ትክክለኛ ዋጋ ሁሉም አልጋ ላይ ሲውል ነው የሚረዳው። ሁሉንም መልሶ መፈለግና ማግኘት ያለመቻሉ ነው ክፋቱ፡፡ በርካቶቹ በራሣቸው የህይወት ውጣ ውረድ ተጠምደው የጓደኛነት ወርቃማ ፍሬ ሲረግፍ ልብ አላሉም፡፡ የሚያስፈልገውን ያህል ጊዜ ባለመስጠታቸው ፥ ጥረትም ባለማድርጋቸው የሚቆጩ ታማሚዎችን ማግኘት አያዳግትም፡፡ ሁሉም ሞት ደጅ ላይ ሲቆሙ ጓደኞቻቸውን ይናፍቃሉ፡፡

መጽሐፍ ደራሲ ፓውሎ ኮኤልሆ

📗📒📕
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
👇

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- http://shorturl.at/binrX

16/01/2023
16/01/2023
16/01/2023

ፎቶ Hilena Tafesse

16/01/2023
26/03/2022
07/07/2021

Like Kkz to get inspiring business ideas.

Address

Addis Ababa
251

Opening Hours

09:00 - 17:00

Telephone

+251919468290

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kkz posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share