23/11/2025
እጅግ ልብ የሚሰብር ዜና 😭
የሁለት ወንድማማቾች ሕይወት በመኪና አደጋ አልፏል።
1. ታላቅ ወንድም ሙዚቀኛ ይስሃቅ አብርሃም በዛሬው ዕለት ሕዳር 13/2018 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ ጉዞ ላይ እያለ በደረሰ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቱ እንዳለፈ የመረጃ ምንጮቻችን ነግረውናል።
2. የወንድሙን መሞት የሰማው የወበዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ አቤኔዘር አብርሃም በዛሬው ዕለት ህዳር 13/2018 ዓ.ም ከሚማርበት ዩኒቨርሲቲ የወንድሙን ቀብር ለመድረስ ከሆሳዕና ወደ ወላይታ ሶዶ እየተጓዘ ሳለ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ዋዕዶሌ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በደረሰው የመኪና አደጋ ህይወቱ እንዳለፈ ዩኒቨርስቲው ገልጿል።
በዚህም ሁለቱ ወንድማማቾች በአንድ ቀን በመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
የወንድማማቾቹ ድንገተኛ ሕልፈት በአርባምንጭና አካባቢው ድንጋጤን ፈጥሯል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው መፅናናትን እንመኛለን።
ምንጭ - Gamo ArbaMinch