20/12/2024
ቴክኖ ኤ አይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ ምርቶቹን አስተዋወቀ
ቴክኖ በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀውን የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን ትናንት ምሽት ማምሻውን በስካይ ላይት ሆቴል አስተዋውቋል፡፡
አዲሱ የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ ቴክኖሎጂ የዕለት ተዕለት ኑሩን በእጅጉ ከማቅለሉም በላይ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመከወን የሚያስችል አጋዥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴከኖሎጂን ተካቶለታል፡፡
መርሐግብሩን የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊክ በመከፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን በንግግራቸውም ቴክኖ ኢትዮጵያ በሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሚሽን ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚናን እየተጫወተም እንደሚገኝ እና በዚህም ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማው የገለፁ ሲሆን አከለውም ቴከኖ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እንዲሁም ማህበረሰቡ አለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመድ መትጋቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በታዋቂው የቴኖሎጂ ኤክስፐርት አቶ ሰለሞን ካሳ ስለ አዲሶቹ የፋንተም V2 የታጣፊ ስልኮች ከቴክኖ ኤ አይ ጋር አጣምረው ስለመጡት ቴከኖሎጂ በምስል የታግዘ ሰፊ ማብራሪያ ለታዳሚው የተሰጠ ሲሆን የዝግጅቱ ታዳሚዎች የቴከኖ ኤ አይ እና አዲሶቹ የፋንተም V2 ታጣፊ ስልኮችን በቅርበት የመመልከት ዕድልም እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪ ከኤ አይ ቴከኖሎጂ ጋር የተገናኙ እንደ VR ያሉ የኤይ አይ ቴከኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጌሞች ላይ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም የስልኮቹን የካሜራ ብቃት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ቀርቧል፡፡
በማስተዋወቂያ መርሐግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የቴከኖ ኢትዮጵያ ሃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
Via FastMereja.com