12/08/2018
የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ
5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች
በኮምፒዩተር ሳይንስ ሙያ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን ትክክለኛ የድረገጽ ምንጭ ማወቅ
መሰረታዊ ጉዳይ ነው። በየግዜው ዓለምን እያጥለቀለቀ ካለው አዳዲስ የቴክኖሎጂ የፈጠራ
ውጤት ጋር እራስን እኩል ለማስኬድም ሆነ ተጨማሪ ክህሎቶችን ለማግኘት ትክክለኛ
የኢንተርኔት ድረገጽ ማግኘት እጅጉን ወሳኝ ነው። ለዚህም ሲባል እነዚህን አምስት ምርጥ
የኮምፒዩተር ሳይንስ ድረገጾችን እንሆ ብለናል።
1᎐ Stanford Engineering Everywhere(SEE)
ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ሲሆን ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች
ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች
ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኤሌክትሪካል
ምህንድስና ናቸው።
2᎐ MIT Open Courseware
የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች
ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው።
ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል
ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።
3᎐ GitHub.com
GitHub በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን
ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ
ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና
እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።
4᎐ W3 Schools
ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ
የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣
CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት የሚሰጥ ይሰጣል።
በተጨማሪም በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ
የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።
5᎐ Codecademy
አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ
ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው።
በተለይ ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ
ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።
GitHub is where people build software. More than 28 million people use GitHub to discover, fork, and contribute to over 85 million projects.