Beta ICT

Beta ICT Beta ICT (ቤታ ቴክ) is a technological and Advertisment firm based on Addis Ababa, Ethiopia.

our vision is provide safe,affordable and timely solutions through technology.

🤳0953902828

Are you a graphics designer ?You should know these terms !
14/10/2025

Are you a graphics designer ?

You should know these terms !

የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ቴክኖ  በባርሴሎና በየዓመቱ በሚካሄደው MWC 2025 የቴክኖሎጂ አውደርእይ ላይ በመሳተፍ አዲሱን የAI ሲስተም የሚጠቀሙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን...
06/03/2025

የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ቴክኖ በባርሴሎና በየዓመቱ በሚካሄደው MWC 2025 የቴክኖሎጂ አውደርእይ ላይ በመሳተፍ አዲሱን የAI ሲስተም የሚጠቀሙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋውቋል።

በዚህ አመታዊ የቴክኖሎጂ ሁነት አዲሱን የTECNO AIን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም መካከል የMEGABOOK S14 የተሰኘው ላፕቶፕ አንዱ ሲሆን በዓለም እጅግ ቀላሉ እና የ14 ኢንች OLED ስክሪን ቴክኖሎጂ ያለው ነው።

የኩዋልኮም Snapdragon® X Elite ፕላትፎርም እና የTecno AI ሲስተምን በማካተት እጅግ የላቀ ፕሮሰሲንግ አቅም ያለው እንደሆነም ተገልጾዋል።

በተጨማሪም TECNO AI Glasses Pro ሌላኛው በዚህ መድረክ የተዋወቀ አዲስ ምርት ሲሆን የ50MP ካሜራ ፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን በቀጥታ ለመተርጎም የሚያስችል አቅም፣ የMicroLED AR ዲስፕሌይ እና በAI ቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ማንሳት የሚያስችል ዲጂታል መነፅር ነው።

ከዚህም ባለፈ የMEGABOOK T14 Air እና K15S ተከታታይ የላፕቶፖ ሞዴሎችን ያስተዋወቀ ሲሆን በAI ሲስተም በመታገዝ ለተጠቃሚዎች የዕለት ተዕለት ተግባራት ለማቅለል የሚያስችል እጅግ ቀልጣፋ ቴክኖሎጂን ይዟል። ቴክኖ ከ MediaTek ፣ Qualcomm እና Google Cloud የተሰኙ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የ AI ቴክኖሎጂን ለአፍሪካ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም በቴክኖሎጂ ሁነቱ ይፋ ተደርጓል።

"Stop at Nothing" በሚለው መርሁ የሚታወቀው ግዙፉ ቴክኖ የተለያዩ አዳዲስ እና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለአለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃል።

የቲክቶክ  መስራቹ የቻይና ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነ ቲክቶክን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ባይተዳንስ ኩባንያ መስራች ዛንግ ይሚንግ በቻይና ሀብታሞች ዝርዝር አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ።በቻይና...
29/10/2024

የቲክቶክ መስራቹ የቻይና ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነ

ቲክቶክን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ባይተዳንስ ኩባንያ መስራች ዛንግ ይሚንግ በቻይና ሀብታሞች ዝርዝር አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ።

በቻይና የሃብታሞች ደረጃ አውጭው ሁሩን እንዳስታወቀው ያንግ ይሚንግ በዓመታዊ የሀብታሞች ዝርዝር ሲወጣ በ49 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ሃብት በማካበት ነው በቻይና ቁጥር አንድ ሀብታም ለመሆን የቻለው።

የ41 ዓመቱ ቱጃር እ.ኤ.አ በ2021 ከባይትዳንስ ዋና ስራ አስፈጻሚነት ስልጣኑ የለቀቀ ሲሆን የአንደኝነቱን ደረጃ የታሸገ ውሃ በማምረት ዘርፍ ከተሰማራው ዦንግ ሻንሻን ተቀብሏል።

ይህን ተከትሎ ሻንሻን በ47 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በማካበት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ምንም እንኳን ባይትዳንስ በአሜሪካና በአውሮፓ ክሶችና የእገዳ ማስፈራሪያዎች ቢበረክቱበትም የባለፈው ዓመት ዓመታዊ ገቢው በ110 ቢሊዮን ዶላር (30 በመቶ) እንዳደገለት ኢኮኖሚክ ታይምስ የተባለ ድረገፅ ዘግቧል።

ለሞባይል ቀፎ መንታፊዎች መላ ተገኘላቸው!•  ጉግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አስታውቋልጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደር...
24/10/2024

ለሞባይል ቀፎ መንታፊዎች መላ ተገኘላቸው!

• ጉግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አስታውቋል

ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን ገለጸ፡፡ የስልክ ንጥቂያ ወንጀል ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት እየተስፋፋ የመጣ ወንጀል መሆኑ ይታወቃል፡፡

ጎግል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ሰዎች ስልካቸውን በስርቆት ሲያጡ፣ ለስልክ ቀፎ አምራች ድርጅት ወዲያውኑ ማመልከት የሚችሉበትን ስርዓት ዘርግቷል ተብሏል፡፡

ከዚህ በፊት ሰዎች ስልካቸውን ሲሰረቁ ቀፎው እንዳይሰራ ለማድረግ ማዘጋት የሚችሉት የይለፍ ቃላቸውን ካስታወሱ ብቻ ነበር የተባለ ሲሆን፤ አሁን ግን ስልክ ቁጥራቸውን መናገር ከቻሉ የተሰረቀው ስልክ እንዳይሰራ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መተግበሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡

ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ፤ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች የጠፋባቸውን መረጃዎች ወደ ሦስተኛ አካል ከመተላለፋቸው በፊት ያለምንም መቆራረጥ ዳግም መልሰው እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
(አል-ዐይን)

ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡

ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ፤ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች የጠፋባቸውን መረጃዎች ወደ ሦስተኛ አካል ከመተላለፋቸው በፊት ያለምንም መቆራረጥ ዳግም መልሰው እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
(አል-ዐይን)

Android rolls out theft protection features to safeguard your data before, during and after a theft incident.

💻 ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል😨?እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን🤔።✔1. Power optionStart menu ላይ ...
13/10/2022

💻 ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል😨?

እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን🤔።

✔1. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

✔2.Disable unwanted start up programs

ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

✔3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

✔4. Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

✔5. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

✔6. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

✔7. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

✔8. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ

ስማርትፎን በምንገዛበት ጊዜ ሊታሰብባቸው የሚገቡ 9 ነገሮች❗️🤔***በዚህ ዘመን ስማርት ስልኮች የሕይወታችን ዋና አካል ሆነዋል፡፡ ከወዳጆቻችን ጋር ተደዋውለን ለመገናኘት፣ ፎቶ ለማንሳት፣ ቪ...
11/08/2022

ስማርትፎን በምንገዛበት ጊዜ ሊታሰብባቸው የሚገቡ 9 ነገሮች❗️🤔
***
በዚህ ዘመን ስማርት ስልኮች የሕይወታችን ዋና አካል ሆነዋል፡፡ ከወዳጆቻችን ጋር ተደዋውለን ለመገናኘት፣ ፎቶ ለማንሳት፣ ቪዲዮ ለመቅረጽ፣ መረጃዎችን ክላውድ ላይ ለማስቀመጥ፣ ሌሎችን ስልኮች ቻርጅ ለማድረግ፣ ኢንተርኔትን ለመጎብኘት… ምን አለፋችሁ የስማርት ስልኮች አገልግሎት እጅግ በጣም ብዙ ነው፡፡



ነገር ግን በገበያ ላይ ካሉት የተለያዩ ስማርትፎኖች መካከል የትኛውን እንደሚመርጡም መወሰን ቀላል አይደለም፡፡ ስለዚህ ስማርትፎን ለመግዛት ከመወሰናችሁ በፊት የሚከተሉትን ጉዳዮች ልብ በሉ፣

1. የተሰራበት ቁስ ጥራት

ጠቅለል ተብሎ ሲታይ አንድ ስልክ በፕላስቲክ አልያም በብረት የተለበጠ ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥ አንዳንዶች ከመስታወትም እንደሚሰሩ ልብ ይሏል፡፡ ነገር ግን ለምሳሌ እርስዎ ስልክዎትን በተደጋጋሚ የሚጥሉ ከሆነ ረዥም እድሜ የሚኖረው ስልክ ያስፈልግዎታል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከፕላስቲኩም ከመስታወቱም ይልቅ በብረት የተለበጡት ስማርትፎኖች ምርጫዎት ሊያደርጉ ይገባል፡፡

2. ስክሪን(ማሳያ)

የስልኩ ስክሪን መጠንና ሪዞሊዮሽን ስልኩን ልንጠቀምበት እንደአሰብነው ጉዳይ ይለያያል፡፡ ብዙ ጊዜ በስማርት ስልክዎ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ከሆነ፣ ፎቶዎችን ወይም ቪዲዮዎችን ኤዲት የሚያደርጉ ከሆነ ወይም ፊልሞችን የሚመለከቱ ከሆነ ከ5.5 ኢንች እስከ 6 ኢንች full-HD ወይም QHD ጥራት ማሳያ ያለው የስማርትፎን ለእርስዎ ምርጡ አማራጭ ነው፡፡

3. ፕሮሰሰር

ፕሮሰሰር የስማርት ስልኮች ልብ ማለት ነው፡፡ ስልኩ ሁሉንም የሚያቀናብረው እዚህ ነው፡፡ ታዲያ በኦፕሬቲንግ ሶፍትዌር፣ በUI፣ በbloatware እና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች የተነሳ ፕሮሰሰር ከስልክ ስልክ ይለያያል፡፡

ቪዲዮ ጌም የምትጫወቱ ከሆነ፣ ቪዲዮና ፎቶዎችን እንዲሁም ዶክመንቶችን የምታቀናብሩ ከሆነ፣ አልያም ቪዲዮዎችን ከስልካችሁ ላይ የምታሰራጩ ከሆነ እና ሌሎች ከበድ ያሉ ስራዎችን የምትሰሩ ከሆነ Qualcomm Snapdragon 652 ወይም Snapdragon 820/821 ፕሮሰሰር ያሏቸው ስልኮች ያስፈልጉዎታል፡፡

4. ካሜራ

ከፍ ያለ የሜጋፒክስሎች ብዛት ብቻ የስማርትፎን ካሜራ የተሻለ አያደርገውም፡፡ እንደ የካሜራ ቀዳዳ፣ የISO ደረጃዎች፣ የፒክሰል መጠን፣ አውቶፎከስ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች አስፈላጊ ናቸው...

ባሻዬ! በዚህ ክረምት ልጆችን ጠቅላላ ዕውቀት ማስተማር ጥሩ ነው። አንድ ጊዜ  ልጄ "በሚስትና በገርል ፍሬንድ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ። እኔም ቀለል ባለ ምሳሌ እንዲህ...
27/07/2022

ባሻዬ! በዚህ ክረምት ልጆችን ጠቅላላ ዕውቀት ማስተማር ጥሩ ነው። አንድ ጊዜ ልጄ "በሚስትና በገርል ፍሬንድ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ። እኔም ቀለል ባለ ምሳሌ እንዲህ ስል አስረዳሁት፣

"ሚስት ቴሌቪዥን ማለት ሲሆን ገርል ፍሬንድ ደግሞ ሞባይል ስልክ እንደማለት ነው። ቤት ስትሆን ቴሌቪዥን ትመለከታለህ፣ ውጭ ስትሆን ደግሞ ሞባይልህን ትጠቀማለህ።

"አንዳንዴ ቲቪ እያየህ ትደሰታለህ፣ ብዙ ጊዜ ግን በሞባይልህ ትዝናናለህ። ቲቪ በነፃ ታያለህ ሞባይል ግን ካልከፈልክ አገልግሎቱ ይቋረጣል።

"ቲቪ መጠኑ ትልቅና ወፍራም ሲሆን በቀላሉ አታንቀሳቅሰውም። አንዳንዴም በአገልግሎት ብዛት ያረጃል። ሞባይል ግን ቆንጆ፣ ቀጭን፣ ለስላሳና አመቺ ነው። አንዳንዴ ተጣጣፊ አንዳንዴ ደግሞ ተንሸራታች ነው። እንደ ልብህም ታገላብጠዋለህ።

"የቴሌቪዥን የአግልግሎት ዋጋው ርካሽ ሲሆን፣ የሞባይል ግን ከባድና ውድ ነው። ቲቪ የመቀያየሪያ ሪሞት አለው፣ ሞባይል ግን የለውም።

"በሞባይል ሁለት ሰዎች እየተነጋገሩና እየተደማመጡ ይገለገሉበታል። በቲቪ ግን አንተ ወደድክም ጠላህም ተናጋሪው ቴሌቪዥኑ ብቻ ነው።

"ከሁሉም በላይ ቲቪና ሞባይል የሚለያዩት በቫይረስ ነው። ቲቪ ንፁህና ቫይረስ የማያጠቃው ሲሆን፣ ሞባይል ግን በየጊዜው ቫይረስ ሊገባበት ይችላል"

ባሻዬ! ቴሌቪዥንህን አጥብቀህ ያዝ!!

"የአማርኛ መፃፊያ ኪቦርድ የፈለሰፈው"የአማርኛ ቋንቋ መተየቢያ መኪና (Type writer) የተፈለሰፈው በ1925 ዓ.ም በኢንጂነርር አያና ብሩ ሲሆን ይህም ለአማርኛ ቋንቋ እድገት ትልቅ አስ...
03/07/2022

"የአማርኛ መፃፊያ ኪቦርድ የፈለሰፈው"

የአማርኛ ቋንቋ መተየቢያ መኪና (Type writer) የተፈለሰፈው በ1925 ዓ.ም በኢንጂነርር አያና ብሩ ሲሆን ይህም ለአማርኛ ቋንቋ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የተወለደው ኢንጂነር አያና ብሩ የአማሪኛ ኪቦርድ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን በ1920ዎቹ ፋሺስት ጣሊያንን የተዋጋ ብርቅዬ የኦሮሞ ልጅ ነው። ይህ ብቻም ሳይሆን ልጁ ጀነራል አበራ አያና ብሩም እንዲሁ በውትድረና ህይወት ያሳለፈ ጀግና ነበት።

Microsoft Collaborates with the Ethiopian Ministry of Education to Help Digitize the Education SectorMicrosoft has colla...
19/06/2022

Microsoft Collaborates with the Ethiopian Ministry of Education to Help Digitize the Education Sector

Microsoft has collaborated with the Ethiopian Ministry of Education to implement a Higher Educational Management Information System supporting the successful digital transformation of the education sector.

ይሄ ወቅት ከማንም በላይ አስቸጋሪ የሆነው ለወጣት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ምክንያቱም የወጣት ዋነኛ ቀለቡ ተስፋ ነው፡፡አሁን ላይ ደግሞ በቀላሉ አልገኝ ያለው ተስፋ ይመስለኛል፡፡ስራ የማግኘት ፥...
06/06/2022

ይሄ ወቅት ከማንም በላይ አስቸጋሪ የሆነው ለወጣት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ምክንያቱም የወጣት ዋነኛ ቀለቡ ተስፋ ነው፡፡አሁን ላይ ደግሞ በቀላሉ አልገኝ ያለው ተስፋ ይመስለኛል፡፡ስራ የማግኘት ፥ ገንዘብ የመቆጠብ ፥ ተምሮ ለውጥ የመፍጠር ፥ የራስን ቤት የማግኘት ፥ ተፍ ተፍ ብሎ ራስን የመቀየር ወዘተ ተስፋዎች ከምንጊዜውም በላይ አሁን ሩቅ ሆነዋል፡፡በዚህም የተነሳ ብዙ ወጣቶች እንዲሁ በቋፍ ላይ እንዳሉ እየታየ ነው፡፡ጥናትም ባላረግበት ከማየው እንደምረዳው ራስን ማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡
ወጣቱ ሁሉ እንዲህ በራሱ ጉዳይ አንጎል በሆነበት እና መስመር ላለመሳት በቋፍ ባለበት በዚህ ወቅት ለሰዎች የእርጋታ እና የሳቅ ምንጭ ለመሆን መሞከር እና ተስፋ ጨርሶ እንዳይጠፋ መሞከር ያስፈልጋል፡፡
#ነገየተሻለቀንይሆናል

Address

Piassa
Addis Ababa

Telephone

+251953902828

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beta ICT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Beta ICT:

Share