04/08/2023
ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣
ከአማራ ባንክ እና መካነ-ኢየሱስ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጋር ብሔራዊ የተቀናጀ የዲጂታል ክፍያ ፕላትፎርም ለመጠቀም የሚያስችል የሶስትዮሽ ውል ስምምነት ተፈራረሙ፡
ስምምነቱ የከተሞቹን ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት የክፍያ አሰባሰብ ለማዘመን የሚያስችል ሲሆን የከተሞቹ ውሃ እና ፍሳሽ ደንበኞች የውሃ አገልግሎት ክፍያን በአካል ቀርበው ከመክፈል ይልቅ ካሉበት ቦታ በተዘጋጀው ፕላትፎርም በኩል የቀረበውን የመክፍያ አማራጭ እና ሌሎችም ባንኩ ያቀረባቸውን አማራጮች በመጠቀም የውሃ ክፍያቸውን እንዲፈፅሙ በማድረግ አገልግሎት ለመስጠት በመስማማት ተፈራርመዋል፡፡