TraceNet Computer Network Design and Installation Company

TraceNet Computer Network Design and Installation Company Contact US for Any ICT issue

26/09/2017

Check out what's new

29/08/2017

ክላውድ ስቶሬጂ ክላውድ ስቶሬጂ የምንለው በኮምፒውተር የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ ኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነ...
20/08/2017

ክላውድ ስቶሬጂ
ክላውድ ስቶሬጂ የምንለው በኮምፒውተር የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ ኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጂቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክምንቶችን ለማስቀመጫ ድርጂቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

ባክአፕ ክላውድ በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጂ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft SkyDrive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጂተዋል፡፡
ማክሮሶፍት ድርጂት ላይ ለማስቀመጥ SkyDriveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡

32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነትእንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተ...
20/08/2017

32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት

እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አፕግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር፦
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡
ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡

64 ቢት ፕሮሰሰር፦
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡

ማስታወሻ
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር አምራቾች 64 ቢት ፕሮሰሰር በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው፡፡

13/08/2017

How to hide your IP address using a VPN and browse the Internet privately The Internet is the backbone of all things we do today. Without the Internet, we

04/08/2017

Try one of these 7 highest paying IT certifications and get yourself a megabucks job After reading our articles on ethical hacking courses, several of our

Check it out!
03/08/2017

Check it out!

CIA Agents Use Dumbo USB-based Hacking Tool to Disable Security Cameras And Microphones During Hollywood style Covert Operations

02/08/2017

Found the correct version to the flowchart.

Which Linux flavour should I go for?

29/07/2017

In this post, we will learn four ways of sending an email with attachment from the Linux command-line or terminal using several command line email clients.

በእንግሊዝ 22,000 ሰዎች መፀዳጃ ቤት በማፅዳት ነፃ ወይፋይ በክፍያ ሊቀበሉ ተስማምተዋል። ዝርዝሩን እነሆ፣
22/07/2017

በእንግሊዝ 22,000 ሰዎች መፀዳጃ ቤት በማፅዳት ነፃ ወይፋይ በክፍያ ሊቀበሉ ተስማምተዋል። ዝርዝሩን እነሆ፣

A public WiFi company just pulled a great stunt to show how potentially dangerous those mostly unread terms and conditions are. 

የኮምፒውተሮቻችን ስራን የመስራት ብቃት እና ቅልጥፍና እንደያዙት የፐሮሰሰር አይነት እና መጠን ይለያያል። ለመሆኑ የኮምፒውተሮቻችን ቅልጥፍና የሚወስነው ፐሮሰሰር አይነት እና ደረጃዎቹ ስንት ...
19/07/2017

የኮምፒውተሮቻችን ስራን የመስራት ብቃት እና ቅልጥፍና እንደያዙት የፐሮሰሰር አይነት እና መጠን ይለያያል። ለመሆኑ የኮምፒውተሮቻችን ቅልጥፍና የሚወስነው ፐሮሰሰር አይነት እና ደረጃዎቹ ስንት ናቸው? ፐሮሰሰሮችን ኮር i3,i5 እና 7 ብለን ስንል በምን መስፈርት ነው? የነዚህ ፐሮሰሰሮች መሰረታዊ ልዩነትስ ምንድነው? ሙሉ መረጃውን እነሆ፣

Which Intel processor should you buy? i3, i5 or i7! Have you ever been in the process of buying a new computer and wondered, which processor should I buy ?

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TraceNet Computer Network Design and Installation Company posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share