Mesob Creative

Mesob Creative Empowering brands with creative design and impactful digital strategies. Mesob Creative where storytelling meets strategy. Let’s bring your vision to life!

Mesob Creative Agency: Crafting culture through innovative design and digital marketing. Specializing in graphic design, branding, and content creation with a cultural touch. Let's bring your vision to life

ፕላስቲክ ተከለከለ? ትኩር ብለን እንይ! አዲስ "የፈጠራ በር" ተከፍቷል! ♻️✨ዛሬ በአዲስ አበባ የፕላስቲክ አጠቃቀም በይፋ ታግዷል። የለመድነው ነገር ሲገታ መጨነቅ ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ እኛ ...
03/02/2026

ፕላስቲክ ተከለከለ? ትኩር ብለን እንይ! አዲስ "የፈጠራ በር" ተከፍቷል! ♻️✨

ዛሬ በአዲስ አበባ የፕላስቲክ አጠቃቀም በይፋ ታግዷል። የለመድነው ነገር ሲገታ መጨነቅ ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ እኛ በ Mesob Creative ለውጡን የምናየው በሌላ መነጽር ነው። ትልልቅ የፈጠራ ስራዎች የሚወለዱት በትልልቅ "ግፊቶች" ውስጥ ነው።

ለምሳሌ ኮቪድ ሲመጣ "እንዴት ምርትና አገልግሎት ማግኘት እንችላለን ብለን አሳስቦን ነበር?" ነገር ግን የዲጂታል ክፍያን እና ዴሊቨሪን እንደለመድን ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ ፕላስቲክ ሲታገድ አዲስና ውብ የፈጠራ ባህል ልንጀምር ነው።

📍 ለምን ይሄን እንደ ትልቅ ዕድል (Opportunity) እናየዋለን?
1️⃣ የብራንዲንግ ለውጥ (Branding Evolution): አሁን ደንበኛህ "ፌስታል" ብቻ አይፈልግም። "ለአካባቢ ጥበቃ የቆመ ዘመናዊ ብራንድ" ይፈልጋል። ፕላስቲክ በሚያምር የጨርቅ (ሸማ) ወይም የወረቀት ከረጢት ስትተካ፣ ለደንበኛህ "እኛ ለትርፍ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድም እንጨነቃለን!" የሚል ጠንካራ መልዕክት እያስተላለፍክ ነው።

2️⃣ የዲዛይን አብዮት (Design Revolution): ፕላስቲክ ላይ ሎጎ ከመለጠፍ ባለፈ፣ በሀገራችን ተፈጥሯዊ ቁሳቁሶች ላይ የሚሰሩ ዲዛይኖች የቢዝነስህን ማንነት ይበልጥ "ቄንጠኛ" እና "ኢትዮጵያዊ" ያደርጉታል። ይህ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም አዲስ የስራ እድል የሚከፍት ነው።

3️⃣ ዘላቂነት (Sustainability) እንደ እሴት: የአውሮፓ እና የአሜሪካ ትልልቅ ቢዝነሶች "Eco-friendly" ለመሆን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያወጣሉ። እኛ ግን ይህ እድል በሩጫ መጥቶልናል። ዛሬ የምትወስደው እርምጃ ለወደፊቱ ቢዝነስህ ትልቅ የገበያ ተወዳዳሪነትን ይፈጥርልሃል።

💡 የ Mesob Creative መርህ እኛ የምናምነው "ችግር የፈጠራ እናት ናት" በሚለው ነው። ፕላስቲክ መታገዱ ስራችንን አይገታውም፤ ይልቁንም ይበልጥ ተፈጥሯዊ፣ ይበልጥ ኢትዮጵያዊ እና ይበልጥ ዘመናዊ እንድንሆን ያደርገናል።

ለውጡን አትፍራው፤ ተጠቀመበት! ፕላስቲክ ያልፋል፤ በፈጠራ የታጀበ ብራንድ ግን ለዘላለም ይኖራል።
እናንተስ ከፕላስቲክ ውጭ ምን አይነት "ቄንጠኛ" እና አካባቢን የማይጎዱ አማራጮችን ለቢዝነስህ እያሰባቹ ነው? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን። 👇

hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag

ሰዓት ማሰር 'ጌጥ' ነው፤ ሰዓት ማክበር ግን 'ብራንድ' ነው! ⌚️🇪🇹በሀገራችን የቢዝነስ ባህል ውስጥ አንድ የሚገርም ፓራዶክስ አለ፦ በእጃችን ላይ ውድ Apple Watch ወይም Rolexእና...
25/01/2026

ሰዓት ማሰር 'ጌጥ' ነው፤ ሰዓት ማክበር ግን 'ብራንድ' ነው! ⌚️🇪🇹

በሀገራችን የቢዝነስ ባህል ውስጥ አንድ የሚገርም ፓራዶክስ አለ፦ በእጃችን ላይ ውድ Apple Watch ወይም Rolexእናስራለን፤ ጭንቅላታችን ውስጥ ግን "እየደረስኩ ነው" የሚል የቆየ ሰበብ ይዞራል።

እንደ ብራንድ ስትራቴጂስት አንድ መራራ እውነት ልንገራችሁ፦ ቢዝነስ ሰዓት አይለይም፤ ቢዝነስ የሚለየው "ታማኝነትን" (Integrity) ብቻ ነው።
ሰዓት ማክበርን ከቴክኒካዊ ጉዳይነት አውጥተን በሶስት ጥልቅ የፍልስፍና ምሰሶዎች እንመልከተው፦

1. ጊዜ የኢንተግሪቲ (Integrity) መስታወት ነው
ብራንድ ማለት ቃል መግባት ነው። ሰዓት ደግሞ ያ ቃል ምን ያህል እውነት እንደሆነ የምናይበት መስታወት ነው።
ሰዓትህን የማታከብር ከሆነ፣ ቃላትህ ክብደት የላቸውም። ቃላትህ ክብደት ከሌላቸው ደግሞ ብራንድህ ባዶ ቅርፊት ነው። ውድ ሰዓት አርገህ ለቀጠሮ ስትረፍድ፣ ለዓለም የምታበስረው መልዕክት "የራሴን ውበት እንጂ የእናንተን ህይወት አላከብርም" የሚል ነው። ይሄ የብራንድ ክህደት ነው።

2. ሰዓት ማክበር የሰውን ህልውና ማክበር ነው
"እየመጣሁ ነው" ብለን ቤታችን ሆነን የምንዋሸው ውሸት ከቀጠሮ መጣስ በላይ የሆነ ጥልቅ ስብራት አለው።

አንድን ሰው ቀጠሮ ቦታ 1 ሰዓት ስታስጠብቀው፣ ዝም ብለህ ደቂቃዎችን እያባከንክ አይደለም፤ ከሰውየው እድሜ ላይ የማይመለስ 1 ሰዓት እየሰረቅህ ነው። ሰዓት ማክበር ማለት የሰውን ልጅ እድሜ እና የህይወት ዋጋ ማክበር ነው።

3. ፕሮቶኮል ወይስ ዲሲፕሊን?
ዩኒፎርም የለበሰ ሁሉ ወታደር እንዳልሆነ ሁሉ፣ ሰዓት ያሰረም ሁሉ ባለቀጠሮ አይደለም።
ሰዓት ማሰር የውጭ ማሳያ (Protocol) ነው። ሰዓት ማክበር ግን የውስጥ ማንነት (Character) ነው። ስማርት ዋችህ "ተነስ ተራመድ" እያለ ሲጮህብህ፣ አንተ ግን "ገና ነው" ብለህ የምታሸልብ ከሆነ፣ መሪው አንተ ሳትሆን ስንፍናህ ነው። እውነተኛ ብራንድ የሚገነባው ሰዓቱን ከእጅ ወደ ጭንቅላት ሲያወርዱት ብቻ ነው።

😊ካፌ ገብተን ማኪያቶአችን 5 ደቂቃ ሲዘገይ "ምን አይነት ሰራተኛ ነው?" ብለን እንናደዳለን። እኛ ግን የሰውን ሰዓት ስናባክን "አምስት ደቂቃ... አሁን መጣሁ" እያለን አመታትን እንቀጥላለን። መሞታችን እንደማይቀር ካመንን፣ ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም። የሰው ጊዜም አናባክን።

እኛ በ Mesob Creative የምናምነው ፍልስፍና ይሄንን ነው፦ "Time is the currency of Respect." ጊዜ የመከባበሪያ መገበያያ ገንዘብ ነው። ብራንድህን ከፍ ለማድረግ ከፈለግህ፣ ቃልህን በሰዓቱ ክፈል።

እናንተስ? በቀጠሮ መዘግየት በቢዝነስ ግንኙነታችሁ ላይ ያደረሰባችሁ ትዝታ ምንድነው? ይህን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ ያጋሩኝ። 👇
hashtag hashtag hashtag

ዛሬ ለShalom Design ያዘጋጀነውን የሎጎ ዲዛይን ይዘን መጥተናል! ይህ ዲዛይን የፋሽንን ውበት፣ የንጽሕናን እና የዘመናዊነትን ስሜት በአንድነት የሚያሳይ ነው።ሎጎው በMockup ሆኖ ሲ...
14/10/2025

ዛሬ ለShalom Design ያዘጋጀነውን የሎጎ ዲዛይን ይዘን መጥተናል! ይህ ዲዛይን የፋሽንን ውበት፣ የንጽሕናን እና የዘመናዊነትን ስሜት በአንድነት የሚያሳይ ነው።

ሎጎው በMockup ሆኖ ሲታይ ምን 'Feeling' (ስሜት) ሰጥቶዎታል?

እውነተኛ አስተያየትዎ ለቀጣይ ሥራችን ትልቅ ግብዓት ነው።

ሌሎች የዲዛይን ሥራዎቻችንን ለማየት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ:
https://t.me/c/1495661121/494

የእርስዎ እውነተኛ አስተያየት ለፈጠራ ሂደታችን ወሳኝ ግብዓት ነው። አስተያየት በመስጠት፣ Like እና Share በማድረግ ይሳተፉ!

መልካም የላብ አደሮች ቀን!
30/04/2025

መልካም የላብ አደሮች ቀን!

ያስፈልጋችሁትን አገልግሎት ወይም ምርት ምን እንደሆነ እባክዎ ይምረጡ።
12/04/2025

ያስፈልጋችሁትን አገልግሎት ወይም ምርት ምን እንደሆነ እባክዎ ይምረጡ።

በዚህ ቻናል መተላለፍ አለበት ብላችሁ የምታስቡት Graphic Design class / Freelance works / Online shopping / File sharing / Others

✨እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!  መልካም በዓል !መሶብ የጥበበኞች ማዕድ📥l        #ጥምቀት
19/01/2025

✨እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል !
መሶብ የጥበበኞች ማዕድ

📥l #ጥምቀት

🎨✨ Transform Your Brand with Digtila! ✨🎯🚀 Ready to take your business to the next level? At Digtila, we bring your brand...
10/01/2025

🎨✨ Transform Your Brand with Digtila! ✨🎯

🚀 Ready to take your business to the next level? At Digtila, we bring your brand to life with stunning:
✅ Branding Design – Build a brand identity that stands out.
✅ Graphic Design – From logos to visuals, we craft designs that inspire.
✅ Marketing Strategies – Connect with your audience like never before.

📈 Let’s make your business shine in a competitive market with creative designs and smart strategies!

🌐 Contact Us Today
📞 Call us: +251911098034
📩 Email: [email protected]
🌟 Your brand deserves to be unforgettable. Let’s create something amazing together!

26/11/2024
Welcome
04/10/2024

Welcome

Address

Addis Ababa
00251

Telephone

+251935369798

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesob Creative posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share