Computer trick and hacking ethiopia

Computer trick and hacking ethiopia get latest technology information

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአዲስ ደንበኞቹ ብዛት ከአንድ ሚሊዮን ማለፉን አስታወቀ። ⚡️ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከወር በፊት በጀመረው የቴሌኮም አገልግሎት የአዲስ ደንበኞቹ ብዛት ከአን...
18/11/2022

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአዲስ ደንበኞቹ ብዛት ከአንድ ሚሊዮን ማለፉን አስታወቀ።

⚡️ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከወር በፊት በጀመረው የቴሌኮም አገልግሎት የአዲስ ደንበኞቹ ብዛት ከአንድ ሚሊዮን ማለፉን ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል። ኩባንያው ባለፉት ሁለት ስምንታት ብቻ 200 ሺህ ደንበኞችን እንዳፈራ የኩባንያው መረጃ ያመለክታል።

⚡️የኩባንያው ተፎካካሪ ኢትዮ ቴሌኮም አለኝ የሚለው የደንበኛ ብዛት 58 ሚሊዮን ነው። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ ካለፈው ጥር ወዲህ አዲስ በጀመረው የቴሌኮም አገልግሎት ላይ 300 ሚሊዮን ዶላር ማፍሰሱን እና በጠቅላላው 650 ሠራተኞችን ቀጥሬያለሁ ብሏል።

ለቀለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ🧩🧩 https://t.me/techzoneethio

የቲውተሩ ባለቤት ኤለን መስክ ሠራተኞቹን አስጠነቀቀ።⚡️በቅርቡ ትዊተርን የገዛው ኤሎን መስክ ሠራተኞቹ “ ለረዥም ሰዓት በከፍተኛ ጥንካሬ” ለመሥራት ቁርጠኝነት ከሌላቸው ኩባንያውን እንዲለቁ ...
18/11/2022

የቲውተሩ ባለቤት ኤለን መስክ ሠራተኞቹን አስጠነቀቀ።

⚡️በቅርቡ ትዊተርን የገዛው ኤሎን መስክ ሠራተኞቹ “ ለረዥም ሰዓት በከፍተኛ ጥንካሬ” ለመሥራት ቁርጠኝነት ከሌላቸው ኩባንያውን እንዲለቁ መናገሩን ሪፖርቶች ይፋ አድርገዋል።

⚡️አዲሱ የማኅበራዊ ድርጅት ባለቤት ለሠራተኞች በላከው ኢሜል ሠራተኞቹ በኩባንያው መቀጠል ከፈለጉ በዚህ ዓይነት አሠራር ለመቀጠል ቃል መግባት እንዳለባቸው ማሳሰቡን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። በኩባንያው አሠራር የማይስማሙ የሦስት ወር የሥራ ስንብት ክፍያ እንደሚሰጣቸው መስክ ተናግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/techzoneethio

አፕል በቀጣይ የሚያመርታቸው የአይፎን ስልኮቹ የUSB-C የቻርጀር እና የዳታ ኬብል እንደሚቀበሉ ገለፀ። ⚡️ ቀደም ሲል በአውሮፓ ህብረት ሁሉም ስልኮች እና ታብሌቶች በ 2024 USB-C  የ...
30/10/2022

አፕል በቀጣይ የሚያመርታቸው የአይፎን ስልኮቹ የUSB-C የቻርጀር እና የዳታ ኬብል እንደሚቀበሉ ገለፀ።

⚡️ ቀደም ሲል በአውሮፓ ህብረት ሁሉም ስልኮች እና ታብሌቶች በ 2024 USB-C የቻርጀር እና ዳታ ኬብል እንዲቀበሉ የተላለፈ ህግ እንደነበረ ይታወሳል። ነገር ግን ይህ ህግ ልክ እንደ አፕል ላሉ የራሳቸውን የፈጠራ ዲዛይን ለሚጠቀሙ ድርጅቶች ትልቅ ስጋት ሆኖ ከርሟል።

⚡️ የአፕል አይፎን ተጠቃሚዎች ከአፕል ውጪ በሌላ ድርጅት የተመረቱ USB-C ቻርጀር፣ ዳታ ኬብሎች እና ሌሎችም መሳሪያዎች እንዳይገዙ እንደሚፈልጉና የእነዚ አይነት ቁሶችን ሙሉ ለሙሉ በአፕል ድርጅት እንዲሸጡ ፍላጎት ስለነበራቸው እንጂ የዚህ አይነት ጥያቄ በተደጋጋሚ ይደርሳቸው እንደነበር ባለሞያዎች ይገልጻሉ።

⚡️ የታዋቂው የቴክኖሎጂ ድርጅት አፕል የበላይ ሀላፊዎች በውሳኔው ደስተኞች ባይሆኑም የአለም መንግስታቶች ብዙ ነገር የማድረግ ስልጣን ስላላቸው አፕልም ይህን ውሳኔ ከመቀበል ውጭ ብዙ አማራጭ እንደሌላችው የአፕል ምክትል ፕሬዚዳንት ግሬግ ጆስዊአክ ገልጸዋል።

ሬድ ፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት በኢትዮጵያ ስራ ጀመረለተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት መረጃ ማዕከል በመሆን የሚያገለግል ሬድ ፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት በዛሬዉ እለት ስራ ጀምሯል። በ ...
19/09/2022

ሬድ ፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

ለተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት መረጃ ማዕከል በመሆን የሚያገለግል ሬድ ፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት በዛሬዉ እለት ስራ ጀምሯል። በ 10 ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ተቋቁሞ ስራዉን የጀመረው የመረጃ ቋቱ ፤ ለጤና ተቋማት የመረጃ አያያዝ ፣ ለቢዝነስ ተቋማት ፣ ለመንግስት እና የግል ድርጅቶች መረጃ ደረጃዉን በጠበቀ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ያስቀምጣል ነዉ የተባለዉ።

የሬድ ፎክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዳነ ካሳዬ እንዳሉት ተቋሙ መቀመጫዉን አዲስአበባ ያድርግ እንጂ ከኢትዮጵያ ባለፈም በቀጠናው ፣ አህጉረ አቀፍ እና በአለማቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ተቋም ለመሆን እቅድ እንዳለዉ ገልጸዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚዉን ከማሳለጥ አንጻርም ይህን መሰል የመረጃ ቋቶች አስፈላጊ መሆናቸዉን የፌድፎክስ ሶሉሽንስ ስራ ዋና አስፈፃሚዉ ተናግረዋል። የተለየ ምርጫን ይዞ ከመምጣቱ ባለፈም ለሀገር ዉስጥ ተቋማት ክፍያቸዉን በብር እንዲፈጽሙ እንደሚያስችላቸዉም ተገልጿል። አሁን ባለዉ ገበያ ከኢትዮ ቴሌኮም እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ተፎካክሮ እና ተወዳድሮ ለመስራት ስጋት እንደሌለበትም ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ጨምረዉ አንስተዋል።

የተቋሙ የቴክኖሎጂ ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳግማዊ ቴድሮስ በበኩላቸዉ በሙሉ አቅሙ ስራዉን ሲጀምርም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑንም መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ 🧩🧩 https://t.me/techzoneethio

ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊውን የኢ-ሲም አገልግሎት መስጠትየሚሰጣቸው ጥቅሞችቀላል እና ብቁ የኔትወርክ ግንኙነትበአንድ ስልክ ከአንድ በላይ የአገልግሎት ቁጥር መጠቀም የሚያስችልሲም ካርድ እየቀያየሩ...
17/09/2022

ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊውን የኢ-ሲም አገልግሎት መስጠት

የሚሰጣቸው ጥቅሞች

ቀላል እና ብቁ የኔትወርክ ግንኙነት

በአንድ ስልክ ከአንድ በላይ የአገልግሎት ቁጥር መጠቀም የሚያስችል

ሲም ካርድ እየቀያየሩ መጠቀምን ያስቀራል

ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በቀላሉ ለማገናኘት፣ ለአምራቾች፣ አከፋፋዮች እና አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም የተለያዩ ዲጂታል ዲቫይሶችን በቀላሉ በማገናኘት ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት ፍላጎት ላላቸው ሁሉ የቀረበ ምርጥ መላ፡፡

በኢ-ሲም የሚሰሩ ስልኮች

ሳምሰንግ

Samsung Galaxy S20

Samsung Galaxy S20+

Samsung Galaxy S20 Ultra

Samsung Galaxy S21

Samsung Galaxy S21+ 5G

Samsung Galaxy S21+ Ultra 5G

Samsung Galaxy S22

Samsung Galaxy S22+

Samsung Galaxy Note 20

Samsung Galaxy Note 20 Ultra 5G

Samsung Galaxy Fold

Samsung Galaxy Z Fold2 5G

Samsung Galaxy Z Fold3 5G

Samsung Galaxy Z Flip

አይፎን

iPhone XR

iPhone XS

iPhone XS Max

iPhone 11

iPhone 11 Pro

iPhone SE 2 (2020)

iPhone 12

iPhone 12 Mini

iPhone 12 Pro

iPhone 12 Pro Max

iPhone 13

iPhone 13 Mini

iPhone 13 Pro

iPhone 13 Pro Max

iPhone SE 3 (2022)

ጉግል

Google Pixel 3a XL

Google Pixel 4

Google Pixel 4a

Google Pixel 4 XL

Google Pixel 5

Google Pixel 5a

Google Pixel 6

Google Pixel 6 Pro.

Google Pixel 3 XL

Google Pixel 2 XL

ሁዋዌ

Huawei P40

Huawei P40 Pro

Huawei Mate 40 Pro

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ 👉👉👉 t.me/techzoneethio

የቻይናው AG600 የተሰኘ አዲስ አውሮፕላን  ከመሬት ወደ ውሃ አካላት ማረፍ የሚችልና ከውሃ አካላት መነሳት የሚችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ አውሮፕላኑ በመነሻነት በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ሁ...
06/09/2021

የቻይናው AG600 የተሰኘ አዲስ አውሮፕላን ከመሬት ወደ ውሃ አካላት ማረፍ የሚችልና ከውሃ አካላት መነሳት የሚችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ አውሮፕላኑ በመነሻነት በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ሁኔታዎች ውስጥ በረራዎችን ለማድረግ ታልሞ የተሰራ ሲሆን በቻይና 13ኛው አለማቀፍ የአቪየሽን ኢግዚቪሽን ላይ ከምድር ወደ ውሃ እንዴት ማረፍ እንደሚችል የሚያሳይ ይሆናል፡፡
አውሮፕላኑን ያበለጸገው የቻይይና አቪየሽን ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እንዳወጣው መረጃ አውሮፕላኑ ያለውን እሳት አደጋን የመቆጣጠር ብቃት በበረራው ወቅት ያሳያል ተብሏል፡፡ ለአውሮፕላኑ የተሰጠው የኮድ ስምም በቻይና የአደጋ መከላከል ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ጥቅም ያለውን ቁስ ምክንያት ያደረገ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በዚህም አውሮፕላኑ በእሳት አደጋ፣ የባህር ላይ አደጋ እና ሌሎች ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋ ሲያጋጥም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ያስችላል፡፡
የመጀመሪያ በረራውን በ2017 በስኬት ያጠናቀቀው አውሮፕላኑ ለግድብ ከተከማቸ ውሃ (a water reservoir) በ2018 አኮብኩቦ መነሳት የቻለ ሲሆን በ2020 ደግሞ መነሻውን ከውቅያኖስ ላይ አድርጎ በረራውን አካሂዷል፡፡ የዚህ አመት የቻይና የበረራ ኤግዚቢሽን ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ በደቡባዊ የቻይና ክፍል ጓንግዶንግ እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

ምንጭ Xinhua net

01/09/2021

ዊንዶው 11 ቀን ተቆረጠለት
*******************
የዊንዶው 10 ተከታይ የሆነው ዊንዶው 11 የተሰኘው መጠቀሚያ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት 5 ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተነገረ፡፡ ላለፉት ጥቂት ወራት ሙከራ ሲደረግበት የነበረው ይህ ፕላትፎርም ከዚህ በፊት የነበረንን መጠቀሚያዎች ለማሻሻልና እንደ ዴል፣ ሌኔቮ ሌሎች የኮምፒውተር አይነቶች ላይ ተጭኖ እንደሚቀርብ ተነግሯል፡፡

በቀጠሮው እለት የሚቀርበውን ማሻሻያ የተደረገበትን የዊንዶው አይነት እንደቀድሞው (አሁን ላይ ጥቅም እየሰጠ ያለው ዊንዶው 10) ተመሳሳይ ማሻሻሎች (updates) ያሉት ሲሆን የቫይረስ ተጋላጭነቱ ዝቅተኛ ነው ሲል ማይክሮሶፍት አሳውቋል፡፡ ወደ ዊንዶው 11 ማሳደጊያውም በነጻ የቀረበ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡


ምንጭ Digital trends

የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡በመስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቀው አዲሱ የአፕል ኩባንያ ምርት አይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን ...
30/08/2021

የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

በመስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቀው አዲሱ የአፕል ኩባንያ ምርት አይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

የቴሌኮም አገልግሎቶች ተደራሽ በማይሆኑባቸው አካባቢዎች በታችኛው የመሬት ምሕዋር የሚገኙ ሳተላይቶችን በመጠቀም የድምፅ እና የአጭር መልዕክት አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚችል ሲኔት ዘግቧል፡፡

አዲሱ ስልክ በሳተላይት አማካኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው Qualcomm X60 የተባለ ቺፕ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህ አዲስ ገፅታ ከቴሌኮም አገልግሎቶች ርቀው ለሚኖሩ እና መሰል አገልግሎቶች ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ተጠቃሚዎችን ትኩረት እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ (Cnet, AICE)

23/03/2021

💥የቢል ጌት እና ጆ ባይደንን አካውንት ሀክ ያደረገው ታዳጊ እስር ተፈረደበት

ባሳለፍነው ሐምሌ የታዋቂ ግለሰብ እና ተቋማትን ትዊተር ገፅ ሀክ በማድረግ እነርሱን መስሎ የቢትኮይን ገንዘብ ዝውውር ይደረግለት ዘንድ በትዊት የጠየቀው የ18 ዓመት ታዳጊ ሦስት ዓመታትን በእስር ለማሳለፍ ተስማማ፡፡ ከአሜሪካኗ የፍሎሪዳ ግዛት የሆነውና ጥቃቱን ሲሰነዘር ገና የ17 ዓመት ታዳጊ የነበረው ግሬሄም አይቫን ክላርክ የጆ ባይደን፣ ቢል ጌት፣ ኢለን መስክ፣ ባራክ ኦባማ እና የሌሎችንም ዝነኞች ትዊተር የትዊተር ገፅ ነው ሀክ አድርጎ ድርጊቱን የፈፀመው፡፡

ክላርክ በቅድሚያ ወደ ገፆቹ መግባት የቻለው የትዊትር ሰራተኞችን በዚያው በድርጅቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ውስጥ እንደሚሰራ ማሳመን ከቻለ በኋላ ነው፡፡ የግለሰቦቹ ገፅ ውስጥ ከገባ በኋላም “ከታች ባለው ሊንክ የሚላኩ ሁሉም ቢትኮይኖች እጥፍ ሆነው ይመለሳሉ” ብሎ ትዊት አድርጎባቸዋል፡፡ የፍርድ ቤት ሰነዶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግሬሄም በዚህ ድርጊቱ ከ100 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰብ ችሏል፤ ምንም እንኳን ጠበቆቹ የኋላ ኋላ አንድም ሳያስቀር መመለሱን ቢናገሩም፡፡

በከፍተኛ የደህንነት ጥሰት ውስጥ የወደቀው ትዊተርም ሁኔታው እንደተከሰተ ማንኛቸውም ማረጋገጫ የተሰጣቸው ወይም ቨርቲፋይ የሆኑ አካውንቶች ለሰዓታት ትዊት ማድረግ እንዳይችሉ አድርጓቸው ቆይቷል፡፡ በወቅቱ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የነበረው ግሬሄምም በቀናት ጊዜ ውስጥ በሕግ አካላት ቁጥጥር ስል እንዲውል ሆኗል፡፡

ታዳጊው ከሕግ አካላቱ ጋር ባደረገው ስምምነት በተደራጀ የማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛነቱን አምኖ የቀረበ ሲሆን እስከ 30 ዓመታት ዘብጥያ ሊያስወርድ በሚችለው በዚህ ወንጀልም እንደ ታዳጊ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ሦስት ዓመታትን ብቻ በእስር እንደሚያሳልፍ ተነግሯል፡፡ የተወሰነው የእስር ጊዜውንም “ቡት ካምፕ” ተብለው በሚታወቁት የታዳጊ ማቆያቀዎች እንደሚያሳልፍም ተነግሯል፡፡ የሂልስብሮ ግዛት አቃቢ ሕጉ አንድሪው ዋረን አላማቸው የታዳጊዎችን ሕይወት ማበላሸት ሳይሆን ከስህተታቸው እንዲማሩ መሆኑን ከግምት በማስገባት የቅጣት እርምጃዎቹ መወሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ከጥቃቱ ጋር በተገናኘ ሜሶን ሼፐርድ እና ኒማ ፋዝሊ የተባሉ ከብሪታንያ እና ከዚያው ከፍሎሪዳ የሆኑ ሌሎች ሁለት ታዳጊዎችም ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን የእነርሱ ጉዳይ በሕግ እየታየ ይቆያል፡፡

ምንጭ፤ The Guardian

✳️ ኦርጅናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ እንዴት መለየት ይቻላል። እነዚን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።🏷 የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገምፌክ ሳምሰንግ ስል...
15/01/2021

✳️ ኦርጅናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ እንዴት መለየት ይቻላል። እነዚን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።

🏷 የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም
ፌክ ሳምሰንግ ስልክ

1. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
2. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
3. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
4. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
5. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን
ይመለከታሉ፡፡

🏷 የስልኩን ፍጥነት እና ትእዛዞችን አፈጻፀም በመገምገም

1. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል
2. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡
3. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም

🏷 የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም

1. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን ይጫኑ
3. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

🔔 * #0* # #አጠቃላይ መገምገሚያ
🔔 * #1234 # or * #9999 # ስልኩ የሚጠቀመዉን
#ሶፍትዌር እና #ሞደም ማወቂያ
🔔 * #12580*369 # #ስለ ስልኩ #ሶፍትዌር እና #ሀርድዌር ማወቂያ
🔔 * #06 # #የስልኩን ኢንተርናሽናል #መለያ ቁጥር
ማወቂያ
🔔 * #9998*246 # #የስልኩን #የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ
ሳምሰንግ ኪይ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ
ይጫኑት
2. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት
3. ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

You can view and join right away.

29/12/2020
❓ለመጀመርያ ግዜ ኢንተርኔት አግኝተህ "Google" ላይ "Search" ያደረከው ነገር ምንድነው❓የአሜሪካዋ የቴክኖሎጂ መናገሻ በምትባለው "San Francisco" "Silicon Valley" ...
23/12/2020

❓ለመጀመርያ ግዜ ኢንተርኔት አግኝተህ "Google" ላይ "Search" ያደረከው ነገር ምንድነው❓
የአሜሪካዋ የቴክኖሎጂ መናገሻ በምትባለው "San Francisco" "Silicon Valley" ውስጥ የሚገኘው "Google" ኩባንያን ለየት የሚያደርገው የቢሮው ሁኔታ እና የሰራተኞቹ የአሰራር መንገድ ነው።

ተቀጣሪዎች "....በዚህ ሰዓት ውጣ፣ በዚህ ሰዓት ግባ ፣ ከዚህ እስከ እዚህ ሰዓት ስራ፣ ፊርማ ፈርም፣ እዚህ ተቀመጥ ፣ ይሄንን አትጠይቅ፣ ይሄንን አትንካ፣ ይሄንን ብቻ ስራ!...." ምናምን መባል የለባቸውም! እንደዚህ አይነት ኃላ ቀር አሰራሮች ለብዙ አመታት ውጤት አላመጡም!፣ ፈጠራን አላበረታቱም!፣ ሰራተኛውንም አሰሪውንም አልጠቀሙም!" ብሎ የሚያምነው የ "Google" ኩባንያ የራሴ አሰራር፣ የራሴ የስራ ፍልስፍና አለኝ ይላል! በዚህም ፍልስፍና እጅግ ውጤታማ ሆኗል!

የመጀመርያው ድርጅቱን ከስራ ቦታ ይልቅ ሁሉም ነገር የተሟላለት መኖርያ ቤት የሚመስልበትን መንገድ ፈጠሩ። የተለመደውን የቢሮ ቅርፅ አስወገዱ! ድርጅቱ ውስጥ የአለቃ እና የሰራተኛ ወንበር የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ቢሮ ክፍት ነው። ሁሉም የፈለገበት ቦታ ላይ ተቀምጦ መስራት ይችላል! የግል ንብረት፣ የግል ኮምፒውተር፣ የግል ወንበር ምናምን የለም! ማንም የምንም ነገር ባለቤት አይደለም! ሁሉም ነገር የሁሉም ንብረት ነው።

የሰራተኞቹን የፈጠራ ብቃት ለመጨመር እና አዕምሯቸው የተፍታታ እንዲሆን በማሰብ የሚዝናኑባቸው እንደ ፑል፣ ቴኒስ፣ ጆተኒ፣ ጎልፍ፣ ዲጅታል ጌም መጫወቻዎች፣ መዋኛ ገንዳዎች እና የሙዚቃ መሳርያዎች በየቦታው አሉ። አንድ ሰራተኛ በፈለገበት ሰዓት መጫወት እና መዝናናት ይችላል።

ስራህን ስትሰራ የተሻለ ስሜት እንዲሰማህ ውሻህ ወይም ድመትህን ጭምር ይዘህ መሄድ ትችላለህ። ድርጅቱ ገደብ (Limitation) የሰዎችን የመፍጠር "tendency" ይቀንሳል! ብሎ ያምናል።

ውስጡ ከ 25 በላይ ትልልቅ ካፍቴርያዎች እና ሬስቶራንቶች ያሉት "Google" ሰራተኞቹ በፈለጉት አጋጣሚ ያሻቸው ምግብ እንዲቀርብላቸው ያደርጋል። አንድ ሰራተኛ ከ 200 ጫማ (60 ሜትር) በላይ ከምግብ መራቅ የለበትም በሚል ፍልስፍናም ድርጅቱ ያምናል! "የራበው አይሰራም! ሁሉም ነገር የቀረበለት ሰራተኛ ደግሞ ትኩረቱን ወደ ስራ እና ስራ ብቻ ማድረግ ይችላል!" በሚል አመለካከት ያምናሉ።

ሰራተኞቹ አዓምሯቸው ከተወጣጠረ እራሳቸውን ለማፍታታት በቢሮ ውስጥ ማሳጅ የሚደረጉባቸው ክፍሎች እና የሰለጠኑ እና ፍቃድ ያላቸው የማሳጅ ቴራፒስቶች ዝግጁ ሆነው ይጠብቋቸዋል!

ለአካባቢያዊ አየር ጥበቃ ካላቸው ትኩረት የተነሳ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞቹ ከስራ ቦታ ወደ ቤት/ከቤት ወደ ስራ ቦታ የሚመላለሱት የልቀቅ መጠናቸው እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆኑ ባሶች ነው። እያንዳንዱ ሰራተኛ የራሱን መኪና እየነዳ ቢመላለስ በአመት ሊለቀቅ የሚችለውን ከ 20 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ልቀት መቀነስ ተችሏል። ግቢ ውስጥ ሰራተኞች የሚንቀሳቀሱት በሳይክል ነው! ይህም ልቀትን ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል!

👉በቅጥር ግቢው የሚበቅለውን ሳር/አረም ለማስወገድ "Google" ማሽኖችን" ሳይሆን "ፍየሎችን" ነው የሚጠቀመው! በየግዜው ፍየሎችን እየተከራየ በግቢው ውስጥ የሚበቅለውን ሳር/አረም እንዲግጡለት ያደርጋል! አንድ ሰራተኛ እየሰራ በአጠገቡ ፍየል ሲያልፍ አይደንቀውም!😃 ሰራተኞቹ እንደውም እነዚህን ፍየሎች ማየታችን የፈጠራ አቅማችንን ጨምሮልናል ይላሉ።

"Google" ዋናው ኩባንያ አጠገብ ለምትገኘው "Mountain View" ለምትባል አነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ በነፃ ዋይ ፋይ እንዲያገኙ እና ኢንተርኔትን ያለምንም ገደብ እንዲጠቀሙ አድርጓል።

በድርጅቱ የተቀጠረ ሰራተኛ ህይወቱ ቢያልፍ ሚስት ወይም ባል የሟች 50% ደሞዝን ለ 10 ዓመታት እንዲከፈላት/እንዲከፈለው ይደረጋል።

በአጠቃላይ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኞች ላፕቶፓቸውን ይዘው ሸርተቴ እና ዥዋዥዌ ሲጫወቱ ማየት ብርቅ አይደለም።

"Larry page" እና "Sergey Brin" በተባሉ በ "Stanford University" የ "PHD" ተማሪዎች የተመሰረተው "Google" ኩባንያ አሁን ላይ ከ 500 ቢልዮን ዶላር በላይ "worth" የሚያደርግ ሲሆን የዓለማችን "Most Visited website" ነው። የዛሬ 22 ዓመት ሲመሰረት የመጀመርያ ቢሮው የክራይ ጋራዥ ውስጥ ነበር። በወቅቱ በተከራዩት ገራዥ ውስጥ 16 ሰራተኞች ብቻ ነበራቸው! አሁን ላይ በዓለም የተለያዩ 50 ሃገራት 70 ግዙፍ ቢሮዎች እና በ ብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞች አሉት።

የመጨረሻ!

"Google" በመጀመርያ ስፔሊንጉ "Googol" የነበረ ሲሆን መስራቾቹ የድርጅቱን "Domain" ለማስመዝገብ ሲሄዱ በተፈጠረ የስፔሊንግ ስህተት ነው "Google" ተብሎ የቀረው። በነገራችን ላይ በአማካይ በቀን "1 ቢልዮን" ነገሮች "Google" ላይ "Search" ይደረጋሉ።

⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251963914160

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Computer trick and hacking ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share