14/06/2026
ውድ የበናሶፍት ቤተሰቦቻችን!
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የተሻሻለው የበናሶፍት ኢ.አር.ፒ ዕትም 3.6.0 የሙከራ ጊዜውን አጠናቅቆ ዛሬ ማለትም ሰኔ-08-2018ዓም በይፋ ተለቋል✅
ይህ አዲስ ማሻሻያ የሚከተሉትን ያካትታል፦
📱 የተሻሻለ የተጠቃሚ ገጽታ እና የስራ ቅልጥፍና
🔒 አስተማማኝ ደህንነት እና የስርዓት መረጋጋት
📊 የተሻሉ የሪፖርት እና የዳሽቦርድ አማራጮች
⚡️ ፈጣን የክፍያ መጠየቂያ (ኢንቮይስ) እና የግብይት ሂደት
🧾 የተሻሻሉ የሂሳብ አያያዝ እና የንብረት ቁጥጥር ሞጁሎች
📱 ለሞባይል ምቹ የሆኑ ማሻሻያዎች
🐞 የቴክኒክ ስህተቶች (Bugs) እርማት እና የስርዓት ማመቻቸት
ለሁሉም ነባር ተጠቃሚዎች ወደ ተሻሻለው ዕትም ያለምንም ክፍያ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የምናሳድግ [Update የምናደርግ] መሆኑን በደስታ እየገለፅን፤ ማሻሻያዎችን መጠቀም የማትፈልጉ ደንበኞቻችን በ0912092158 በመደወል እንድታሳውቁን እንገልጻለን።
ወደ አዲሱ እትም የምንቀይርበትን (Update የምናደርግበትን] ቀን በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) የምናሳውቅ ይሆናል።
በበናሶፍት ኢ.አ.ርፒ (BenaSoft ERP) ላይ ላላችሁ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና እምነት እናመሰግናለን። ❤️