Gecho_ICT

Gecho_ICT Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gecho_ICT, Computer Company, 14, Bahir Dar.

ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!!፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡☞ ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጀ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየ...
03/02/2023

ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
☞ ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጀ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ አስተማሪውን "አስታወስከኝ ወይ?" አለው።

አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" አለው፤ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ፤ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር።

እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ሄዶ ይናገራል፤አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፍታችንን ወዴ ግድግዳ ኣዙረን እንድንቆም አዘዝከን።በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤የምገባበትን አጣሁ።

አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ሲሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርግቴን ስሰሙ።

በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ስገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤በቃ መጥፎ ዜናው ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ።

ፍተሻውም ስያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን።እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ።በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።

በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠራ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤አንተም ምንም ብለሃኝ አታውቅም።እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬ እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው።

አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።

አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው።

በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል።እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!!
አስተማሪ ሆኖ ካገኘህ ለወዳጅህ አካፍለው

 #ብሉቱዝ ( )ብሉቱዝ በአጭር ርቀት ውስጥ ምንም አይነት ገመድ ሳይጠቀም ዝቅተኛ ፓወር ራዲዮ ቴክኖሎጂ በመጠቀም  #ስልኮች፤  #ኮምፒውተሮች እና የተለያዩ ኔትወርክ ዲቫይሶች እንዲገናኙ( ኮ...
09/01/2023

#ብሉቱዝ ( )
ብሉቱዝ በአጭር ርቀት ውስጥ ምንም አይነት ገመድ ሳይጠቀም ዝቅተኛ ፓወር ራዲዮ ቴክኖሎጂ በመጠቀም #ስልኮች፤ #ኮምፒውተሮች እና የተለያዩ ኔትወርክ ዲቫይሶች እንዲገናኙ( ኮሚኒኬሽን እንዲያደርጉ) ያስችላል፡፡ ብሉቱዝ ስታንደርድ 802.15.1 ሲሆን ስሙን የወሰደው 1000 ዓመት በፊት ከነበረ Bluetooth ከተባለ #ዴንማርክ ንጉስ ነው፡፡

#ብሉቱዝ ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲዛይን የተደረገው ቀላል ዋየርለስ ኔትወርክ ዲቫይሶችን፤ ስልኮችን እና ዋየርለስ ሄድሴት ሰፖርት ለማድረግ ሲሆን ዋየርለስ ሲግናል ትራንስሚትድ (የሚተላለፈው) በብሉቱዝ በአጭር ርቀት 10 ሜትር ውስጥ ነው እንዲሁም ብሉቱዝ ዲቫይሶች በአጠቃላይ ግንኙነት የሚያደርጉት ያነሰ ነው፡፡

#የብሉቱዝ ኔትወርክ #ፒኮኔት ( ) ወይም ፐርሰናል ኤርያ ኔትወርክ ( ) ሲሆን ፒኮኔት ቢያንስ ቢያንስ 2 እና ከ8 ያልበለጡ ብሉቱዝ ዲቫይሶች የተገናኙበት የብሉቱዝ ኔትወርክ አይነት ነው፡፡ ዲቫይሶች ግንኙነት ሲያደርጉ ፕሮቶኮል ይጠቀማሉ። ብሉቱዝ የተለያዩ ቨርዥን ሲኖሩት እነሱም 1.1, 1.2 እና 2.0 ናቸው፡፡

#ብሉቱዝ በተለያዩ ዲቫይሶች ላይ የምናገኘው ሲሆን ለምሳሌ፡- #በኮምፒውተር፤ #በስልክ፤ #በጌም መጫወቻዎች፤ #ሄድሴት፤ ወዘተ
ብሉቱዝ ዲቫይሶች ለማገናኘት ምንም አይነት ኢንስታሌሽን ወይም ኮንፊገሬሽን (ኔትወርክ ዝርጋታ) አያስፈልግም በቀላሉ ዲቫይሱን ብሉቱዝ ኢኔብል (መክፈት) ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡
👇
https://t.me/gechoICT

🆙  Telegram Hack እንዳይደረግብን ማድረግ ያለብን ወሳኝ ነጥቦችን እነሆ ከዚህ በታች አስቀምጬላችኋለው:-         ➡️ ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging appli...
09/10/2022

🆙 Telegram Hack እንዳይደረግብን ማድረግ ያለብን ወሳኝ ነጥቦችን እነሆ ከዚህ በታች አስቀምጬላችኋለው:-


➡️ ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc

👉 Telegram እንደ Viber, Whatsapp,imo በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል

👉 ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ .... ነው

👉 በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉ
👉 Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

ማሳሰቢያ: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።

👉 ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

✅ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***** ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

✅ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

✅ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
👉 ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
👉 ማንም ሰው ለመግባት በ E-Mail የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።
👉 የሰጠነውን Password እንዳይጠፋን በጥንቃቄ መያዝ ይጠበቅብናል።
https://t.me/gechoICT

32 Vs 64 bit OSየርስዎ ኮምፒውተር 32 ቢት ውይም 64 ቢት ሲፒዮ ነው? ልዩነት ምንድን ነው?32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ መሆኑን ለማወቅ Computer ላይ Right click -> ...
07/10/2022

32 Vs 64 bit OS

የርስዎ ኮምፒውተር 32 ቢት ውይም 64 ቢት ሲፒዮ ነው? ልዩነት ምንድን ነው?

32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ መሆኑን ለማወቅ Computer ላይ Right click -> properties -> system type የሚለውን ይመልከቱ
እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር 32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ
ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡
ማስታወሻ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 32 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች
የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም) 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad
core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡ 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር
አምራቾች 64 ቢት ፕሮሰሰር በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው።
https://t.me/gechoICT

👉 ኮምፒውተራችን ላይ  #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እን...
05/08/2022

👉 ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።

👉ኮምፒውተራችንን ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል አድርገን እንዴት መቆለፍ እንችላለን።

1⃣ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት this pc ወይም my computer ላይ Right Click እናደርጋለን።
2⃣ ከዛም ከሚመጡልን ምርጫዎች ውስጥ Manage የሚለውን እንመርጣለን።
3⃣ ቀጥሎም Device Manager
4⃣ ከዛም በቀኝ በኩል ካሉት ምርጫዎች Universal Serial Bus Controllers ከሚለው ስር ያለውን drop down arow ወይም የዝርዝር ቀስቱን እንነካለን።
5⃣ ከዛም extensible host controller ላይ ራይት ክሊክ እናደርጋለን ።
6⃣ ከተዘረዘሩት ዉስጥ Disable ክሊክ እናደርጋልን አለቀ👍👍👍
🔴 ወደነበረበት ለመመለስ Enable Device የሚለውን ይጫኑ!

👍አሁን ላፕቶፓችን ወይም ዴስክ ቶፕ ኮንፒተራችን ፍላሽ፣ሃርድዲስክ እንዳያነብ ብሎክ ሁኖል ማለት ነው።
ወደ ቴሌግራም ይግቡ!
https://t.me/gechoICT

ስልካችን ቢጠፋብን ቀድመን ልናደርገው የሚገባን-----------------***----------------የጠፋብን ወይም የተሰረቀ ሞባይል በቀላሉ ማግኘት የምቻልበት መንገድ። ሞባይላችን ከጠፋ ...
04/08/2022

ስልካችን ቢጠፋብን ቀድመን ልናደርገው የሚገባን
-----------------***----------------
የጠፋብን ወይም የተሰረቀ ሞባይል በቀላሉ ማግኘት የምቻልበት መንገድ።
ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቅን በኋላ ወደ ፖሊስ ከመሄድ፥ እግራችን እና እጃችን ሰብስብን ከመቀመጥ፥ በሞባይላችን ያስቀመጥናቸው ኣስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ከጥንቃቄ ጉድለት ጠፍቶብን ወይኔ ከማለት የምያድነን ቀላሉ
መንገድ።

ሞባይል የተለየ የራሱ የሆነ IMEI ኣለው፡፡ ማለትም international mobile equipment Identity የይህንን ቁጥር በመጠቀም ሞባይላችን ያለበት ቦታ ማወቅ እንችላለን።
የሚከተለው መንገድ መከተል እንችላለን።
1) * #06 # ይደውሉ
2)የሞባይላች የተለየ 15 ቁጥሮች ወይም ልዩ ኮድ IMEI ያሳየናል።
3) የይህንን ቁጥር ማስታወሻችን ላይ ማስፈር ፡ ምክንያቱም የይህንን
ቁጥር ሞባይላችን ከጠፋብን ወይም ከተሰረቅን የምንፈልግበት መንገድ ኣንዱ
ዘዴ ነው ። ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ ይህንን ምስጥራዊ ኮድ IMEI
በ ኢሜል( e mail ) ወደ [email protected] ከሚከተለው ዝርዝር ጋር እንልካለን።
# Your name …………………..
# Address …….
# Phone model ….
# Make ….(company name, made in......)
# Last used number ,…………….
# E mail for communication ………
# Missed date ….
#.IMEI number
# በ24 ሰዓታት ውስጥ በተራቀቀው GPRS system በመጠቀም ኣድራሻውን ማግኘት እንችላለን፡፡ ሞባይላችን ከማን እጅ ጋር እንዳለና ማን እየተጠቀመበት እንዳለ ፡ እየተጠቀመበት ያለው ግለሰብ ቁጥር በ email ይላካል ማለት ነው።
Gecho_ICT

"IT" is the power of life!

04/08/2022

ስልክዎ እንዳይጠፋ ኢሜል ላይ ለማስቀመጥ የሚከተለውን ይጠቀሙ።
፩) contact ላይ ይሂዱ።
፪) ከዛ በላይ በኩል 3 ነጠብጣብ ይመጣሉ ይጫኑት።
፫) manage contacts የሚለውን ይጫኑ
፬) default storage location የሚለውን ይጫኑ።
፭) ከዛ የራሰዎን ኢሜል ይምረጡ።
📳ተፈፀመ
https://t.me/gechoICT

04/08/2022

የስልካችን RAM busy እየሆነ ከተቸገርን
ቀላል መፍትሔ
፩) ስልክ መደወየው ላይ ይሂዱ እና * #9900 # ብለው ይጻፉ።
፪)ከሚመጣለወት ዝርዝር ውስጥ delete DumpSTtate/logCAt የሚለውን ይጫኑ።
፫) ከዛ OK ይበሉ እና ይጨርሱ።
📳ተፈፀመ

Gecho_ICT

https://t.me/gechoICT

Firewall ምንድን ነው? ጥቅሙስ?ኮምፒውተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉባጭሩ የኮምፕዩተር ቫይረስ ማለት ልክ እንደ ማንኛውም ፕሮግራም ሆኖ ግን አላማውና አሰራሩ ሌላ ኮምፕዩተር ለ...
03/08/2022

Firewall ምንድን ነው?
ጥቅሙስ?

ኮምፒውተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ
ባጭሩ የኮምፕዩተር ቫይረስ ማለት ልክ እንደ ማንኛውም ፕሮግራም ሆኖ ግን አላማውና አሰራሩ ሌላ ኮምፕዩተር ለመበከል ነው።

ማንኛውም የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለቫይረስ ኢላማ ነው። የኮምፕዩተር ቫይረስ በግለሰብ፣ በድርጂቶች፣ በመንግስቶች፣ በነጋዴወች ወዘተ ይሰራል።

የሌላውን አበላሽተው ለመደሰትም ቫይረስ የሚሰሩ ግለሰቦች አሉ። የዚህንም ያህል የታመሙ ሰወች አሉ። ሁሉም የየራሱ አላማ አለው። የኮምፕዩተር ቫይረስ ውስብስብ ግን መጠኑ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር ሲነጻጻር በጣም ትንሽ ነው። ብዛቱ ሳይሆን ክብደቱና ይዘቱ ትንሽ ሆኖ ግን አደገኛ ነው።

አንቲ ቫይረስ፤ አንቲ ቫይረስ የተሰራው የኮምፕዩተር ቫይረስን ለመከላከል ነው። አሁን ከቅርብ አመታት ወዲህ እራሱ ዊንዶውስ አንቲ ቫይረስ(Windows Defender) በነጻ ለተጠቃሚው ይሰጣል። ሆኖም ግን ሌሎችም የሚሸጡ ነጋዴወች አሉ። ተጠቃሚው እራሱ የትኛውን አንቲ ቫይረስ መግዛት እንደሚፈልግ ይወስናል ማለት ነው። እንደጥራቱ ይለያያል።

የነጻ አንቲ ቫይረሶችም አሉ። በሰፊውና ባይነቱ ለመከላከል ግን የሚገዛው ይሻላል። ለማንኛውም ዊንዶውስ በየጊዜው ስለሚጠቃ አንቲ ቫይረስም ቢሆን ሁሉንም ጥቃት አይከላከልም። አንቲቫይረስ እየሰሩ የሚሸጡ ነጋዴወችም እራሳቸው ቫይረስ ይሰራሉ እየተባለ ይታማሉ።

ፋየርዎል ያልተፈቀደ የኮምፒዩተር ኔትወርክን በመጠቀም ከኮምፒውተር የሚገባንና የሚወጣን ያልተፈቀደ ግንኙነትን ለመከላከል የተነደፈ የደህንነት ስርዓት ነው።

ፋየርዎል ከኮምፒዩተር በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባውን እና የሚወጣውን የኔትወርክ ትራፊክ ይቆጣጠራል።

ፋየርወል በእንግሊዘኛው እሳት የሚከላከል ግድግዳ እንደማለት ነው። ፋየርወል ከውጭ ወደ ኮምፒውተራችን በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባን ቫይረስ መሰል የመረጃ በካይ፣ አጥፊ፣ ሰራቂ፣ ሰላይ ፕሮግራሞች እንዳይገቡ በመጠኑም ቢሆን የሚከላከል ሲሆን በጣም ጠቃሚና ለመረጃ ደህንነት አስፈላጊ የኮምፒውተር ማስተካከያ ነው።

ስለዚህ ኮምፒውተታችንን ከኢንተርኔት ጋር የምናገናኝ ከሆነ የኮምፒውተራችንን Firewall on ማድረግ ይጠበቅብናል ማለት ነው። ስለዚህ ለኮምፕዩተርም መከላከያ የሚሆን ፋየርወል አለ።

ለምሳሌ፣ የእርስዎ የግል ኮምፒውተር ፋየርዎል ከሌለው ወይም ፋየርውሉ ዝግ(Off) ከሆነ ቫይረሶች፣ ማልዌር እና ሰርጎ ገቦች(ሀከር) ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ።

ሁለት አይነት ፋየርወሎች አሉ። አንደኛው ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ጋር አብሮ እዛው ተጠቃሚው ያገኘዋል። (መጨረሻ ላይ ያለውን Step ይከተሉ) ለምሳሌ የዊንዶውስ ኮንትሮል ፓነል ላይ ሄዶ ፋየርወሉን እንደ አስፈላጊነቱ (ከፍተኛ ወይም መካከለኛ) መጠን ላይ መርጦ መቀስቀስ ይቻላል። የሚገዙ አንቲቫይረስ ፕሮግራሞችም የራሳቸው ፋየርወል አላቸው። ሌሎችም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ፋየርወል አላቸው።

የኮምፒውተታችንን ፈየርወል ለማስተካከል ቅደም ተከተል Windows 10, 8, 7: ላይ Control Panel > System and Security > Windows Firewall > Turn Windows Firewall on or off
✅ the bubble next to Turn off Windows Firewall (not recommended) and then select OK.
✅To disable the firewall for private and public networks, select Turn off Windows Firewall (not recommended) in both sections.
Gecho_ICT
https://t.me/gechoICT

የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡ ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CP...
31/07/2022

የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡
ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡

❖በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡

🖱የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡

“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር የሚደረግ CPU ናቸው፡፡
ለምሳሌ Core i7-6700k እና Core i7-5820k ባሉ የሞዴል ቁጥር መጨረሻ ላይ unlocked(ያልተቆለፈ) ስለሆሀን Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) የተሠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ማለት Unloc Processors ከፋብሪካ ዋና ፍጥነቶች በበለጠ ፍጥነት ከመጠን በላይ ሊጫኑ ይችላሉ ፡፡ የተቆለፉ ማቀነባበሪያዎች (Processors) ከመጠን በላይ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) አይችሉም።
ስለዚህ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-8600K

“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።

“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡

🖱በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i7-7700HQ

”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) የደረጋል፡፡

“Y” - Extremely low Power

“U” – Ultra low Power

ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-7200U

"IT" is the power of life!

ከኢንተርኔት ጋር ለመገናኘትየሚያስፈልጉ አራት (4) መሠረታዊ ነገሮች(Four things needed to connect the internet)√ Computer√ ISP(Internet service ...
27/07/2022

ከኢንተርኔት ጋር ለመገናኘት
የሚያስፈልጉ አራት (4) መሠረታዊ ነገሮች
(Four things needed to connect the internet)

√ Computer
√ ISP(Internet service provide)
√ Modem
√ Communication software

Address

14
Bahir Dar

Telephone

+251936323879

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gecho_ICT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gecho_ICT:

Share