Micky Computers

Micky Computers In Front of Bethlehem school Sherif Building 2nd floor

09/08/2023

ኮምፒውተራችን ላይ Sleep, Hibernate, Shutdown ጥቅማቸው ምንድን ነው?
ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ መንቀራፈፍ ይጀምራል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም ማሳረፍ ያስፈልጋል።
ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን። ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው። እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች በዝርዝር እንመለከታለን።
♐️“ስሊፕ”
በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ” የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።
ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል። የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።
ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ። በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ ማድረግ ተገቢ ነው።
♐️“ሸት ዳውን”
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም። በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም። ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር) ይወስዳል።
♐️“ሀይበርኔት”
ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው። “ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ። ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥ ከ“ስሊፕ” አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው። በሀይበርኔትም ሆነ “ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው ሀይል ተመሳሳይ ነው።
ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።
✅ መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?
በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም። ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።
ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።
ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን”ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ ይልቅ “ሀይበርኔት”ን ይመርጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን” ማድረጉ ተመራጭ ነው።
ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው። ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል። ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ። “ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል።በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል።

የኮምፒውተር ሀርድ ዲስክን እንዴት መክፈል እንችላለን?ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ከዚያ በላይ ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው። ለምሳሌ Local disk C:...
02/08/2023

የኮምፒውተር ሀርድ ዲስክን እንዴት መክፈል እንችላለን?
ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ከዚያ በላይ ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው።
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
click on My computer
Manage የሚለውን እንነካለን
ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
#6-ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
ማስጠንቀቂያ:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
እስኪ ለምሳሌ 152 GB ለመክፈል ብንፈልግ ስንት ብለን መጻፍ ይጠበቅብናል?

13/05/2021

DEAR TRAINERS

you can certified in our center with those short term courses
→English Language Skill
→Basic Computer Skill
→Microsoft Office Training
→Computer Programming Languages
→Accounting Peachtree Course

Send a message to learn more

Learning process
11/12/2020

Learning process

Address

Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Micky Computers posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Micky Computers:

Share