Zegerami Job

Zegerami Job Infotainment 24/7
(1)

👉👉👉ከነገ ጀምሮ  የፕላስቲክ ከረጢቶችን ስስ ፌስታል  ይዞ የተገኘ ግለሰብ ከ2 ሺህ ብር ጀምሮ ይቀጣልየአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን  ከነገ ጥር 23 ጀምሮ  ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ...
30/01/2026

👉👉👉ከነገ ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ስስ ፌስታል ይዞ የተገኘ ግለሰብ ከ2 ሺህ ብር ጀምሮ ይቀጣል

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከነገ ጥር 23 ጀምሮ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚጠቀሙ፣ የሚያመርቱና ወደሀገር ውስጥ የሚያስገቡ አካላትን መቅጣት ሊጀመር መሆኑን አሳውቋል።
ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና ይዞ መገኘት የሚከለክለው አዋጅ ከሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጸደቀ ቢሆንም፣ ባለስልጣኑ የስድስት ወራት የሽግግር ጊዜ ሰጥቶ መቆየቱን ገልጿል።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ሀላፊ እና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ አቡኔ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት እገዳው ሁሉንም አይነት ፌስታሎች (ጥቁር፣ ነጭ፣ ትናንሽ እና ትልልቅ) እንደሚያጠቃልል እና በእጁ ፌስታል ይዞ የተገኘ ከነገ ጀምሮ እንደሚቀጣ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የህግ አስከባሪዎች አስፈላጊውን ስልጠና ወስደው በየአካባቢው ለክትትል ዝግጁ የሆኑ ሲሆን ቅጣቱ ይጀመራል ተብሏል፡፡
ህጉን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ በእጅ ይዞ ለተገኘ ግለሰብ፡ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር ቅጣት። ለአምራቾች፣ አከማችዎች እና አከፋፋዮች፡ ከ50,000 እስከ 200,000 ብር ቅጣት እና እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ አቶ ተሾመ አቡኔ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

Via ዳጉ_ጆርናል

የተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ህልፈት ተሰማ! 😭​ ​በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራም እና በተለያዩ የፊልም ስራዎቹ በህዝብ ዘንድ እጅግ የተወደደው አርቲስት ...
16/01/2026

የተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ህልፈት ተሰማ! 😭

​ ​በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራም እና በተለያዩ የፊልም ስራዎቹ በህዝብ ዘንድ እጅግ የተወደደው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ፤ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ዛሬ ረፋድ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

​ነጻነት በስነ-ምግባሩ፣ በፈገግታው እና በሙያ ፍቅሩ የሚታወቅ ታላቅ ባለሙያ ነበር። ነፍስሄር ባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ነበር።

ፈጣሪ ነፍስህን በአጻድ ጻድቅ ያኑርልን!

"ስምንት ጎን" በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሙ ምንድነው❓|•|•ከታች ያሉት ሁለት ፎቶዎች/ምስሎች ተመሳሳይ ቅርጽ አላቸው። ከላይ ያለው መቐለ የሚገኝው የማርያም ጉግሳ ቤተክርስቲያን ጥንታዊ ምስል ነ...
07/01/2026

"ስምንት ጎን" በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሙ ምንድነው❓
|

|

ከታች ያሉት ሁለት ፎቶዎች/ምስሎች ተመሳሳይ ቅርጽ አላቸው። ከላይ ያለው መቐለ የሚገኝው የማርያም ጉግሳ ቤተክርስቲያን ጥንታዊ ምስል ነው።

ከታች ያለው ደግሞ ትናንት በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የኣላፋት ዝማሬ ፕሮግራም መድረክ ነው። እንዴት ሊመሳሰል ቻለ❓
|
በክርስትና ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ የስምንት ጎን (Octagon) ትርጉም የስምንት ጎን ቅርፅ ወይም የስምንት ቁጥር ምልክት እጅግ ትልቅ መንፈሳዊ ምስጢር አለው። ይህ ቅርፅ ብዙውን ጊዜ የሚዘወተረው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስነ ህንጻ፣ በጥምቀት ቦታዎች እና በተለያዩ ንዋያተ ቅድሳት ላይ ነው።

ይህም:-
👉 የስምንት ጎን ቅርፅ ወይም የስምንት ቁጥር ምልክት የአዲስ ጅምር እና የትንሳኤ ምልክት ነው። እንደሚታወቀው በመጽሐፍ ቅዱስ ሰባት ቁጥር የፍጹምነት እና የሥራ ማጠናቀቂያ ምልክት ነው። እግዚአብሔር ዓለምን በስድስት ቀናት ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን አርፏል። ስለዚህ ስምንተኛው ቀን ከሰባቱ ቀናት በኋላ የሚመጣ "አዲስ ቀን" ወይም "አዲስ ጅምር" ነው።

👉 የስምንት ጎን ቅርፅ ወይም የስምንት ቁጥር ምልክት የክርስቶስ ትንሳኤ መገለጫ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳው ከሰንበት በኋላ ባለው በመጀመሪያው ቀን (በስምንተኛው ቀን) ነው። ይህም ለሰው ልጅ አዲስ ሕይወት እና ትንሳኤ የተገኘበት ቀን በመሆኑ ስምንት ቁጥር የትንሳኤ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።

👉 የስምንት ጎን ቅርፅ ወይም የስምንት ቁጥር ምልክት የድኅነት (የመዳን) ምልክት ነው። በኖኅ ዘመን ከጥፋት ውሃ የዳኑት ሰዎች ቁጥር ስምንት ነበር (1ኛ ጴጥሮስ 3፡20)። ይህም ስምንት ቁጥር የሰው ልጅ ከጥፋት ድኖ አዲስ ዓለምን የወረሰበት ምልክት እንደሆነ ያሳያል።

👉 የስምንት ጎን ቅርፅ ወይም የስምንት ቁጥር ምልክት የጥምቀት ምስጢር ነው። በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የጥምቀት ገንዳዎች ባለ ስምንት ጎን ተደርገው ይሰሩ ነበር።

ትርጉሙም ጥምቀት የሰው ልጅ ከኃጢአት ሙትነት ተነስቶ አዲስ ሕይወት የሚጀምርበት "ሁለተኛ ልደት" መሆኑን ለማሳየት ነው። አሮጌው ሰው ሞቶ አዲሱ ሰው የሚነሳበት (Regeneration) ሂደት መሆኑን ይወክላል።

👉 የስምንት ጎን ቅርፅ ወይም የስምንት ቁጥር ምልክት የዘላለም ሕይወት መገለጫ ነው። ሰባት ቁጥር በዚህ ምድር ላይ ያለውን የጊዜ ዑደት (ከሰኞ እስከ እሁድ) ይወክላል። ስምንት ቁጥር ግን ከዚህ ምድር የጊዜ ገደብ ውጭ ያለውን "የዘላለም ሕይወት" ወይም "መንግሥተ ሰማያትን" ያመለክታል። በነገረ መለኮት ትምህርት ስምንተኛው ሺህ ወይም ስምንተኛው ቀን የማይመሽበት የመንግሥተ ሰማያት ምልክት ተደርጎ ይቆጠራል።

👉 በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስነ-ህንጻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ብዙውን ጊዜ ክብ ወይም ባለ ስምንት ጎን ሆነው ይታነጻሉ። ይህ ቅርፅ ምእመናን ከየአቅጣጫው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚመጡ (ሁለንተናዊነትን) ያሳያል። የእግዚአብሔር ፍቅር እና ምሕረት ማብቂያ የሌለው (Infinite) መሆኑን ያመለክታል።

በአጠቃላይ ባለ ስምንት ጎኑ ምስል የትንሳኤ አዲስ ሕይወትን፣ ከኃጢአት መታጠብን (ጥምቀትን)፣ የእግዚአብሔርን አዲስ ኪዳን እና የማያልፈውን የዘላለም ሕይወት ያመለክታል።

Via Tesfaye Y. Hailu

እንኳን ለገና በአል በሰላም አደረሰን!መልካም በአል!!
06/01/2026

እንኳን ለገና በአል በሰላም አደረሰን!
መልካም በአል!!

🇺🇸🇺🇸🇺🇸 VS 🇻🇪🇻🇪🇻🇪አሜሪካ ለሊቱን ሉዓላዊ ሀገር ወደሆነችው ቬንዝዌላ ገብታ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽማ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን እና ባለቤታቸውን ይዛ ከሀገሪቱ ወጥታለች።አሁን ላ...
03/01/2026

🇺🇸🇺🇸🇺🇸 VS 🇻🇪🇻🇪🇻🇪
አሜሪካ ለሊቱን ሉዓላዊ ሀገር ወደሆነችው ቬንዝዌላ ገብታ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽማ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን እና ባለቤታቸውን ይዛ ከሀገሪቱ ወጥታለች።

አሁን ላይ ማዱሮና ባለቤታቸው ሕግ ፊት ሊቀርቡ በአሜሪካ መርከብ ወደ ኒውዮርክ እየተወሰዱ ነው ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል ፤ " የለሊቱን የፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን መያዝ ልክ እንደ ቴሌቪዥን ሾው ነበር ያየሁት " ብለዋል።

" ፍጥነቱን ብታዩ ኖሮ አስደናቂ ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ቡድናቸው እጅግ አስደናቂ ስራ እንደሰራ አወድሰው " ከአሜሪካ ውጪ እንዲህ አይነት ኦፕሬሽን/ተግባር መፈጸም የሚችል ሌላ ሀገር ምድር ላይ የለም " ብለዋል።

Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ

https://youtu.be/6Ccv9ZghJGc
28/12/2025

https://youtu.be/6Ccv9ZghJGc

ኤሚል ቡሶን … በእርግጥ አጊ ሰአሊው ከጥርጣሬ ዝርዝር ውስጥ ነጻ ሊሆን እንደሚችል ገብቶታል ሆኖም በዚያ ረገድ የሚኖረውን ጥርጣሬ ከአእምርዕው ፍጹም ነጻ ለማድረግ ይቻለው ዘንድ ውል .....

21/12/2025

የጊነስ ሪከርድ ባልቤቱ ኪሩቤል ይልማ

https://youtu.be/iN3WFINMFX8
21/12/2025

https://youtu.be/iN3WFINMFX8

ኤሚል ቡሶን … በርግጥ የኤሚል የሰውነት አቋም ይህን ያህል የሚያሸብርና የሚያስደነግጥ አቋሞ አልነበረም። ሆኖም የፈጣንነቱና የጨካኝ ቀዝቃዛ አይኖቹን ሁኔታ አንዴ ያዬ ሁሉ በቀላሉ የ....

👉👉👉"በስንቱ" ሲትኮም እና ኢቢኤስ (EBS) ተለያዩ::ላለፉት ሦስት ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ተወዳጁ የቤተሰብ ድራማ "በስንቱ" ከጣቢያው ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት ማ...
20/12/2025

👉👉👉"በስንቱ" ሲትኮም እና ኢቢኤስ (EBS) ተለያዩ::

ላለፉት ሦስት ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ተወዳጁ የቤተሰብ ድራማ "በስንቱ" ከጣቢያው ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት ማብቃቱን አዘጋጁ አብሪኮም መልቲሚዲያ አስታወቀ።
አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቢኤስ ጋር የነበረው የሦስት ዓመት የሥራ ስምምነት በስኬት መጠናቀቁን ገልጿል።
በዚሁ ምክንያት ድራማው ከፊታችን ጥር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ እንደማይቀርብ ታውቋል።

* የቀጣይ ጉዞ፦
ድራማው ወደፊት ስለሚኖረው ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮች አዘጋጅ ድርጅቱ በቅርቡ ዝርዝር መረጃ ለተመልካቾች እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።
አብሪኮም ላለፉት ዓመታት ከጣቢያው ባለቤቶች እና ሰራተኞች ጋር ለነበረው መልካም የሥራ ቆይታ ያለውን አድናቆት ገልጿል።
"በስንቱ" የቤተሰብ ሲትኮም በቀጣይ በየትኛው ቻናል ወይም ፕላትፎርም ሊቀርብ እንደሚችል በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

©️አብሪኮም መልቲሚዲያ

https://youtu.be/kiDQSUjCUhM
14/12/2025

https://youtu.be/kiDQSUjCUhM

አይሊን ውርኖስ … ነፍሰ ገዳይ ወይስ የስነልቦና ተጠቂ?የስነ ልቦና ባለሞያዎች የአይሊን ዉርኖስን አይነት ድርጊት borderline personality disorder ዋና ምልክት አድርገው ይቆጡሩታል ይህም ከፍተኛ የ....

Address

United States
Addis Ababa
85017

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zegerami Job posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zegerami Job:

Shortcuts

Share